Posts

12 ሺ ቶን ቡና በተጭበርበረ ሰነድ ወደ ውጭ አገር መላኩ ታወቀ

Image
የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የስነምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ በቡና አስተዳደር ላይ የሚታየውን ችግር አስመልክቶ ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ 12 ሺ ቶን ወይም  1 መቶ 20 ሺ  ኩንታል ቡና በተጭበረበረ ሰነድ ወደ ውጭ ተልኮ መሸጡን አመልክቷል። ኮሚሽኑ ቡናው በማን በኩል ተሰርቆ እንደተላከ እያጣራ መሆኑን የዘገበው ሪፖርተር፣ የሽያጩ ገንዘብም ወደ አገር ውስጥ አለመግባቱን ገልጿል። ዛሬ ባለው የአለም የቡና የመሸጫ ዋጋ 120 ሺ ኩንታል ቡና ከ16 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያወጣል። ይህን ያክል ገንዘብ በአንድ ጊዜ በተጭበረበረ ሰነድ መዝረፍ የሚቻልባት አገር ሆናለች የሚለው ዘጋቢያችን፣ ድርጊቱ መንግስት አለ ወይ ያሰብላል ሲል ሃሳቡን አሰፍሯል። አቶ መለስ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት 10 ሺ ኩንታል ቡና መጥፋቱ ይታወቃል። ስለዚሁ ጉዳይ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ መለስ መንግስታቸው እያጣራ መሆኑን ተናግረው ነበር። ይሁን እንጅ የምርመራው ውጤት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የታወቀ ነገር የለም። ዘጋቢያችን እንደሚለው ጸረ ሙስና ኮሚሽን እየመረመርኩ ነው ቢልም፣ የምርመራው ውጤት ታፍኖ ሊቀር የሚችልበት እድሉ ሰፊ ነው። በጉዳዩ ዙሪያ የንግድ ሚኒስቴር ባለስልጣናትን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። http://ethsat.com/amharic/12-%E1%88%BA-%E1%89%B6%E1%8A%95-%E1%89%A1%E1%8A%93-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%8C%AD%E1%89%A0%E1%88%AD%E1%89%A0%E1%88%A8-%E1%88%B0%E1%8A%90%E1%8B%B5-%E1%8B%88%E1%8B%B0-%E1%8B%8D%E1%8C%AD-%E1%8A%A0%E1%8C%88/

ሃዋሳ ሐይቅ እና ወፎቿ

Image
ኣስደዳሚ እና ብርቅዬ የሐዋሳ ሐይቅ ኣእዋፋት ፎቶ ለማየት እዚህ ይጫኑ

የመላው ደቡብ ክልል ስፖርቶች ውድድር በሲዳማ ዞን አሸናፊነት ተጠናቀቀ

Image
አርባምንጭ የካቲት 23/2006 በደቡብ ክልል በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን የስፖርቱን መስክ ከሌሎች የልማት ፕሮግራሞች ጋር አቀናጅቶ በማስኬድ ውጤታማ ስራ መከናወኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዳሴ ዳልኬ ገለጹ። ባለፉት 2 ሳምንታት በአርባምንጭ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የመላው ደቡብ ክልል የልዩ ልዩ ስፖርቶች ውድድር በሲዳማ ዞን አጠቃላይ አሸናፊነት ትናንት ተጠናቋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዳሴ ዳልኬ በስፖርት ውድድሩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን በስፖርቱ መስክ ባስቀመጣቸው ግቦች መሰረት ስኬታማ ውጤቶች አስመዝግቧል፡፡ በእግር ኳስ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት የሚያስችሉ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ስፖርት የአምራቹን ኃይል የአካል ብቃት ለማጎልበትና ጤንነቱን ለመጠበቅ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው የገልጹት ርዕስ መስተዳድሩ  የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህል ልውውጥ በማሳደግና ገጽታን በመገንባት የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ህዳሴ ለማረጋገጥ እንደሚያግዝም ተናግረዋል፡፡ ዘርፉ ለሁለንተናዊ ልማትና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ይበልጥ ለማጠናከር በየደረጃው የሚገኘው አመራር የስፖርት ቤተሰቦችን በማቀናጀት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራም አሳስበዋል። የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መዝርድን ሁሴን በበኩላቸው ላለፉት 2 ሳምንታት በተለያዩ ድማቅ ስነስርዓቶች ታጅቦ ሲካሄድ የቆየው የመላው ደቡብ ስፖርቶች ውድድር ተተኪ ስፖርተኞችን ለይቶ ለማዘጋጀት ማስቻሉን ገልጸዋል። በውድድሩ ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ ከ14 ዞኖችና ከ4

ችግር ፈጥረዋል የተባሉ ስድስት የቡና ነጋዴዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

- በተጭበረበረ ሰነድ የተላከ ቡና የተሸጠበት ዶላር የደረሰበት እየተመረመረ ነው በቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸም ችግሮች ላይ ለመምከር በተጠራው ስብሰባ ላይ ስድስት ታዋቂ የቡና ላኪዎች የችግሩ መስንዔዎች ናቸው በሚል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፡፡ ባለፈው ሐሙስ በንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ ሰብሳቢነት በተካሄደው ስብሰባ 86 ከፍተኛ ቡና ላኪዎች ብሶት የተሞላበት ግልጽ ውይይት ማካሄዳቸውን ስብሰባውን የተካፈሉ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸም ደካማነት መንስዔ ናችው የተባሉት ስድስት ታዋቂ ቡና ላኪዎች በግልጽ ጣት እንደተቀሰረባቸውና በመጨረሻም ይቅርታ መጠየቃቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ስድስቱ ቡና ላኪዎች ሙለጌ፣ ሆራ ትሬዲንግ፣ ትራኮን ትሬዲንግ፣ ከማል አብደላ ቡና ላኪ፣ ለገሰ ሸሪፍ ቡና ላኪና አልታ አግሪ ቢዝነስ ናቸው ተብሏል፡፡  እነዚህ ቡና ላኪዎች ላይ የቀረበው ቅሬታ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ በውድ ዋጋ ቡና እየገዙ በዓለም ገበያ በርካሽ ይሸጣሉ የሚል ነው፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ይህንን የሚያደርጉት በውድ ገዝተው እየከሰሩ የሚሸጡት ከውጭ የሚመጣውን የውጭ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ ለሚያስገቡ  ሸቀጣ ሸቀጦች እንዲጠቀሙበት ስለሚፈቀድ ነው ተብሏል፡፡ ነጋዴዎቹ በዚህ አካሄድ በቡናው ንግድ የከሰሩ ቢመስልም፣ ከውጭ በሚያስገቧቸው የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች እንደሚያካክሱ ተገልጿል፡፡ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ እነዚህን ጉዳዮች በስብሰባው ላይ ሲያነሱ ከቡና ላኪዎች ቅሬታ ቀርቦላቸዋል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ስድስት ቡና ላኪዎች ቡና በውድ ዋጋ እየገዙ በርካሽ ሲሸጡ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በዚህም በርካታ የቡና ነጋዴዎች ትክክለኛ ዋጋ በጨረታ አቅርበው ማሸነፍ ባለመቻላቸው ለኪሳራ ተዳርገዋል፡፡ ነገር ግን መ

Wolassa Kumo, and the Independence Struggle for the Sidama Land

Image
By:  Muhammad Shamsaddin Megalommatis   Wolassa Kumo reveals details about the Loqqe massacre that, carried out by the Abyssinian tyrant Meles Zenawi, consists in sufficient reason for us to raise the issue of the criminally ignored by the materialistic and apathetic Western World Sidama Genocide.  We end this brief introduction by formulating an alarming warning for the devious international community our decayed times: when you focus on one, and forget numerous other genocides, more genocides will happen to you.  Supporting the Sidama Pledge for Independence today is not a matter of mere Humanism; it becomes an issue of instinctive self-defense against Evil. To read more