Posts

አዲስ አበባን እና ሃዋሳን ጨምሮ በ24 ከተሞች የመሬት ይዞታ ምዝገባ ሊጀመር ነው

Image
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በአዲስ አበባና በ23 ከተሞች የመሬት ይዞታ ምዝገባን ለማከናወን የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውን የከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የፌዴራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ኤጀንሲ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ከበደ እንዳሉት፥ የመሬት ይዞታ ምዝገባው ከተሞች ያሏቸውን ለልማት ዝግጁ የሆኑ መሬቶች እንዲያውቁ ከማስቻሉም በላይ የይዞታ ይገባኛል ክርክርን ያስቀራል። ለኢንቨስትመንት አጋር የሆኑት ባንኮችም ከስጋት ነጻ የሆነ የብድር አገልግሎት እንዲቀርቡ ያስችላቸዋል ነው ያሉት። ምዝገባውን በከተሞቹ ለመጀመር አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ማለትም የከተሞች ካርታ ስራና የሲስተም ልማት ስራዎች ተጠናቀዋል ብለዋል። የመሬት ይዞታ ምዝገባው በተመረጡ 69 ከተሞችም በቀጣይ እንደሚከናወንም ገልፀዋል። በአማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ክልልች ስርአቱን የሚያግዙ ማዕከላት ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን፥  የይዞታ መሬት ምዝገባው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚከናወን ይሆናል ሲሉ አክለዋል። ምዝገባው በህግ ወጥ መልኩ ተይዘው የነበሩ ይዞታዎችን ወደ መሬት ባንክ እንዲመለሱ የሚያደርግ ሲሆን፥ ሀገሪቱ ለልማት የምታውለው ተጨማሪ መሬትም እንድታገኝ ያስችላታል ነው የተባለው። አሰራሩ የሀገሪቱን የመሬት ሀብት ከአንድ ማዕከል ማወቅ የሚቻልበት አሰራር ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

ኣዳሬ_ሃዋሳ

Image
በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር የቀረበ

ETHIOPIA: THE SIDAMA AND GUJI ZONE

Image
FOR THE MOST PART, I REMAIN RELATIVELY UNBIASED WHEN IT COMES TO PRODUCING COUNTRIES. YOU KNOW, IT’S NOT JUST ABOUT THE TERROIR, IT’S ABOUT UNDERSTANDING YOUR PRODUCT AND MARKET — WITH A LITTLE OLD FASHIONED HARD WORK THROWN IN TOO. MOST COFFEE FARMERS HAVE ALL THE POTENTIAL IN THE WORLD. YES, IT’S TRUE THAT SOME DO LIVE ON THE SUNNIER SIDE OF THE HILL, OR AT THE HIGHEST PEAK WHICH CAN PROVIDE SOME ADVANTAGE TO CUP QUALITY. HOWEVER FOR THE MOST PART, VARIETY, PROCESSING, SOIL NUTRIENTS AND SELECTIVE PICKING ARE THINGS YOU CAN HAVE SOME CONTROL OVER IN ORDER TO INCREASE THE QUALITY AND UNIQUENESS OF YOUR COFFEE. AFTER SPENDING THE PAST COUPLE OF YEARS VISITING THE COFFEE GROWING COUNTRIES OF THE WORLD, I FINALLY MADE MY WAY TO ETHIOPIA, THE BIRTHPLACE OF COFFEE. ONLY TO DISCOVER THAT MOST OF THEIR SECRET LIES IN THE GIFTS MOTHER NATURE HAS PROVIDED FOR THEM. There is something about a great Ethiopian coffee that I really appreciate. For the most part, I would consider them some of

አንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ከመድረክ አባልነት በጊዚያዊነት ታገደ፤ የሲዳማ አርነት ንቅናቄን በአዲስ አባልነት ተቀበለ

Image
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣  2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ትናንት 9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡ አንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ከመድረክ አባል ፓርቲነት በጊዜያዊነት እንዲታገድ ጉባኤው መወሰኑንም የመድረክ አመራሮች አስታውቀዋል፡፡ የመድረክ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና እንደተናሩት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የመድረክን መግባቢ ሰነድ በሚጻረር መልኩ የሰጡትን መግለጫ በይፋ እንዲያስተባብሉ ቢጠየቁም ባለማስተካከላቸው አንድነት በጊዜያዊነት ከመድረክ አባል ፓርቲነት ታግዶ እንዲቆይ በጉባኤው ተላልፏል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው በበኩላቸው የመድረክ ውሳኔ ትክክል አይደለም ብለዋል፡፡ አንድነት የሚያስተባብለው ነገር የለም ብለዋል። እንድም የሰጠነው አስተያየት የለም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ እንደ ተቋም መድረክን ገምግመን ሰጥተናል፤  እገዳው ለምን እንደሆነ አልገባንም ብለው ለኢሬቴድ ገልጸዋል። ጉባኤው የሲዳማ አርነት ንቅናቄን  በአዲስ አባልነት ተቀበሏል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የምደባ ማስተካከያዎች ችግር እየፈጠሩ መሆኑ ተገለፀ

Image
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ. ) ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚመደቡበት ወቅት የሚደረጉ ማስተካከያዎች ችግር እየፈጠረብን ነው አሉ ዩንቨርስቲዎች። ዛሬ እዚህ አዲስ አበባ ላይ ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪጅስትራር የተውጣጡ ባለሙያዎች ከሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር እየተወያዩ ነው። በውይይቱ ፥ የትምህርት ክፍሎች ካላቸው አቅም በላይ እና በታች የተማሪ ቁጥር መመደብ እንደ ክፍተት ተነስቷል ። ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጓቸው አካል ጉዳተኞች ፤ ሴቶች እና ሌሎችም መረጃን በአግባቡ ባለመሙላትም የሚፈጠሩ ክለሳዎች ፥ ዩንቨርስቲዎችን ለተጨማሪ ስራና የጊዜ ብክነት እየዳረጉ ስለሆነ ሊቀረፍ ይገባል ብለዋል። የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሪክተር አቶ አርአያ ገብረ እግዚአብሄር በበኩላቸው ፥ የተነሱትን ሀሳቦች በመያዝ ለቀጣይ ምደባ የተሻለ ነገር ለመስራት አልሞ የተዘጋጀ መድረክ በመሆኑ እንደ ግብአት ወስደን የተሻለ ጥራት ያለው ስራ ለመስራት እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል። በውይይቱ የተማሪዎች ምደባ አፈፃፀም መመሪያ ማሻሻያ ላይ ውይይት ይደረጋል።