Posts

የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቁንጥጫ በርትቷል

Image
ፎቶ ሪፖርተር ጋዜጣ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ግቦች መሠረት በማድረግ የተጀመሩ በርካታ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ ፈርጀ ብዙ ግንባታዎች በሚካሄዱበት አገር ውስጥ ለዓመታት አስቸጋሪ የነበሩ ኋላ ቀር የአገልግሎት ዘርፎች የሚፈጥሩትን ችግር እያየን ነው፡፡ ከኋላ ቀር አሠራርና አኗኗር ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት መሰናክል ሲሆኑበትም ይታያል፡፡ እነዚህን መሰናክሎች እንዲህ ማየት የግድ ይላል፡፡  1.የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቆራረጥ  ምንም እንኳን በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ማጠቃለያ ላይ የአገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አቅም አሥር ሺሕ ሜጋ ዋት ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ቢባልም፣ በአገሪቱ ውስጥ ካሉ የተለያዩ የኃይል ማመንጫዎች የሚገኘውን ከሁለት ሺሕ ሜጋ ዋት በላይ ኃይል በቅጡ ማሰራጨት አልተቻለም፡፡ ለትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሳካት ጉልህ ሚና ይኖራቸዋል ተብለው የሚታሰቡ ትላልቅና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በኃይል መቆራረጥና እጥረት ምክንያት ማምረት እየተቸገሩ ናቸው፡፡  ከፍተኛ ኢቨስትመንት የፈሰሰባቸው የተለያዩ የንግድ፣ የማምረቻና የአገልግሎት ተቋማት በኃይል መቋረጥ ምክንያት ለኪሳራ እየተዳረጉ ናቸው፡፡ የባንክ ብድር መመለስ እስኪያቅታቸው ድረስ ምርት እየተስተጓጐለባቸው ነው፡፡ የተመረተውን ምርት መሸጥ አልተቻለም፡፡ ሆቴሎች ለጄኔሬተርና መሰል የኃይል አማራጮች ለከፍተኛ ወጪ እየተዳረጉ ናቸው፡፡ በኢንቨስትመንት አካባቢ ከፍተኛ ጉዳት እያጋጠመ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ በቢሮዎች፣ በመኖሪያ ቤቶችና በመሳሰሉት ከግለሰብ እስከ አገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ነው፡፡ ሕፃናትን መመገብና መንከባከብ የማይቻልበት ደረጃ እየተደረሰ ነው፡፡ በቤተሰብ ደረጃ እንኳ ቢታይ

የፊታችን ማክሰኞ ሀዋሳ ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፤ ሲዳማ ቡና ከሙገር ሲሚቶ በተመሳሳይ 9 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፤ መልካም እድል ለሲዳማ ክለቦች!

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ. ) አስራ አንደኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ቀጥሎ ይካሄዳል። ዛሬ መብራት ሃይል ከኢትዮጵያ መድን 8 ሰዓት ላይ ፤ ኢትዮጵያ ቡና ከዳሽን ቢራ 10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ። ከነገ በስቲያ አርባ ምንጭ ላይ አርባምንጭ ከነማ ከሃረር ቢራ 10 ሰዓት ላይ ጫወታቸውን ያደርጋሉ። የፊታችን ማክሰኞ ደግሞ ሀዋሳ ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፤ ሲዳማ ቡና ከሙገር ሲሚቶ በተመሳሳይ 9 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ። በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግና የኮንፌደሬሽን ዋንጫ ነገ ደደቢትናመከላከያ የመልስ ጫዋታቸውን ያደርጋሉ። 2 ለ0 የተሸነፈው መከላከያ የመልስ ጨዋታውን ነገ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያካሂዳል። ደደቢት በበኩሉ ወደ ዛንዚባር ተጉዞ ነገ ከኬኤም ኬኤም ጋር የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል። በሌላ በኩል አምስተኛው ዙር የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ዛሬና ነገ ይካሄዳል። ዛሬ 9 ሰዓት ከ45 ሰንደርላንድ ከሳውዝአምፕተን ሲጫወት ፤ ካርዲፍ ሲቲ ዊጋንን 12 ሰዓት ላይ ይገጥማል። ትልቅ ግምት ባገኘው ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ  በሜዳው ቼልሲን ምሽት 2 ሰዓት ከ15 ላይ ይፋለማል። ነገ ደግሞ አርሰናል ሊቨርፑልን ምሽት 1 ሰዓት ላይ በሜዳው ያስተናግዳል።

በመላ የደቡብ ክልል ጨዋታ የሚሳተፉ የስፖርት ልኡካን አርባምንጭ ከተማ እየገቡ ነው፤ መልካም እድል ለሁለት ተከፍለው ለምሳተፉ ለሲዴዎች

አርባምንጭ የካቲት 8/2006 በደቡብ ክልል በአርባምንጭ ከተማ ከነገ ጀምሮ በሚካሄደው መላ የደቡብ ጫዋታዎች ላይ የሚሳተፉ የስፖርት ልዑካን አርባምንጭ ከተማ በመግባት ላይ መሆናቸውን የዝግጅት ኮሚቴው ገለጸ። የዝግጅት ኮሚቴው ሰብሳቢና የጋሞጎፋ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ጣሰው ጫቾ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከአራት ሺህ የሚበልጡ ስፖርተኞችና የስፖርት ቤተሰቦች የሚሳተፉበትና ለሁለት ሳምንት በ17 የስፖርት ዓይነት ውድድር ይካሄዳል።  የጋሞ ጎፋ ዞን ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲና ከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት ከክልሉ 15 ዞኖችና 4 ልዩ ወረዳ በጫዋታው የሚሳተፉ የስፖርት ልዑካንን ለማስተናገድ ሁሉን አቀፍ ዝግጅት አጠናቆ እንግዶችን በመቀበል ላይ መሆኑን ገልጸዋል። እስከአሁን የአዋሳ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የ12 ዞኖችና የሁለት ልዩ ወረዳ የስፖርት ልዑካን አርባምንጭ ከተማ ደርሰዋል። በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአባያ ካምፓስ በሚገኘው ትልቁ ስታዲዮም ነገ በድምቀት በሚጀምረው የመክፈቻ ስነ ስርአት ላይ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትና የስፖርት ቤተሰቦች እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የባለሥልጣናት ሃብት ተመዝግቦ አያልቅም እንዴ?

የሃብታቸው መጠን ይፋ የሚደረገው  ከስልጣን ሲወርዱ ይሆን? (ያመለጡን አሉ!) በሃብት ምዝገባው ላይ የትዳር አጋርም  ሊካተት ይገባል (መነጣጠቅ ተጀምሯላ!) “Grand corruption” አለ የሚባለው ገንዘብ ሚኒስቴር ሲዘረፍ ነው እንዴ? የእነቴሌ “የእንኳን አደረሳችሁ” መልዕክት “ፅድቁ ቀርቶብኝ--” ያሰኛል! ኢትዮ- ቴሌኮም በየበዓሉ የሚልከው የ “እንኳን አደረሳችሁ” መልካም ምኞት አሁን አሁን “ሙስና” እየመሰለኝ መጥቷል፡፡(ግራንድ ኮራፕሽን ሳይሆን ሚጢጢዬ ሙስና!) ለነገሩ ቢመስለኝም እኮ አይፈረድብኝም፡፡ ለምን መሰላችሁ? ዓመቱን ሙሉ በብዙ የአገልግሎት አሰጣጦች ችግር ሲያማርረን ከርሞ --- በዓል ሲደርስ እንደ ደህና አገልጋይ “እንኳን አደረሳችሁ” የሚለን ሊደልለን ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? (“ደለለኝ --- ደለለኝ” ነው ያለችው ድምፃዊቷ) ነፍሷን ይማረውና! እውነቴን እኮ ነው… ኔትዎርክ ሳይኖር፣ ኢንተርኔት ተቋርጦ፣ የቢሮና የቤት ስልክ ጠፍቶ… እንዴት ነው “እንኳን አደረሳችሁ” የሚለን? (ያውም ለእኛ አሻፈረኝ በሚለን ኔትዎርክ!) እኔ የምለው ---- እኛና ቴሌ የምንተዋወቀው በስልክ አገልግሎት አይደለም እንዴ? (ከዚያ ውጭ የት ስንተዋወቅ ነው!) ከሁሉም የሚገርመኝ ደሞ ”ከመጪው ዘመን ጋር አገናኛችኋለሁ” የሚለው ፉከራው ነው፡፡ (“ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” አሉ!) እንኳንስ ከመጪው ዘመን… ከዛሬ ጋር እንኳን መች ተገናኘን! (ማን ነበር “አቅምን አውቆ ማደር ጥሩ ነው ታላቅ ችሎታ ነው” ያለው?!) አሁንማ ከምንፈልገው ሰው ጋር መገናኘት አይደለም--- ሂሳብ ለመሙላትም ኔትዎርክ ማግኘት መከራ ሆኗል (ቴሌኮም በነፃም እንኳን ገንዘብ አልቀበልም እያለን እኮ ነው!) እስካሁን የውሃና የመብራት መ/ቤቶች ለገና በዓል “እንኳን አደረ

ልጓም ያልተገኘለት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ

Image
መንግስት የነዳጅ ዋጋን ማረጋጋት አለበት” (ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ ብሩህ ተስፋ) ባለፉት 8 ዓመታት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከአራት እጥፍ በላይ አድጓል የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መንግስት ለዜጎቹ ግድ ማጣቱን አመላካች ነው፡፡(የከተማዋ ነዋሪ) የስምንት ዓመት የዋጋ ንረት     1998         2006 ቤንዚን             6.57        20.47 ነጭ ጋዝ            3.45        15.75 ታክሲ (አጭር ርቀት)        0.60ሳ        1.50 ታክሲ (ረዥም ርቀት)    1.25        3.00 አንበሳ አውቶብስ        0.50ሳ        300% ጭማሪ አቶ መስፍን ወርቅነህ በመንግስት መ/ቤት የንብረት አስተዳደር ክፍል ውስጥ ተቀጥረው መስራት ከጀመሩ ወደ 18 ዓመት ገደማ አስቆጥረዋል፡፡ ሥራ ሲጀምሩ የወር ደመወዛቸው 720 ብር ነበር፡፡ በሥራ ዘመናቸው ለሦስት ጊዜ ያህል የደረጃ ዕድገቶችና የደመወዝ ጭማሪ ዕድሎችን አግኝተዋል፡፡ በ18 ዓመት ጊዜ ውስጥ ደሞዛቸው 1690 ብር ደርሷል፡፡ ከ15 ዓመት በፊት ትዳር የመሰረቱት በ280 ብር ከግለሰብ በተከራዩት ቤት ውስጥ ሲሆን ሦስት ልጆቻቸው የተወለዱትም እዚሁ ቤት ውስጥ ነው፡፡ የዛሬ 10 ዓመት ገደማ አከራያቸው ድንገተኛ የሃምሳ ብር ጭማሪ ሲያደርጉባቸው ክው ብለው ደነገጡ፡፡ የከተማው ዳርቻ አካባቢ አነስተኛ የኪራይ ቤት ማሰስ ጀመሩ።  በመጨረሻም አየር ጤና የተባለው ሰፈር በ200 ብር የኪራይ ቤት አገኙና ቤተሰባቸውን ይዘው ገቡ፡፡ አቶ መስፍን ከከተማ ወጣ ብለው ቤት የተከራዩት፣ወጪያቸውን በመቀነስ የሚያገኟትን ደሞዝ አብቃቅተው ሦስቱን የአብራካቸውን ክፋዮች ሳይርባቸው ሳይጠማቸው አሳድጋለሁ በሚል ነበር፡፡ ጊዜው ግን ከእሳቸው ጋር እልህ የተጋባ መሰለ፡፡ ከዓመት ዓመት ኑሮው ወ