Posts

ልጓም ያልተገኘለት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ

Image
መንግስት የነዳጅ ዋጋን ማረጋጋት አለበት” (ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ ብሩህ ተስፋ) ባለፉት 8 ዓመታት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከአራት እጥፍ በላይ አድጓል የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መንግስት ለዜጎቹ ግድ ማጣቱን አመላካች ነው፡፡(የከተማዋ ነዋሪ) የስምንት ዓመት የዋጋ ንረት     1998         2006 ቤንዚን             6.57        20.47 ነጭ ጋዝ            3.45        15.75 ታክሲ (አጭር ርቀት)        0.60ሳ        1.50 ታክሲ (ረዥም ርቀት)    1.25        3.00 አንበሳ አውቶብስ        0.50ሳ        300% ጭማሪ አቶ መስፍን ወርቅነህ በመንግስት መ/ቤት የንብረት አስተዳደር ክፍል ውስጥ ተቀጥረው መስራት ከጀመሩ ወደ 18 ዓመት ገደማ አስቆጥረዋል፡፡ ሥራ ሲጀምሩ የወር ደመወዛቸው 720 ብር ነበር፡፡ በሥራ ዘመናቸው ለሦስት ጊዜ ያህል የደረጃ ዕድገቶችና የደመወዝ ጭማሪ ዕድሎችን አግኝተዋል፡፡ በ18 ዓመት ጊዜ ውስጥ ደሞዛቸው 1690 ብር ደርሷል፡፡ ከ15 ዓመት በፊት ትዳር የመሰረቱት በ280 ብር ከግለሰብ በተከራዩት ቤት ውስጥ ሲሆን ሦስት ልጆቻቸው የተወለዱትም እዚሁ ቤት ውስጥ ነው፡፡ የዛሬ 10 ዓመት ገደማ አከራያቸው ድንገተኛ የሃምሳ ብር ጭማሪ ሲያደርጉባቸው ክው ብለው ደነገጡ፡፡ የከተማው ዳርቻ አካባቢ አነስተኛ የኪራይ ቤት ማሰስ ጀመሩ።  በመጨረሻም አየር ጤና የተባለው ሰፈር በ200 ብር የኪራይ ቤት አገኙና ቤተሰባቸውን ይዘው ገቡ፡፡ አቶ መስፍን ከከተማ ወጣ ብለው ቤት የተከራዩት፣ወጪያቸውን በመቀነስ የሚያገኟትን ደሞዝ አብቃቅተው ሦስቱን የአብራካቸውን ክፋዮች ሳይርባቸው ሳይጠማቸው አሳድጋለሁ በሚል ነበር፡፡ ጊዜው ግን ከእሳቸው ጋር እልህ የተጋባ መሰለ፡፡ ከዓመት ዓመት ኑሮው ወ

An awakening giant

Image
If Africa’s economies are to take off, Africans will have to start making a lot more things. They may well do so LESS than an hour’s drive outside Ethiopia’s capital, Addis Ababa, a farmer walks along a narrow path on a green valley floor after milking his cows. Muhammad Gettu is carrying two ten-litre cans to a local market, where he will sell them for less than half of what they would fetch at a dairy in the city. Sadly, he has no transport. A bicycle sturdy enough to survive unpaved tracks would be enough to double his revenues. At the moment none is easily available. But that may be about to change. An affiliate of SRAM, the world’s second-largest cycle-components maker, based in Chicago, is aiming to invest in Ethiopia. Its Buffalo Bicycles look ungainly but have puncture-resistant tires, a heavy frame and a rear rack that can hold 100kg. They are designed and assembled in Africa, and a growing number of components are made there from scratch, creating more than 100 man

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስትር ካላ ሐርቃ ሐሮዬ በገበያ ውድድር ፖሊሲ እና ሕግ ላይ ያቀረቡት የምርምር ጽሑፍ

Image
ካላ ሐርቃ ሐሮዬ በኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ታሪክ የመጀመሪያው የሲዳማ ተወላጅ ሚኒስትር በመሆናቸው የምታወቁት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስትር ካላ ሃርቃ ሃሮዬ ከሰሯቸው የምርምር ስራዎች መካከል  COMPETITION POLICIES AND LAWS: Major Concepts and an Overview of Ethiopian Trade Practice Law በምል ርዕስ ያቀረቡትን የምርምር ስራቸውን እንድያነቡ ኣቅርበነዋል። የምርምር ስራውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ከልማድ ያልተላቀቁት የአቤቱታ ደንቦች

መኳንንት ከሕግ ትምህርት ቤት ተመርቆ ሲወጣ ግር ያለው ነገር የትምህርቱና የአተገባበሩ ልዩነት ነው፡፡ በአብዛኛው በንድፈ ሐሳብ አስተምህሮና ትንተና ላይ የሚተኮረው ትምህርቱ በተግባር ከሚታየው የፍርድ ቤት ነባራዊ ሁኔታ ጋር አልታረቅ ብሎት ተቸግሯል፡፡ ይህን ችግሩን ያባባሰው ደግሞ ከቤተሰቡ አንዱ የወራሽነት የምስክር ወረቀት ከፍርድ ቤት እንዲሰጠው በማሰብ አቤቱታውን እንዲያዘጋጅለት ሲጠየቀው ነው፡፡ አቤቱታውን አዘጋጅቶ ለቤተሰቡ አባል ቢሰጠውም በአንዱ ክልል ከሚገኘው የወረዳ ፍርድ ቤት የገጠመው ነገር ሌላ ነው፡፡ ቤተ ዘመዱ በፍርድ ቤቱ አቤቱታው በትክክል አለመጻፉን ተነግሮት በፍርድ ቤቱ ደጃፍ ከሚገኙት ራፖር ጸሐፊ ተጽፎ እንዲመጣ ተመከረ፡፡ ሰውዬውም የተባለውን ፈጽሞ አቤቱታው ተቀባይነት አግኝቶ የወራሽነት የምስክር ወረቀት አገኘ፡፡ የመኳንንትና የራፖር ጸሐፊው አቤቱታ ልዩነት ቀላል ነበር፡፡ የመኳንንት አቤቱታ ፍሬ ነገሩን በአጭር የሚገልጽ፣ የሕግና የማስረጃ ትንተና የሌለውና ግልጽ ዳኝነትን የሚጠይቅ ነበር፡፡ የራፖር ጸሐፊው አቤቱታ ግን ረዥም፣ ውስብስብ የሕግ ቃላትን የሚጠቀምና በብዙ የሕግ ድንጋጌ የተዘበዘበ ነበር፡፡ ይህን የተረዳው መኳንንት አምስት ዓመት የተማረበት የሕግ ትምህርት ሥልጠና የማይፈልግና በፍርድ ቤት ተግባራዊ ረብ የሌለው መስሎት ተከዘ፡፡ የተወሰኑ ዓመታትን በሕግ ሙያ አገልግሎት ካሳለፈ በኋላ ግን ለዘመናት የዳበረውን ልምድ መስበር አስቸጋሪ ስለመሰለው ራሱን በተወሰነ ደረጃ ከተለመደው አሠራር ጋር አቀራረበ፡፡ አሁን ለአቤቱታ ርዝመት ጭንቀት የለውም፣ የሕግ ድንጋጌዎችን በዓይነት ለመዘብዘብ፣ የሕግና የማስረጃ ትንታኔዎችን ለማግተልተል ቀዳሚ አይገኝለትም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፍርድ ቤቶች የአሠራር ማሻሻያ በማድረግ፣ የሬጅስትራርና

‹‹የተቃዋሚ ድርጅት አባል ሆኖ ከመንግሥት ሥራ ማግኘት ከባድ ነው››፦ በሲዳማም እውኔታው ከዚህ የተለየ ኣይደለም

Image
ፎቶ ኢትዮጵያን ሪፖርተር ጋዜጣ  ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ የኮንስትራክሽን ሥራና የሆቴል ባለቤት ተወልደው ያደጉት በኦሮሚያ ክልል ጂማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ጋሉ አካባቢ ነው፡፡ ትምህርታቸውን በጂማ ዞን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ከተከታተሉ በኋላ በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ ለዓመታት በጂማ ማዘጋጃ ቤት ከዚያም ባቱ (ዝዋይ) ከተማ በሚገኘው ሼሪ ኢትዮጵያ አበባ እርሻ ውስጥ በቴክኒካል ማኔጀርነት ሠርተዋል፡፡ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ በአሁኑ ወቅት የራሳቸውን የኮንስትራክሽን ኩባንያ አቋቁመውና በመቂ ከተማ  ሆቴል ከፍተው በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢንጂነር ዘለቀ ከቢዝነስ ሥራቸው ውጭ በፖለቲካም ንቁ ተሳታሳፊ ናቸው፡፡ ሥራቸውን አስመልክቶ  ውድነህ ዘነበ  አነጋግሯቸዋል፡፡ ሪፖርተር:-  በሆቴልና በኮንስትራክሽን ሥራዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሥራዎች ውስጥ ሆቴሉ በምን ደረጃ እንደሚገኝ ቢገልጹልኝ? ኢንጂነር ዘለቀ :- ሆቴሉ የሚገኘው ከአዲስ አበባ ወደ ሐዋሳ በሚወስድ መንገድ ላይ በምትገኘው መቂ ከተማ ነው፡፡ የቱሪስት ማረፊያ የቱሪስት መሸጋገሪያ ለማድረግ ሆቴሉን በአዲስ መልክ  እንደገና ልገነባ እየተዘጋጀሁ ነው፡፡ ሪፖርተር:- በኮከብ ደረጃ ለማሳደግ ነው? ኢንጂነር ዘለቀ :- አዎ፡፡ በኮከብ ደረጃ ለማሳደግ ነው እቅዴ፡፡ ምክንያቱም መስመሩ የቱሪስት ነው፡፡ በርካታ ቱሪስቶች ይመጣሉ፡፡ ሆኖም በመስመሩ ጥሩ ሆቴል አያገኙም፡፡ የግድ ሐዋሳ መጓዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አማካይ ቦታ ላይ ጥሩ ሆቴል ቢሠራ ከሚል ነው ይህንን እቅድ ያመነጨሁት፡፡ አሁን ነባሩን ሆቴል አፍርሼ ዘመናዊ ባለ ኮከብ ሆቴል ለመገንባት ዲዛይን እየሠራሁ እገኛለሁ፡፡ ከአዲስ አበባ እስከ ሐዋሳ 270 ኪሎ ሜትር ነው፡፡ መቂ በሁለቱ ከተሞች አማካይ ቦታ ላይ ትገኛለች፡