Posts

የግብፅ ሚኒስትር የግድቡ ግንባታ እንዲቆም በመጠየቃቸው ውይይቱ ተቋረጠ

Image
የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትር መሐመድ አብዱል ሙታሊብ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ለማድረግ በጠየቁት መሠረት ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ ቢገቡም፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲቆም በመጠየቃቸው ውይይቱ በሰዓታት ውስጥ ተቋረጠ፡፡ የግብፅ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ አለማየሁ ተገኑና ከባልደረቦቻቸው፣ እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተወከሉ ባለሙያዎች ጋር ባለፈው ሰኞ መገናኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡  በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና ተያያዥ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ከጋዜጠኞች ጋር ለመወያየት ባዘጋጀው መድረክ ላይ የተገኙት አቶ አለማየሁ ተገኑ፣ የግብፅ አቻቸው ሁለት አጀንዳዎችን ይዘው መቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡  የግብፅ ሚኒስትር በስልክ ደውለው ወደ አዲስ አበባ ለመምጣትና ለመወያየት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት መገኘታቸውንና ይዘው የመጡዋቸው አጀንዳዎችም ከዚህ ቀደም ተቀባይነት ሊያገኝ ያልቻለውን የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ተጨማሪ ጥናት እንዲያከናውን የሚጠይቅ፣ እንዲሁም በግንባታው ላይ መተማመንን ማጐልበት የሚሉ ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡  የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድንን በተመለከተ ኢትዮጵያና ሱዳን እንደማይቀበሉት ከዚህ ቀደም መገለጹንና አሁንም ይህንን አቋም በድጋሚ እንዲገነዘቡት መደረጉን አቶ አለማየሁ አስረድተዋል፡፡ በግድቡ ግንባታ ላይ መተማመንን ማጐልበት በሚል በግብፅ በኩል በቀረበው ሐሳብ ውስጥ የቀድሞው የግብፅ የውኃ መጠን እንደማይቀንስ ኢትዮጵያ እንድታረጋግጥ የሚጠይቅ መሆኑን ሪፖርተር ያገኛቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህንን በተመለከተ በሰኞው ስብሰባ የግብፁ ሚኒስትር በድጋሚ አንስተው ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ግልጽ እንደተደረገላቸው አቶ አለማየሁ በ

የሲዳማ ቡና የእግር ኳስ ክለብ በዞኑ መንግስት ትኩረት ተነፍጓል ተባለ

Image
ከሲዳማ ዞን መንግስት ትኩረት የተነፈገው የሲዳማ ቡና የእግር ኳስ ክለቡ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ ውድድር ያለ ውጤት ጉዞውን ቀጥሏል። ሲዳማን በወከል በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ ውድድር በመሳተፍ ላይ ካሉት የእግር ኳስ ክለቦች መካከል የይርጋዓለም ከተማ ተወካይ የሆነው ሲዳማ ቡና በተከታታይ ሽንፈትን ማስተናገዱን ቀጥሏል። እስከኣሁን ደረስ ካደረጋቸው ኣስር ጫዋታዎች መካከል ከኢትዮጵያ መብራት ኃይል ጋር የደረገውን  ጫዋታ ከማሸነፉ ሌላ በተቀሩት በስድስት ጫዋታዎች በመሸነፍ እና በሁለቱ ብቻ ነጥብ በመጋራት በደረጃ ሰንጠረ ዥ ኣስራ ሶስተኛ ደረጃ ይዞ ይገ ኛ ል። በዘንድሮው የውድድር ዘመን የክለቡ ውጤት ኣልባ ጉዞ  የሲዳማ ዞን መንግስትን ጨምሮ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ኣካላት ትኩረት በ መነፈጉ የተነሳ መሆኑን ኣንዳንድ የክለቡ ደጋፊዎች ተናግረዋል ። በጉዳዩ  ዙሪያ ሪፖርተራችን ቱንስሳ ጂሎ በይርጋኣለም ከተማ ያናገራቸው የክለቡ ደጋፊዎች እንደምሉ ት ከሆነ ፤ የሲዳማ ክለቦች ያልሆኑትን እንደወላይታ ዲቻ ያሉትን በቅርብ በፕሪሜዬር ሊግ ውድድር የገቡ ክለቦችን በገንዘብ እና በሰው ኃይል ለማጠናከር በሲዳማ ከተሞች የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች እየተደረጉ ሲረዱ ለሲዳማ ክ ለ ቦች ግን መሰል ዝግጅቶችን ኣልተደረጉም ። ክለቡ ብቃት ያላቸውን ተጫዋቾች በማስፈረም እና በፋይናስ ኣቅሙን በማጠናከር ውጤታማ ለማድረግ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ስለሌሉ ክለቡ ውጤት ኣልባ ጉዞውን ለመቀጠል ተገዷል ብለዋል። ኣክለውም፤ ክለቡ ያሉበትን የብቃት ችግሮች ኣስተካክሎ በቀጣይ ውድድሮች ማሸነፍ ካልቻለ ከፕሪሜዬር ሊግ ውድድር መውረዱ ስለማይቀር የሚመለከታቸው ኣካላት ክለቡን በሰው እና ፋይናንስ ኃይል የ

Patient satisfaction with outpatient health services in Hawassa University Teaching Hospital, Southern Ethiopia

Image
ለተጨማሪ ንባብ ፦ Full Length Research Paper

Fish Market at Awassa Lake

Image
ተጨማሪ  ፎቶዎችን በዚህ ሊንክ ይመልከቱ፦  Fish Market at Awassa Lake

AWASSA KENEMA VS. KEDUS GIORGIS

Image