Posts

የይርጋለም ከተማ የንጽህ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክት መቼ ይሁን የምጠናቀቀው?

Image
ኣንድ ሚሊዮን ለምጠጉ የ ይርጋለም ከተማ እና ለኣከባቢዋ የገጠር ቀበሌያት ነዋሪዎች ኣገልግሎት ይሰጣል ተብሎ፤ ከ 50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በመገንባት ላይ የሚገኘው የውሃ ፕሮጀክት በተለያዩ ምክንያቶች ከሚጠበቀው በላይ ተጓቷል። ይህ የውሃ ፕሮጀክት 60  ሊትር በሰከንድ ወይም  5  ሺ  142  ሜትር ኪዩብ በቀን የመስጠት አቅም ያለው እና እስከ  2012 ዓ . ም ድረስ ለ 898  ሺ ያህል የከተማዋ ሕዝብ አገልግሎት ለመሥጠት ያስችላል መባሉ ይታወሳል ። እንደ ኣዲስዘመን ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ፤ የውሃ ፕሮጀክት በአንድ ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ቢጠበቅም ከቧንቧ መገጣጠሚያ አካል  ( ፊቲንግ )  አቅርቦት ችግር ጋር ተያይዞ መጓተቱን የሥራ ኃላፊዎች ይናገራሉ፡፡ አምስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ካሉት ፕሮጀክት መካከል ሁለቱ በጄነሬተር ሥራ ቢያስጀምሩም ሌሎቹ ግን ውሃ መስጠት አልቻሉም። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ውሃ መግፋት የሚያስችል በቂ የኃይል አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት ነው።   « ትራንስፎርመር ለማስተከል ክፍያ የፈፀምነው በ 2003  ዓ . ም ቢሆንም እስካሁን ከአንዱ በቀር ምላሽ አልተሰጠንም »  የሚሉት የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች፤ በዚህ ምክንያት ህብረተሰቡ በቂ ውሃ ማግኘት አለመቻሉን ይገልጻሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንድ ትራንስፎርመር ቢተከልም በሶስት ቀን ውስጥ እንደፈነዳና አገልግሎት እንዳቆመ ይናገራሉ፡፡ የፈነዳውን ለማስለወጥ ያደረጉት ጥረት ምላሽ አለማግኘቱን ጨምረው ገልጸዋል፡፡ እንደጋዜጣው ዘገባ፤ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ክልል ቅርንጫፍ የገበያና ሽያጭ ኃላፊ አቶ ታደሰ መርጋ፤ ከፍላጎት መጨመር ጋር ተያይዞ ወረፋ መኖሩን ገልፀው፤  « ፈነዳ »  ስለተባለው ትራንስፎርመር ግን የሚያውቁ

በሃርቤ ጎና ወረዳ በአንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ቀርከሃ ልለማ ነው

Image
ፋብሪካው በሲዳማ ዞን በአንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ  ቀርከሃ ለማልማት ዝግጅት እያደረገ ነው በኢትዮጵያዊ ባለሀብትና በአሜሪካ የልማት ድርጅት ትብብር የተቋቋመው  « አፍሪካን ባንቡ »  የተሰኘው የቀርከሃ ፋብሪካ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቀርከሃ ጣውላ በማምረት ወደ ጀርመንና የተለያዩ የዓለም ሀገራት ለመላክ ማቀዱን አስታወቀ፡፡ የአፍሪካ ባምቡ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ካሊድ ዱሪ የፋብሪካውን በይፋ ስራ መጀመር አሰመልክቶ ከትናንት በስቲያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሲዳማ ዞን አርቤጎና ወረዳ ውስጥ በ 250  ሚሊዮን ብር የተገነባው ይኸው የቀርከሃ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በየአመቱ  140  ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ ለማስገባት አቅዷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከምርቱ  52  በመቶውን ወደ ጀርመን ለመላክ ስምምነት ፈጽሟል፡፡ « በሀገሪቱ የደን ሽፋን ካለፉት  40  አመታት ወዲህ እየተመናመነ በመምጣቱ የእንጨት ጥሬ እቃ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ አጋጥሟል »  ያሉት ስራ አስኪያጁ፣ በየአራት ዓመቱ ራሱን በሚተካው ቀርከሃ ይህን የጥሬ ዕቃ አቅርቦቱን በመሸፈን ከቀርከሃ ጣውላ እንደሚመረት ነው ያስታወቁት። ከሀገሪቱ የደን ሽፋን ከ 50 በመቶ በላይ የሚሆነው ቀርከሃ መሆኑንም አስታውቀዋል። እንደ ስራ አስኪያጁ ገለጻ፤ የፋብሪካው ዋነኛ ጥሬ ዕቃ የሆነውን ቀርከሃ በሲዳማ ዞን አርቤ ጎና ወረዳ በአንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ለማልማት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በአሁኑ ወቅትም 50  ሺ ችግኞችን በማፍላት ለአርሶ አደሮች እየተከፋፈለ ይገኛል። በየአመቱም አርሶ አደሮቹ የሚያመረቱትን ቀርከሃ ከ 30  ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ እየገዛ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡አርሶ አደሮ

ጥቂት ስለ Ajuuja Children’s Home እና The FIG program (Family In the Gap)

Image
Ajuuja Children Home Association Profile Ajuuja Children Home Association (ACHA) established with the initiative of  seven  people who have a keen interest to help and mobilize children’s peers toward the protection of their basic needs as stipulated in international convention from SNNPR Bureau of Justice in September 2008 in Hawassa as local NGOs. But after the charities and societies legislation takes place at federal level in Ethiopia, the Association registered as local CSOs with the registration number 1493 on February 2010 from the Federal Democratic Republic of Ethiopia. Ajuuja Children Home Association (ACHA) established with the initiative of  seven  people who have a keen interest to help and mobilize children’s peers toward the protection of their basic needs as stipulated in international convention from SNNPR Bureau of Justice in September 2008 in Hawassa as local NGOs. Vision To see orphans and vulnerable children’s problems are solved and, to see soc

2014 EVERY ONE Campaign Race in Hawassa is set to take place on Sunday 11 May 2014

Image
EVERY ONE Campaign Race in Hawassa More than 7000 participants including more than hundred runners from overseas and around 1500 runners from Addis Ababa took part in the 3rd & 4th editions of the EVERY ONE Campaign Races in Hawassa. In the main half-marathon race for elite athletes, course records were broken in the 4th edition.   Hawassa is situated 275km south of Ethiopia's capital Addis Ababa at an altitude of 1700m. Hawassa is the regional capital of southern Ethiopia. A section of the race course runs alongside Lake Hawassa which is a popular place for birdwatchers. Temperatures in Hawassa in May tend to rise to around 30C in the middle of the day but are at around 10-15C in the early morning and late evening. EVERY ONE: is a campaign to reduce newborn, child and maternal deaths in Ethiopia.                                                Hotel options in Hawassa  Hotels with room price under 300 Birr  Centeral Hotel      Tel. 046 221 4143/8  Atenet Hotel   Te

ሜትሮፖሊቲያን ከተማችንን እንዴት እናስተዳድር በማለት ቀርበው የነበረው የመወያያ ጽሁፍ ከየት ደረሰ?

Image
በህወሃት የምመራው ኢህኣዴግ ስልጣን ላይ መውጣቱን ተከትሎ በክልል ደረጃ ተደራጅቶ የነበረው የሲዳማ ኣስተዳደር በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት በኣቶ መለስ ዜናዊ ኣጭር የጽሁፍ ትዕዛዝ ለማዕከላዊ ኣስተዳደር እንዲመች በምል በደቡብ ኢትዮጵያ ብሄር፤ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መስተዳደር ተብለው በኣንድ ክልል ተጨፍልቀው እንድደራጁ ሲደረግ የሲዳማ ህዝብ ፍቃደኝነት ኣልተጠየቀም። በወቅቱ የሲዳማ ህዝብ የራሱን የክልል ኣስተዳደር ትቶ ከሌሎች ጋር እንድዋሄድ ያለ ህዝቡ ፍላጎት እና ፍቃድ ውሳኔ በኣንድ ግለሰብ ተወስኖበት ከላይ ስወርድ በጊዜው የሲዳማን ክልል ሲያስተዳድር የነበረው የሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ( ሲህዴድ ) ልፍስፍስ ኣመራር ትዕዛዙን ተቀብሎ ከማስፈጸም በስተቀር ለመቃዎም ያደረገው ጥረት ኣልነበረም። ካዛን ጊዜ ጀምሮ የሲዳማ ህዝብ የራሱ የሆነ ክልላዊ ኣስተዳደር እንደምፈልግ እና እንደምገባው በመግለጽ ሰላማዊ ትግል በማድረግ ላይ ሲሆን፤ ገዥው የኢህኣዴግ መንግስት በራሱ ጊዜ ጽፎ ያረቀቀውን ህገ መንግስት በመናድ፤ ህገ መንግስቱ ለብሄር እና ብሄረሰቦች የሰጠውን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በመጣስ፤ ለሲዳማ ክልላዊ ኣስተዳደር መብት የምታገሉትን የሲዳማ ተወላጆችን በግፊ በኣደባባይ በመግደል፤ ሰብኣዊ መብታቸውን በማፈን ያለ ምንም ፍትህ በማሰር፤ ከስራ ገበታቸው ያለምንም ምክንያት በማባረር፤ ከኣገር በማሳደድ፤ በመደብደብ እና በማስቃየት፤ ብሎም የሚቆጣጠሯቸውን የመገናኛ ብዝሃን በመጠቀም የሲዳማን ህዝብ በመስደብ እና በማስፈራራት የክልል ጥያቄ ለማዳፈን ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሆኖም የሲዳማ ህዝብ ለክልል ጥያቄ መመለስ ካለው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ በኣሁኑ ጊዜ ከመቼውም ጊዜ በላይ መክሮ እና ዘክሮ ኣንድ በመሆን ትግ