የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ በወቅታዊ የፖለቲካ ኣካሄዱ ላይ የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ
መግቢያ የሲዳማ ህዝብ የትግል ታሪክ እንደሚያሳየው የሲዳማ ህዝብ እንደማንኛውም ጭቁን ህዝቦች ለነፃነትና ዴሞክራሲ መስፈን ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡ አሁን ለሚታየውም አንፃራዊ መረጋጋት አያለ የህዝብ ልጆች ደማቸውን በማፍሰስና አጥንታቸውን በመከስከስ አኩሪ የታሪክ አሻራ አስቀምጠው አልፈዋል፡፡ ምንም እንኳን የተከፈለው መስዋዕትነት ከፍተኛ ቢሆንም የሲዳማ ህዝብ እስከ አሁን ድረስ የተሰዋለትን ነፃነት ፣ ሰላምና ዴሞክራሲ ብሎም አስተዳደራዊ ነፃነት እንደተነጠቀ ዘመናትን አስቆጠረዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላላፈው የነፃነት ትግልም እስከ አሁን ድረስ የቀድሞውን ቁልፍ የህዝብ ጥያቄዎችን በማንገብ የሚነሳውን የአሁኑን ትውልድ ደም እያፈሰሰ፣ የሕይወት ዋጋም እያስከፈለ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጠናክሮ ቀጥለዋል፡፡ ስለዚህ የሚያባሪር ካልቆሜ የሚሸሽ ስለማይቆምም (shorrannohu uurrikkinni xooqannohu diuurranno) እንደምባለው የህዝብን ታሪካዊ አደራ ከዳር ለማድረስና ሰላማዊ ትግል ለማቀጣጠል በየደረጃው የሚገኙ የሲአን አመራርና መላው የሲዳማ ህዝብ ብሎም የትግሉ ደጋፊ የሆኑ የሌላ ብሔር አባላት ከምን ጊዜውም በላይ መጠናከር ወሳኝ ጉዳይ ከመሆኑም ባሻገር የሲአን ከፍተኛ አመራርም የድርጅቱን አላማ አንግቦ ይበልጥ ወደ ህዝብ መድረስ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን አንገብጋቢ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ ክፍል አንድ የትግል ማጠናከሪያ አንኳር ዘዴዎች፡ 1. የውስጥ አደረጃጀት ማጠናከር፣ ከሌሎች ትክክለኛና ተቀራራቢ የትግል ዓላማ ካላቸው ተቃዋም ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመተዳደሪያችን ደንብና ፖለቲካ ፕሮግራማችን መሠረት በጋራ መስራት ይገኝበታል፡፡ የውስጥ አደረጃጀትን ማጠናከር አብዘኛው የዓለም ታሪክ እንደሚያ