Posts

የኮፒ ፔስት ጉዳይ ወዴት እየወሰደን ይሆን?..............እንዳለ ደበላ ሀዋሳ ኢዜአ

ዘወትር ከሚቀመጡባት የዛፍ ጥላ ስር ዛሬም እንደወትሯቸው ተቀምጠዋል። በተለመደው ሁኔታ ከፊት ለፊታቸው ካለች ሰባራ የእንጨት ባለመደገፊያ ወንበር ላይ የተቀመጡ ደምበኛቸው የመጡበትን ሁኔታ እየገለጹላቸው ነው።  እርጅናና ኑሮ ያጎሳቆለው እጃቸው ቢንቀጠቀጥም እንደወትሮ አስኪሪፕቶ ጨብጦ ከባለጉዳያቸው የሚነገራቸውን ዋና ዋና ሀሳብ በያዟት እንደርሳቸው እድሜ የተጎሳቆለች የምትመስል ማስታወሻ ቢጤ ደብተር ላይ ጫር ጫር ያደርጋሉ።  እንግዳቸው የመጡበትን ጉዳይ አስረድተው እንደጨረሱ ሻምበል ቢተው በተለመደ ሁኔታ በመካከሉ ካርቦን የገባበት የታጠፈ ወረቀት አውጥተው መጻፍ ጀመሩ።  የመጀመሪያውን ጨርሰው ሌላ ሁለተኛ ካርቦን በመካከሉ የገባበት ወረቅት አውጥተው ያለ ምንም የሀሳብ መቆራረጥ በሚንቀጠቀጥ እጃቸው በማስታወሻ ላይ የጫሩትን ሀሳብ መልከት እያደረጉ የቃላት ዝናብ በወረቀቱ ላይ ያዘንቡ ጀመር።  እንደጨረሱ የጻፏቸውን ሁለት ገጽ ወረቀቶች በየተራ አንብበው እንደጨረሱ ለደንበኛቸው አስፈረሙበትና ቴምብር ለጥፈው በክላሰር በማድረግ ሰጧቸው።  ለዚህ አገልግሎታቸው ከደንበኛቸው የክላሰሩንና የቴምብሩን ዋጋ ሳይጨምር የተቀበሉት 20 ብር ብቻ ነው።  ዛሬ ዘመናዊው አለም በፈጠራቸው የጽሁፍ ማሽኖች ሳቢያ የምንጽፋቸው ጽሁፎች ለራሳችንም የማይገቡና ግራ የሚያጋቡ እየሆኑና በኮፒ ፔስት የተሞሉ ጽሁፎች ተበራከተው በመጡበት ወቅት ራፖር ጸሀፊው ሻምበል ያለምንም መመሳሰልና ኮፒ ፔስት የባለጉዳዮቻቸውን ሀሳብ አዳምጠው ያለምንም የሀሳብ መቆራረጥ ለሁሉም በሚገባ መልኩ ያለማቋረጥ ይጽፋሉ።  የደረስንበት የቴክኖሎጂ አለም ስራችንን ቀልጣፋና በአጭር ጊዜ እንድናከናውን የረዳን ቢሆኑም ኢንተርኔትና ፌስ ቡክ አድራጊና ፈጣሪ በመሆን ከአዕምሯችን አፍልቀን እንዳንጽፍ እን

የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) ብሄራዊ የፖለቲካ ፓርቲ የሆነውን መድረክን "Forum for Democratic Dialogue in Ethiopia" ልቀላቀል መሆኑ ተሰማ

Image
የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ በጠራው ጉባኤ በድርጅቱ የወደፊት የትግል ኣካሄድ ላይ በመወያየት ወሳኔዎች ኣሳልፏል። ቅዳሜ ቀን በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ድርጅቱ እስከኣሁን ድረስ የተከተለውን የትግል ስልት የገመገመ ሲሆን፤ ይከተለው የነበረው የተናጠል የትግል ስልት ፖለቲካዊ ግቦቹን ለማሳካት እንዳላስቻለው ኣመልክቷል። በመሆኑም በችግሮቹ መፍትሄ ላይ በስፋት በመምከር፤ ለተሳካ የፖለቲካ ትግል ከሌሎች መሰል ብሄራዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመታገል ወስኗል። በውሳኔው መሰረት በኣሁኑ ጊዜ በብሄራዊ ደረጃ በመንቀሳቀስ ላይ ካሉት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል Forum for Democratic Dialogue in Ethiopia - Medrek '' መድረክን '' በመምረጥ መድረክን በመቀላቀል በጋር ለመስራት መወሰኑን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ ዘግቧል። ክቡራን ኣንባቢያ በሲኣን ውሳኔ ላይ ያላችሁን ኣስተያየት በምከተለው ኣድራሻ ላኩልን: nomnanoto@gmail.com ጥቂት ስለ መድረክ፦ Medrek  (officially the "Forum for Democratic Dialogue in Ethiopia") is an  Ethiopian  opposition political coalition founded in 2008 which contested the  Ethiopian general election, 2010 . In thatelection, Medrek won a single seat in the  Council of People's Representatives , representing an electoral district in  Addis Ababa . [1]  This was allegedly d

የሙሲና ነገር በኢትዮጵያ!

Image
Petty Corruption Rife in Ethiopia Although the latest survey suggested that petty corruption is common, grand corruption is not an issue Ameha Diana, director general of Selam Development Consultants Plc, left, and Wedo Atto, the deputy Commissioner of FEACC during the presentation on Thursday, January 23, 2014. The first draft of the World Bank sponsored corruption study comes out pointing fingers at petty corruption in various government institutions, while playing down the impact of grand corruption. The power, tax, investment and transport sectors have been identified as having the highest level of corruption, according to a draft finding by a study under the Federal Ethics & Anti-Corruption Commission (FEACC). Employees of the Ethiopian Electric Power Corporation (EEPCo) have been identified by the study as being frontrunners in asking for unofficial payments, with an average of 10 bribe requests for a single respondent in the study. The EEPCo is als

“የግንቦት 20 ፍሬን የምንለካው ኢህአዴግ በሰላማዊ መንገድ ከሥልጣን ሲወርድ ነው”

Image
ጭቆና ትግልን ያጠነክራል እንጂ አይገድልም... ኢህአዴግን በምርጫ ለማሸነፍ የአንድ ወር ሥራ በቂ ነው…. ኢህአዴግ ሁልጊዜ የትግራይ ህዝብ በስጋት እንዲኖር ነው የሚፈልገው  በቅርቡ ለፓርቲዎች የውህደት ጥያቄ አቅርባችኋል፡፡ ለየትኞቹ ፓርቲዎች ነው ጥያቄውን ያቀረባችሁት? መስፈርታችሁስ ምን ነበር? እኛ እንግዲህ ያሰብነው በመድረክ ውስጥ ካሉት ፓርቲዎች ጋር ውህደት ለመፈፀም ነው፡፡ ግን ከመድረክ ውጪም ቢመጣ ችግር የለብንም፡፡ እንግዲህ በጠየቅናቸው ፓርቲዎች ሙሉ ፈቃደኝነት በቅርቡ ከግንባር ወደ ውህደት እንሄዳለን የሚል እምነት ነው ያለኝ። ጥያቄውን ለኦፌኮ፣ ለአንድነት እና ለደቡብ ህብረቶች አቅርበናል፡፡ እነሱም በጐ ምላሽ እየሰጡን ነው፡፡ ውህደት የተጠየቁት ፓርቲዎች የመድረክ አባል ከሆኑ ለምን ራሱን መድረክን አልጠየቃችሁም? ፓርቲዎቹን በተናጠል መጠየቅ ለምን አስፈለገ? ሁለት አቅጣጫ ነው ያለው፡፡ እንዳልከው በቀጥታ መድረክንም መጠየቅ ይቻል ነበር፤ ግን በተናጠል የመጠየቁን መንገድ ነው የመረጥነው፡፡ ይሄን ጥያቄ ያነሳሁት “አረና በመድረክ ላይ እምነት የለውም” የሚሉ አስተያየቶች ስለሚሰነዘሩ ነው… በተናጠል መጠየቁን በመድረክ ህልውና ካለማመን የመጣ ነው የሚሉ ወገኖችም አሉ… እኛ እኮ ሁሉንም ነው የጠየቅነው፡፡ ነጥለን የተውነው ፓርቲ ቢኖር ሊያስብል ይችላል፡፡ ግን የጠየቅናቸው በአጠቃላይ በመድረክ ውስጥ ያሉትን ነው:- አረና፣ ኦፌኮ፣ አንድነት እና የደቡብ ህብረት፡፡ አረና ተነሳሽነቱን ወስዶ ነው የእንዋሃድ ጥያቄውን ያቀረበው፡፡ ስለዚህ መድረኩን አይፈልጉትም የሚያስብል ሁኔታ አይፈጥርም፡፡ ይሄኛውን መንገድ መምረጣችን ብዙም ችግር አለው ብዬ አላስብም፡፡ ለውህደቱ ጥያቄ መነሻችሁ ምንድን ነው? እንዴትስ ይሄኛውን ጊዜ መረጣችሁ? ምናልባት ምርጫው

ሂውማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ይበልጥ ጠቧል አለ

Image
መንግስት፤ ተቋሙ የተቃዋሚዎች የፕሮፖጋንዳ ማስፈፀሚያ ነው “በኢትዮጵያ የነፃ ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ ነው” “በኤርትራ የመብት ጥያቄ ማንሳት ነውር ሆኗል” ብሏል የኢትዮጵያ መንግስት የዜጐችን  ሰብአዊ መብት በስፋት ይጥሳል በማለት ተደጋጋሚ ወቀሳና ስሞታ የሚያቀርበው ሂውማን ራይትስ ዎች የተሰኘው አለማቀፍ የመብት ተቋም፤  ሰሞኑን ይፋ ባደረገው አመታዊ ሪፖርቱ፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ነፃነት ይበልጥ መጥበቡንና የነጻ ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ፤ የተቋሙን ሪፖርት ያጣጥላል፡፡ በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ነፃነትና የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማካሄድ እድል (የፖለቲካ ምህዳር) እየጠበበ የመጣው ከምርጫ 97 በኋላ መሆኑን የገለፀው ሂውማን ራይትስ ዎች፤ ከዚያ ወዲህ በመንግስት የፀደቁትን የፀረ - ሽብር እና የበጐ አድራጐት ማህበራት አዋጆችን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡ በፀረ - ሽብር አዋጁ መነሻነት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ሽብርተኛ ተብለው እንደታሠሩና እንደተፈረደባቸው የተቋሙ ሪፖርት ጠቅሶ፣ በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፍርሃት እንዲሸበቡ ተደርገዋል ብሏል፡፡  ጋዜጠኞች የፀረ-ሽብር አዋጁን በመፍራት የሙያ ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ መታፈናቸውን ሲገልጽም፤ የአዋጁ አንቀፅ እየተጠቀሰ እሥራት የተፈረደባቸው ጋዜጠኞች መኖራቸውንም አውስቷል፡፡ በኢትዮጵያ ጐልተው የሚታዩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የፖለቲካ ምህዳር መጥበብና የኘሬሶች አፈና ቢሆኑም፤ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም መሻሻል አላሣዩም ብሏል ሪፖርቱ፡፡  በማረሚያ ቤት ያሉ እሥረኞች በገለልተኛ አካላት እንዳይጐበኙ መከልከል፣ ያልተፈረደባቸው ግለሰቦችን አስሮ ማቆየትና ለፍርድ ቤት አቤቱታ እንዳይቀርቡ ማገድ፤ ያልተፈረደባቸውን ሰዎች በብሔራዊ ቴሌቪዥን