የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) ብሄራዊ የፖለቲካ ፓርቲ የሆነውን መድረክን "Forum for Democratic Dialogue in Ethiopia" ልቀላቀል መሆኑ ተሰማ
የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ በጠራው ጉባኤ በድርጅቱ የወደፊት የትግል ኣካሄድ ላይ በመወያየት ወሳኔዎች ኣሳልፏል። ቅዳሜ ቀን በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ድርጅቱ እስከኣሁን ድረስ የተከተለውን የትግል ስልት የገመገመ ሲሆን፤ ይከተለው የነበረው የተናጠል የትግል ስልት ፖለቲካዊ ግቦቹን ለማሳካት እንዳላስቻለው ኣመልክቷል። በመሆኑም በችግሮቹ መፍትሄ ላይ በስፋት በመምከር፤ ለተሳካ የፖለቲካ ትግል ከሌሎች መሰል ብሄራዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመታገል ወስኗል። በውሳኔው መሰረት በኣሁኑ ጊዜ በብሄራዊ ደረጃ በመንቀሳቀስ ላይ ካሉት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል Forum for Democratic Dialogue in Ethiopia - Medrek '' መድረክን '' በመምረጥ መድረክን በመቀላቀል በጋር ለመስራት መወሰኑን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ ዘግቧል። ክቡራን ኣንባቢያ በሲኣን ውሳኔ ላይ ያላችሁን ኣስተያየት በምከተለው ኣድራሻ ላኩልን: nomnanoto@gmail.com ጥቂት ስለ መድረክ፦ Medrek (officially the "Forum for Democratic Dialogue in Ethiopia") is an Ethiopian opposition political coalition founded in 2008 which contested the Ethiopian general election, 2010 . In thatelection, Medrek won a single seat in the Council of People's Representatives , representing an electoral district in Addis Ababa . [1] This was allegedly d