ሲዳማ እና የጫት ምርቷ
በሪፖርተራችን በጥቻ ወራና የቀረበ የሲዳማ ጫት ገበያ እንደተለመደው ዘንድሮም ሞቅ ያለ ነው። እንደምታወቀው በተለይ በበጋ ወራት የጫት ገበያው ሞቅታ ከፍተኛ ይሆናል ምክንያቱ በበጋ ወራት የጫት ምርት ኣነስተኛ ስለምሆን ነው። በተቃራኒው በክረምት የጫት ምርት ከፍተኛ ስለምሆን እና ኣብዛኛዎቹ የጫት ኣምራቾች ምርታቸውን በገፍ ይዘው ወደ ገበያ ስለሚወጡ የጫት ዋጋ ይቀንሳል። የሲዳማ ጫት ምርት በመላው ኣገሪቷ ተፋላጊነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ የተነሳ የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮች ሌሎች ለምግብነት የምሆኑ የእርሻ ምርቶችን ማምረት ትተው ማሳቸውን በጫት በመሸፈን ላይ ናቸው። በኣሁኑ ጊዜ በሲዳማ ውስጥ 60 ከመቶ የምሆነው መሬት በጫት በመያዝ ላይ ነው ብባል ውሽት ኣይደለም፤ ምክንያቱም ኣነሰም በዛም በ 21 ዱም የሲዳማ ወረዳዎች ውስጥ ጫት ይመረታልና። በጣም የምገርመው ከዚህ በፊት በቡና ምርቱ ይታወቅ የነበረው የኣለታ ጩኮ ወረዳ በኣሁኑ ጊዜ በኣብዛኛው የእርሻ መሬት የጫት የተያዘ ነው። በሲዳማ ውስጥ ባሉት ከዚህ በፊት ጫት በማይመረትባቸው ኣሮሬሳን የመሳሰሉ ወረዳዎችን ጨምሮ በሁሉም ወረዳዎች ጫት በመረቱ ከጫት የምገኘው ገቢ ከሌላው የእርሻ ምርት ከምገኘው ገቢ በላይ በመሆኑ በመሆኑን መገመት ኣያስቸግርም። ለዚህም ይመሰላል ሲዳማ ውስጥ የቡና ተክል እየቆረጡ ጫት እየተከሉ ያሉ ኣርሳ ኣደሮች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱ። ሲዳማ ለምግብነት የሚሆን ምርት ማምረት ኣለበት ወይስ ካሽ ክሮፕ ወይም የተሻለ ገቢ የሚያስገኙ እንደጫት ኣይነት ምርቶችን ማምረት ኣለበት በምለው ዙሪያ ብዙ ኣከራካሪ ጉዳዮች ልኖሩ ይችላሉ፤ ከዚህም ባሻገር ሰው በገዛ ማሳው የሚያዋጣውን ምርት የማምረት መብት ሰላሌው ክርክር ውስጥ ኣንገባም። ሲዳማ