በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ማህበራት የተደራጁ የሲዳማ ወጣቶች የመንግስት ትኩረት እንደምያሹ መግለጻቸውን ተከትሎ የዞኑ መንግስት ለማህበራቱ የገበያ ትስስር መፈጠሩን ኣስታወቀ
ከሶስት ሳምንታት በፊት የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ዘጋብ ሪፖርተር ጥቻ ወራና '' በተለያዩ የሲዳማ ከተሞች በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ማህበራት ተደራጅተው ያሉ የሲዳማ ወጣቶች የመንግስት ትኩረት ያሻቸዋል ተባለ '' በምል ሃዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ዞን ባሉ በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ማህበራት የተደራጁ ወጣቶችን የስራ እንቅስቃሴ የምቃኝ ዘገባ ማቅረቡን ተከትሎ የዞን መንግስት ለወጣቶቹ የገበያ ትስስር ስራ መስራቱን በመናገር ላይ ነው። ሪፖርተራችን ያናገራቸው በጥቃቅን እና ኣነስተኛ የልማት ስራዎች የተደራጁ ወጣቶች ዘላቂነት ያለው የሙያ ስልጠና የማግኘት እና ለምርቶቻቸው ደግሞ ገበያ የማፈላለግ ችግሮች እንዳሉባቸው የጠቆሙ ሲሆን፤ የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ በበኩሉ ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር መፈጠሩን ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና ኣገልግሎት በሰጠው መረጃ ኣመልክቷል። ሁለቱንም ዘጋባዎች ኣያይዘን ኣቅርበናል ከታች ያንቡ፦ አዋሳ ጥር 14/2006 በሲዳማ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት ተደራጅተው በጥቃቅንና አነስተኛ የልማት ስራዎች ለተሰማሩ አንቀሳቃሾች ከ85 ሚልዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር መፈጠሩን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ፡፡ በመምሪያው የኢንተርፕራይዞች ልማት የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ደበበ ተገኝ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የገበያ ትስስሩ የተፈጠረው ከ11ሺህ በላይ ለሚሆኑ አንቀሳቃሾች ነው፡፡ በዞኑ ሁለት የከተማ አስተዳደሮችና 19 ወረዳዎች ለሚገኙት ለእነዚሁ አንቀሳቃሾች ምርትና አገልግሎታቸውን ለገበያ የሚያቀርቡበት ሁኔታ በማመቻቸት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በዞኑ ባለፉት 6 ወራት ከ11ሺህ በላይ ሰዎች ተደራጅተው በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድና የስራ ዘ