Posts

Natural Attraction in Sidama

Image
Tourism Natural Attraction in Sidama The magnificent natural scenery & hot spring water in the Sidama zone include:   Wondo Genet, Burqito Gidabo, etc.     Like wise the zone is blessed with spectacular water falls; Logita Fall Sidama 120km from Hawassa with torrential sound and Bonora Fall Sidama 135km from Hawassa cataract & blue winged birds There are two areas proposed as protected wildlife reserve that are now being delimited. Garamba   Mountain   is the highest point in the zone. It is located at a distance of 363 km from   Addis Ababa , 84 km distance from Hawassa, and also only 14 km away from Yaye (District main town). The height of the mountain is between 2800m and 3360m. The mountain is surrounded by bamboo forest; and it is convenient for tourists who have mountain trekking hobby. The mountain is home for various wildlife and bird species. There is an attractive topography round the foot of the mountain. One can watch   Bale   Mountai

በሀዋሳ ከተማ አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ በእሳት በመያያዙ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

Image
አዋሳ ጥር 12/2006 በሀዋሳ ከተማ ከትናንት በስቲያ ምሽት አንድ የነዳጅ መጫኛ ቦቴ ባልታወቀ ምክንያት በእሳት በመያያዙ ተሽከርካሪውና ነዳጁ መውደማቸዉን  የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዳንኤል ገዛኽኝ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በእለቱ ከምሽቱ  አንድ ሰዓት ገደማ ላይ አደጋዉ የደረሰዉ ቦቴዉ የጫነዉን ነዳጅ በኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ዉስጥ በማራገፍ ላይ እንዳለ በተነሳዉ ድንገተኛ እሳት ነዉ  ። የነዳጅ መጫኛ ቦቴዉ  በእሳት በመያያዙ ሾፌሩ በፍጥነት መኪናውን ከነዳጅ ማደያው በማውጣትና ወደ ዋናው መንገድ ላይ ወስዶ በማቆም እሳቱ ወደ  እንዳይዛመት በማድረግ ሊደርስ ይችል የነበረዉን አደጋ መከላከል መቻሉን አስታዉቀዋል ። አሽከርካሪውን በፍጥነት ከማደያዉ አካባቢው በማራቁም  በአቅራቢያ  በሚገኙ ሁለት ሌሎች የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ላይ ሊደርስ የሚችለዉን  አደጋ መከላከል መቻሉን  ተናግረዋል ። እሳቱን ለማጥፋት የከተማው ነዋሪዎችና የፖሊስ አባላት ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸዉንና በንብረት ውጪ በሰው ህይወት  ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ዋና ኢንስፔክተሩ ጠቁመው የአደጋው መንስኤና የደረሰው ውድመት እየተጣራ ነዉ ብለዋል ። የነዳጅ ቦቴው በውስጡ ባሉት አራት ክፍሎች  በአጠቃላይ እስከ 600 ሺህ ሊትር ነዳጅ የመያዝ አቅም እንዳለው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸዉ ባለሙያዎች ጠቁመዋል ።

በሲዳማ ዞን ከ13ሺህ በላይ ላሞችና ጊደሮችን የማዳቀል ስራ ተከናውኗል

Image
አዋሳ ጥር 12/2006 በሲዳማ ዞን ባለፉት 6 ወራት ከ13ሺህ በላይ ላሞችና ጊደሮችን የውጭ ዝርያ ካላቸው ኮርማዎችና በሰው ሰራሽ ዘዴ የማዳቀል ስራ መከናወኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ ፡፡ የማዳቀሉ ስራ የተከናወነው በሸበዲኖ፣በአለታ ጩኮ፣ በአለታ ወንዶና በዳሌ ወረዳዎች ሲሆን በቀጣይም በቀሪ የዞኑ ሁሉም ወረዳዎች በተመሳሳይ ለማካሄድ ዝግጅት መጠናቀቁም ተመልክቷል፡፡ በመምሪያ   የግብርና ልማት እቅድ፣ ዝግጅት፣ ክትትልና ግብረ መልስ የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ ደርቤ በትራ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት እንስሳቱን ማዳቀል ያስፈለገው  የወተትና የስጋ  ምርትና ምርታማነታቸውን በማሻሻል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማጎልበት ነው፡፡ በዚህም አንዲት የአካባቢው ዝርያ ያላት ላም በቀን የምትሰጠውን ከሁለት እስከ ሶስት ሊትር ያልበለጠ የወተት ምርት ከሶስት እጥፍ በላይ ማሳደግ ያስችላል፡፡ በየወረዳዎቹ የሚገኙ አርሶ አደሮችን በአንድ ለአምስትና በልማት ቡድኖች በማቀናጀት በየደረጃው በሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች አማካኝነት የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠቱን የገለጹት ኦፊሰሩ የእንስሳት ዝርያ የማሻሻሉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ቀደም ብሎ በኮርማና በሰው ሰራሽ ዘዴ የተዳቀሉ ከ6ሺህ በላይ ጥጆች መወለዳቸውንም ተናግረዋል፡፡ በዚህም  ባለፉት ስድስት ወራት የወተት ምርትና ምርታማነትን በማሻሻል 66ሺህ 890 ቶን ወተት በማምረትና ለገበያ በማቅረብ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡ በዞኑ ሰፊ የእንስሳት ሃብት ቢኖርም በተለይ የወተትና ወተት ተዋፅኦ ምርት ዝቅተኛ በመሆኑ ይህንን ለማሻሻል በሁሉም የዞኑ ወረዳዎች የዝርያ ማሻሻሉ ስራ ለማስፋፋት መዘጋጀታቸውን የስራ ሂደቱ ኦፊሰር አመልክተዋል፡፡

ጃፓን ለኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ጠንካራ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት መካከል በ3ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች-አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ

አዲስ አበባ ጥር 9/2006 ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው የተለያዩ የልማት ስራዎች ጠንካራ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት መካከል ጃፓን በ3ኛ ደረጃ ላይ እንድምትገኝ በጃፓን የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አስታወቁ። የሁለቱ አገራት አመታዊ የኢኮኖሚና የንግድ ግንኙነት 153 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃል ምልልስ እንዳሉት ጃፓን በኢትዮጵያ በሚካሄዱ የልማት ስራዎች ውስጥ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ረገድ ከአሜሪካና ቻይና በቀጠል በሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። የኢትዮ-ጃፓን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተጀመረ 80 አመታት ማስቆጠሩን የጠቆሙት አምባሳደሩ ግንኙነቱ በጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተና በጽኑ መሰረት ላይ እየተገነባ መምጣቱን ጠቁመዋል። የአገሮቹ ግንኙነት በማህበራዊ መስኮች በተለይም በባህልና በህዝብ ለህዝብና ትብብሮች ረገድም በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አምባሳደሩ ተናግረዋል። አምባሳደር ማርቆስ በአሁኑ ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ያለው አመታዊ የኢኮኖሚና የንግድ ግንኙነት 153 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ጠቁመዋል። የጃፓን ባለሃብቶች  በኢትዮጵያ መዋእለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ረገድ ከሌሎች አገራት አንጻር ሲታይ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አምባሳደር ማርቆስ ገልጸዋል። ባለሃብቶቹ በማእድን ልማት፤በንግድ፣በኮንስትራክሽንና በሌሎችም ዘርፎች በሰፊው የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል። 0፡40 የጃፓን መንግስት በሰው ሃይል ልማት፣በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድም ለኢትዮጵያ በተግባር የታገዘ ስልጠና ለመስጠት ተጨባጭ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አብራርተዋል። ለአብነትም በመጪው ሚያዝያ ወር 150 ኢትዮጵውያን  ወደ ጃፓን በመሄድ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ስልጠና

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ራሳቸውን ከፖለቲካ አገለሉ

‹‹የሕዝብ መብት ከሚቃወም የፖለቲካ ድርጅት ጋር መሥራት አስቸጋሪ ነው››   ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹የአንድነትን አቋም ሳያውቁ የፓርቲው አባል ሆነዋል ለማለት ያስቸግራል›› m  አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር የነበሩትና ለ45 ዓመታት በፖለቲካ ውስጥ እንደቆዩ የሚናገሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ከጥር 8 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ከማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከፖለቲካው ዓለም ለመሰናበት የወሰኑት አንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ስላልተመቻቸው ለብሔራዊ ምክር ቤቱ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ምላሽ ባለማግኘታቸው መሆኑን በተለይ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡  ዶ/ር ነጋሶ እንደገለጹት፣ መድረክ ግንባር ከመሆኑ አስቀድሞ ባነሳቸው ሐሳቦች ላይ ሁሉም ድርጅቶች ጠቅላላ ጉባዔ በማድረግ ከተወያዩባቸው በኋላ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ መስማማታቸውንም ለመድረክ በመግለጽ መድረክ ወደ ግንባር መሸጋገሩን አስታውሰዋል፡፡  በሚያዝያ ወር 2005 ዓ.ም. በአንድነት ፓርቲና በእሳቸው የአመለካከት፣ የአቋምና የአቅጣጫ ልዩነት መፈጠሩን የገለጹት ዶ/ር ነጋሶ፣ አንድነት ፓርቲ መድረክ ወደ ግንባር የተቀየረው በጠቅላላ ጉባዔውና በብሔራዊ ምክር ቤቱ እምነትና ውሳኔ ሳይሆን በአመራሮች መሆኑን በመጥቀስ፣ እንደማይስማማ በዚያን ወቅት ባደረገው ግምግማ ላይ በመግለጹ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡  መድረክ ወደ ግንባር ከመቀየሩ አስቀድሞ ይፋ ባደረገው ፕሮግራም ላይ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ተወያይተውና ተመካክረው በሕገ መንግሥት ጉዳይ፣ በቤት ጥያቄና በሌሎችም በተነሱ ነጥቦች ላይ መስማማታቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ነጋሶ፣ በሕገ መንግሥቱ አ