Posts

ጃፓን ለኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ጠንካራ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት መካከል በ3ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች-አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ

አዲስ አበባ ጥር 9/2006 ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው የተለያዩ የልማት ስራዎች ጠንካራ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት መካከል ጃፓን በ3ኛ ደረጃ ላይ እንድምትገኝ በጃፓን የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አስታወቁ። የሁለቱ አገራት አመታዊ የኢኮኖሚና የንግድ ግንኙነት 153 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃል ምልልስ እንዳሉት ጃፓን በኢትዮጵያ በሚካሄዱ የልማት ስራዎች ውስጥ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ረገድ ከአሜሪካና ቻይና በቀጠል በሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። የኢትዮ-ጃፓን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተጀመረ 80 አመታት ማስቆጠሩን የጠቆሙት አምባሳደሩ ግንኙነቱ በጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተና በጽኑ መሰረት ላይ እየተገነባ መምጣቱን ጠቁመዋል። የአገሮቹ ግንኙነት በማህበራዊ መስኮች በተለይም በባህልና በህዝብ ለህዝብና ትብብሮች ረገድም በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አምባሳደሩ ተናግረዋል። አምባሳደር ማርቆስ በአሁኑ ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ያለው አመታዊ የኢኮኖሚና የንግድ ግንኙነት 153 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ጠቁመዋል። የጃፓን ባለሃብቶች  በኢትዮጵያ መዋእለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ረገድ ከሌሎች አገራት አንጻር ሲታይ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አምባሳደር ማርቆስ ገልጸዋል። ባለሃብቶቹ በማእድን ልማት፤በንግድ፣በኮንስትራክሽንና በሌሎችም ዘርፎች በሰፊው የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል። 0፡40 የጃፓን መንግስት በሰው ሃይል ልማት፣በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድም ለኢትዮጵያ በተግባር የታገዘ ስልጠና ለመስጠት ተጨባጭ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አብራርተዋል። ለአብነትም በመጪው ሚያዝያ ወር 150 ኢትዮጵውያን  ወደ ጃፓን በመሄድ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ስልጠና

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ራሳቸውን ከፖለቲካ አገለሉ

‹‹የሕዝብ መብት ከሚቃወም የፖለቲካ ድርጅት ጋር መሥራት አስቸጋሪ ነው››   ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹የአንድነትን አቋም ሳያውቁ የፓርቲው አባል ሆነዋል ለማለት ያስቸግራል›› m  አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር የነበሩትና ለ45 ዓመታት በፖለቲካ ውስጥ እንደቆዩ የሚናገሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ከጥር 8 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ከማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከፖለቲካው ዓለም ለመሰናበት የወሰኑት አንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ስላልተመቻቸው ለብሔራዊ ምክር ቤቱ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ምላሽ ባለማግኘታቸው መሆኑን በተለይ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡  ዶ/ር ነጋሶ እንደገለጹት፣ መድረክ ግንባር ከመሆኑ አስቀድሞ ባነሳቸው ሐሳቦች ላይ ሁሉም ድርጅቶች ጠቅላላ ጉባዔ በማድረግ ከተወያዩባቸው በኋላ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ መስማማታቸውንም ለመድረክ በመግለጽ መድረክ ወደ ግንባር መሸጋገሩን አስታውሰዋል፡፡  በሚያዝያ ወር 2005 ዓ.ም. በአንድነት ፓርቲና በእሳቸው የአመለካከት፣ የአቋምና የአቅጣጫ ልዩነት መፈጠሩን የገለጹት ዶ/ር ነጋሶ፣ አንድነት ፓርቲ መድረክ ወደ ግንባር የተቀየረው በጠቅላላ ጉባዔውና በብሔራዊ ምክር ቤቱ እምነትና ውሳኔ ሳይሆን በአመራሮች መሆኑን በመጥቀስ፣ እንደማይስማማ በዚያን ወቅት ባደረገው ግምግማ ላይ በመግለጹ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡  መድረክ ወደ ግንባር ከመቀየሩ አስቀድሞ ይፋ ባደረገው ፕሮግራም ላይ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ተወያይተውና ተመካክረው በሕገ መንግሥት ጉዳይ፣ በቤት ጥያቄና በሌሎችም በተነሱ ነጥቦች ላይ መስማማታቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ነጋሶ፣ በሕገ መንግሥቱ አ

ግብፅ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለኢትዮጵያ ብድርና ዕርዳታ እንዳይሰጡ እየተንቀሳቀሰች ነው ተባለ

‹‹ለሱዳን የተሰጠ መሬት የለም››  መንግሥት ዓለም አቀፍ አበዳሪና ለጋሽ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን ብድርና ዕርዳታ እንዲያቆሙ ግብፅ እየተንቀሳቀሰች መሆኗን መንግሥት መረጃ እንዳለው አስታወቀ፡፡  በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው የሦስትዮሽ ድርድር ሦስተኛ ስብሰባ በቅርቡ ያለውጤት ከተበተነ በኋላ፣ በግብፅ በኩል አፍራሽ የሆኑ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡  ባለፈው ዓርብ ረፋድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጽሕፈት ቤታቸው መግለጫ የሰጡት አምባሳደር ዲና፣ በግብፅ በኩል የቀረበውና በኢትዮጵያና በሱዳን ውድቅ የሆነው ሐሳብ፣ እስካሁን ግድቡን አስመልክቶ የተጀመሩ ውይይቶችን ወደኋላ የሚመልስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡  የውጭ ባለሙያዎች ያሉበትና ከሦስቱም አገሮች የተውጣጡ የውኃ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የኤክስፐርቶች ፓነል ለአንድ ዓመት በግድቡ ዙሪያ ጥናት አካሂዶ ባወጡት ሪፖርት፣ ከተወሰኑ ቴክኒካዊ ማስተካከያዎች ውጪ ግድቡ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሟላ መሆኑን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡  የፓነሉ ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ የሚያደርግ ከሦስቱ አገሮች የተውጣጡ የውኃ ባለሙያዎች ያሉበት ኮሚቴ የተቋቋመ መሆኑን፣ ግብፆች አዲስ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ የኮሚቴውን ሥራ በበላይነት እንዲከታተል የሚል ሐሳብ ነው ያቀረቡት፡፡  እንደ አምባሳደር ዲና ገለጻ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞ በዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ፓነል መቋቋም ላይ ሳይሆን፣ ሚናውን በተመለከተ ነው፡፡ በዚህ ልዩነት የተነሳ ያለውጤት ስብሰባው ከተበተነ በኋላ፣ ግብፆች በሚዲያዎቻቸው ‹‹ኢትዮጵያ ለመተባበር እምቢተኛ ሆነች›› እያሉ እያቀረቡ መሆኑንና ከዓለም ባንክ፣ ከአይኤምኤፍና በሌሎች ዓለም አቀፍ

Ethiopia: Hawassa Earned 48 mln. Birr Revenue from Tourism

Hawassa City earned over 48 million birr revenue from tourists who visited attraction in the city in the past six months, The Ethiopian Herald reported. The amount earned in the reported period increased by nine million birr compared to the same period in the pervious year, according to the city's Culture, Tourism and Communication Affairs Department. The department attributed the growth to promotion activities carried out in collaboration with stakeholders, infrastructure developments and making destinations attractive for tourists. Over 93,940 local and foreign tourists visited historic and natural sites during the reported period. Source: The Ethiopian Herald

የደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ 60 አቃቢያነ ህግን በስነምግባር ግድፈት ከስራ አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2006(ኤፍ.ቢ.ሲ.) የደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ 60 አቃቢያነ ህግን በስነምግባር ግድፈት ከስራ አሰናበተ። ቢሮው ሌሎች 211 የሚሆኑትን ከቀላል እስከ ከባድ የሚደርስ እርምጃ ወስዶባቸዋል። በተመሳሳይ የክልሉ ማረሚያ ኮሚሽንም 42 የሰራዊቱ አባላት ላይ ከባድ እርምጃ የወሰደ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 10 የሚሆኑት ሙሉ በሙሉ ከስራቸው የተሰናበቱ ናቸው የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ እድማሱ አንጎ እና የማረሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ አዳነ ዲንጋሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ግለሰቦቹ እርምጃው የተወሰደባቸው ጉቦ በመቀበል፣  ፍትህ በማዛባት፣ በወገናዊነት መስራት እና እስረኞች እንዲያመልጡ ማድረግ የመሳሰሉትን ወንጀሎች ፈፅመው በመገኘታቸው ነው። ከቀበሌ እስከ ክልል ድረስ ነዋሪዎችን ባሳተፈ ሁኔታ የተካሄደው እርምጃ ቀጣይነት የሚኖረው መሆኑንም የስራ ሃላፊዎቹ ተናግረዋል። እርምጃ  ከተወሰደባቸው  ግለሰቦች መካከልም አብዛኛዎቹ  ክስ  ይመሰረትባቸዋል ተብሏል። http://www.fanabc.com/index.php?option=com_content&view=article&id=7153:----60------&catid=102:slide