Posts

በሲዳማ ዞን ከ1ሚሊዮን ለሚበልጡ የቤት እንስሳት ህክምናና ክትባት ሰጠሁ ኣለ

Image
ሃዋሳ ጥር 6/2006 በሲዳማ ዞን  ባለፉት ስድስት ወራት ከ1ሚሊዮን  ለሚበልጡ የቤት እንስሳት የተለያዩ በሽታዎች  መከላከያ ክትባትና ህክምና መሰጠቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ ። በመምሪያው የግብርና ልማት እቅድ ኦፊሰር አቶ ደርቤ በትራ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ያለውን የእንስሳት ሃብት በዘመናዊ መንገድ በማርባት አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ ነው ። አርሶ አደሮቹ ከእንስሳት ሃብቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በጤና አጠባበቅ ረገድ መንግስት በሰጠው ትኩረት ለ692 ሺህ057 እንስሳት የተለያዩ በሽታ መከላከያ ክትባት፣ ለ429ሺህ 586ቱ ደግሞ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን አስታውቀዋል ። ለቤት እንስሳቱ የበሽታ መከላከያ ክትባቱና ህክምናው የተሰጠው የእንስሳት ህክምና ባለሙያዎች ከቦታ ቦታ በመዘዋወርና በእንስሳት ጤና ከላዎች በመገኘት መሆኑን ተናግረዋል ። የህክምና አገልግሎቱ የእንስሳት ሰውነት በማቁሰል ለሞት የሚዳርጉ የጎሮርሳ፣ የጉርብርብ፣የአባጎርባና አባሰንጋ፣ የሰንባ በሽታን ለመቆጣጠር  የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል ፡፡ መምሪያው በዚህ አመት  156 ሺህ 700 የዳልጋ ከብቶች፣ ፍየሎችና በጎች በማድለብና በማሞከት  ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉን አቶ በትራ ተናግረዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/index.php?option=com_k2&view=item&id=856%3A%E1%89%A0%E1%88%B2%E1%8B%B3%E1%88%9B-%E1%8B%9E%E1%8A%95-%E1%8A%A81%E1%88%9A%E1%88%8A%E1%8B%AE%E1%8A%95-%E1%88%88%E1%88%9A%E1%89%A0%E1%88_%E1%8C%A1-%E1%8B%A8%E1%89%A4%

ስታር ባክስ የሲዳማን ቡና በቻይና አስተዋወቀ

Image
በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ የሚገኘው የስታር ባክስ ኬሪ ማዕከል ለቡና መገኛዋ ኢትዮጵያ ክብር የቡና ቀመሳ ሥነ ሥርዓት አካሄደ፡፡ እንደ ዋልታ ዘገባ፣ ስታር ባክስ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የሚያደርገው ጥረት በኢትዮጵያ ኤምባሲ አንድ የሥራ ኃላፊ ምሥጋና ቀርቦለታል፡፡ በቻይና የስታር ባክስ ኩባንያ ባለሥልጣን ስለኢትዮጵያ የተፈጥሮ ቡና ጣዕም መልካምነት በሥነ ሥርዓቱ ላይ መግለጻቸው ታውቋል፡፡ ስታር ባክስ ለዓለም ገበያ ከሚያቀርባቸው የተፈጥሮ ቡናዎች ልዩ ጣዕም ያላቸው የሊሙና የሲዳማ ቡና እንደሚገኙበት ዘገባው አስረድቷል፡፡

Church hopes coffee house will change the lives of Ethiopians

Image
P astor Renault Van Der Riet started a coffee shop, Axum, in Winter Garden to benefit an Ethiopian village of the same name. He hopes to expand the business to further benefit the village. All profits go to the village.   ( George Skene, Orlando Sentinel   /   December   30 , 2013 ) On the walls of the   Winter Garden   coffee shop featuring peppermint bark latte and gingerbread whoopie pie are black-and-white photographs of an impoverished African city and its people. The city and the coffee shop share a name: Axum. Axum Coffee was started three years ago by Mosaic Community Church pastor Renaut van der Riet to improve the lives of the 60,000 residents in Axum, Ethiopia. "The heart of Mosaic is to make real redemptive change, locally and globally. The heart of Axum Coffee is the same thing," said van der Riet, 40, who was born in South Africa. The plan was for the coffee shop's profits to go to his Oakland-based church's missionary work in the African com

ቡናና ወርቅ በወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ ማሽቆለቆል ማሳየታቸው ቀጥሏል

Image
የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከሦስት ዓመታት በፊት ይፋ ሲደረግ፣ ከአምስት ዓመት በኋላ በየዓመቱ ያስገኛል ተብሎ የተጠበቀው ገቢ ከአሥር ቢሊዮን ዶላር በላይ ቢሆንም፣ በየዓመቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ያስገኛሉ ተብለው ከታሰቡት ውስጥ ወቅርና ቡና ከፍተኛ ማሽቆልቆል በማሳየት ሦስተኛ ዓመታቸውን ይዘዋል፡፡ የንግድ ሚኒስቴር የ2006 በጀት ዓመት አምስት ወራት ኤክስፖርት አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያረጋግጠው፣ ካለፈው ዓመት አምስት ወራት ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮው የቡና ኤክስፖርት በገቢም ሆነ በተላከው መጠን ዝቅተኛ ሆኗል፡፡ ባለፈው ዓመት በመጀመሪዎቹ አምስት ወራት ከተላከው ከ81 ሺሕ ቶን በላይ ቡና ከ322.3 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ ዘንድሮ እስከ ታኅሳስ መጨረሻ የተመዘገበው የቡና የወጪ ንግድ ከ59 ሺሕ ቶን ብዙም ፈቅ ያላለ ከመሆኑም በላይ፣ ከ200 ሚሊዮን ዶላር በታች ገቢ የተገኘበት ሆኗል፡፡ በመሆኑም በመጠን የ27 በመቶ ወይም 22 ሺሕ ቶን ቅናሽ ሲመዘገብ፣ በገቢ ደግሞ የ38 በመቶ ወይም የ122.5 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ተመዝግቧል፡፡ በግብርና ምርቶች ዘርፍ ዋና ዋና ከሚባሉት ሸቀጦች መካከል ከቡና ኤክስፖርት መቀነስ ባሻገር በኅዳር ወር የነበረውን አፈጻጸም በማስመልከት  ምክንያቶችን ያቀረበው ንግድ ሚኒስቴር፣ ኅዳር ወር የከረመ ቡና የሚሟጠጥበት ወቅት በመሆኑና የዓለም ገበያ የቡና ዋጋ በተከታታይ በመቀነሱ፣ ለቡና ግብይት መዳከም አስተዋጽኦ አድርገዋል ብሏል፡፡ ከቡና ተጨማሪ ካላፈው ዓመት ተመሳሳይ ወራት አኳያ ዝቅተኛ ገቢ ያስገኙት የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬ፣ የብዕርና የአገዳ እህሎችና ጥጥ በግብርናው ዘርፍ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡  አበባም ከፍተኛ የገቢና የመጠን ቅናሽ ካስመዘገቡት ውስጥ ተመድቧል፡፡   በማዕድን ዘርፍ

ሃዋሳ «እኔን ነው ማየት» ትላለች

Image
ሃዋሳ መሐል ከተማ ከአንዱ ግራር ሥር ቁጭ ብዩ የይርጋ ጨፌ ቡናን እያጣጣምሁ ነው። ሀዋሳ ሞቃት ብትሆንም ከሀይቋና ከከተማዋ ዛፎች የሚወጣው ንፋስ ሙቀቱን እንድትመክት አድር ጓታል። የመንገዶቿ ስፋትና ውበት ከንጽህነዋ ጋር ተደምሮ ዓይንን ይስባል። የመኖሪያ ቤቶችም ሆኑ የንግድ ህንጻዎቿ ውበቷ ልዩ ነው። እየተገነቡና ለግንባታ ቦታ የተከለላቸው ቦታዎች ከተማዋ በእቅድ እየተገነባች መሆኑን ያመለክታሉ። በአጠቃላይ ከተማዋ ወገቧን ይዛ   « እኔን ነው ማየት የምትል ወይዘሪት »   ትመስላለች። ይህን ያየ ምንው ሌሎቹ የአገራችን ከተሞች ከሃዋሳ ቢማሩ ያስብላል። የከተማዋ እንዲህ መሆን ምስጢር ምን ይሆን ብለው እንዲመረምሩም ያደርግዎታል። እኔና ሌሎች የሥራ ጓደኞቼ በሥራ አጋጣሚ ሃዋሳ ሂድን ነበር። ከተማዋን በግር በባጃጅ እየዞርን ከተመለከትን በኋላ የውብቷን ምስጢር ለማወቅ ልባችን ተነሳሳ። ተነሳስተን ብቻ አልተውነውም ስለከተማዋም አጠቃላይ መረጃ የሚሰጠንን ሰው ለማናገር ወሰንን። በሃሳቡም ሁሉም ተስማምቶ የከንቲባው የቅርብ ሰው ቀጠሮ እንዲያሲዝልን ተነጋገርን። ተሳክቶልን ፈቃደኛ ሆኑ። በቀጠሯችን መሰረትም ከከንቲባው ቢሮ ከሥራ ባልደረቦቼ ጋር ተገኘን። የሃዋሳ ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ በፈገግታ ተቀበሉን። እኛም ለተደረገልን ትብብር አመስግነን ስለ ከተማዋ ያሉንን አጠቃላይ ጥያቄዎችን አቀረብን። እሳቸውም   « መረጃ መስጠት አንዱ ሥራዬ ነው። እንኳን ወደ ከተማችን በደህና መጣችሁ »   በማለት አቀባበል አደረጉልን።   « ከፍት ፍቱ ፊቱ »   የሚለው የአገሬ ሰው ወዶ አይደለም። ሁሉም ነገር የሚጀመረው ከፊቱ እንደሆነ ለማመላከት እንጂ። የከንቲባው አቀባበልና መረጃ ቶሎ ለመስጠት ያደረጉት ትብብር ምነው ሌሎቹስ ባለሥልጣኖችም እንደእርሳቸው ቢሆኑ ያስብላ