ሃዋሳ «እኔን ነው ማየት» ትላለች
ሃዋሳ መሐል ከተማ ከአንዱ ግራር ሥር ቁጭ ብዩ የይርጋ ጨፌ ቡናን እያጣጣምሁ ነው። ሀዋሳ ሞቃት ብትሆንም ከሀይቋና ከከተማዋ ዛፎች የሚወጣው ንፋስ ሙቀቱን እንድትመክት አድር ጓታል። የመንገዶቿ ስፋትና ውበት ከንጽህነዋ ጋር ተደምሮ ዓይንን ይስባል። የመኖሪያ ቤቶችም ሆኑ የንግድ ህንጻዎቿ ውበቷ ልዩ ነው። እየተገነቡና ለግንባታ ቦታ የተከለላቸው ቦታዎች ከተማዋ በእቅድ እየተገነባች መሆኑን ያመለክታሉ። በአጠቃላይ ከተማዋ ወገቧን ይዛ « እኔን ነው ማየት የምትል ወይዘሪት » ትመስላለች። ይህን ያየ ምንው ሌሎቹ የአገራችን ከተሞች ከሃዋሳ ቢማሩ ያስብላል። የከተማዋ እንዲህ መሆን ምስጢር ምን ይሆን ብለው እንዲመረምሩም ያደርግዎታል። እኔና ሌሎች የሥራ ጓደኞቼ በሥራ አጋጣሚ ሃዋሳ ሂድን ነበር። ከተማዋን በግር በባጃጅ እየዞርን ከተመለከትን በኋላ የውብቷን ምስጢር ለማወቅ ልባችን ተነሳሳ። ተነሳስተን ብቻ አልተውነውም ስለከተማዋም አጠቃላይ መረጃ የሚሰጠንን ሰው ለማናገር ወሰንን። በሃሳቡም ሁሉም ተስማምቶ የከንቲባው የቅርብ ሰው ቀጠሮ እንዲያሲዝልን ተነጋገርን። ተሳክቶልን ፈቃደኛ ሆኑ። በቀጠሯችን መሰረትም ከከንቲባው ቢሮ ከሥራ ባልደረቦቼ ጋር ተገኘን። የሃዋሳ ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ በፈገግታ ተቀበሉን። እኛም ለተደረገልን ትብብር አመስግነን ስለ ከተማዋ ያሉንን አጠቃላይ ጥያቄዎችን አቀረብን። እሳቸውም « መረጃ መስጠት አንዱ ሥራዬ ነው። እንኳን ወደ ከተማችን በደህና መጣችሁ » በማለት አቀባበል አደረጉልን። « ከፍት ፍቱ ፊቱ » የሚለው የአገሬ ሰው ወዶ አይደለም። ሁሉም ነገር የሚጀመረው ከፊቱ እንደሆነ ለማመላከት እንጂ። የከንቲባው አቀባበልና መረጃ ቶሎ ለመስጠት ያደረጉት ትብብር ምነው ሌሎቹስ ባለሥልጣኖችም እንደእርሳቸው ቢሆኑ ያስብላ