Posts

የኣለምኣቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ መንግስት የሲዳማን ህዝብ ህገ መንግስታዊ መብቶች እንድያከብር እና ለክልላዊ መንግስት ጥያቄ ምላሽ እንድሰጥ ግፊት እንዲያደርግ ከኣንድ ኣመት በፊት የቀረበ ጥሪ ኣጥጋብ ምላሽ ኣላገኘም

የሲዳማ ዳይስፖራ ማህበረሰብ ተወካይ የሆኑት ካላ ቤታና ሆጤሳ ለኣለም ኣቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ካላ ባንኪሙ፤ ለኣውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ካላ ጆሴ ኣማኑኤል ባሮሶ፤ ለኣፍሪካ ህብረት ዋና ጸሃፊ ዲኮ ኢንኮሳዛና ዲላሚን ዙማ እና ለኣሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኮ ሂላሪ ሮዲሃም ክልንተን ደብዳቤ ጽፈዋል። በጻፉትም ደብዳቤ ላይ በሲዳማ ህዝብ ላይ በገዥው መንግስት በመፈጸም ላይ ያሉ የሰብኣዊ መብት ጥስት እንዲቆም፤ የሲዳማ እስረኞች እንድፈቱ እና የሲዳማ ህዝብ ህገ መንግስታዊ ጥያዊ የሆነው የክልል ጥያቄ በኣግባቡ እንዲመለስ ጥሪ ኣቅርበው ነበር። ብዙዎቹ ሲዳማውያን እንደሚያምኑት ከሆነ ጥሪውን ተከትሎ የተገኘው ውጤት የተጠበቀውን ያህል ኣይደለም። ጥሪውን ተከትለው የሲዳማ እስረኞች መካከል ኣንዳንዶቹ ያለ ምንም ምክንያት ከታሰሩበት የተፈቱ ቢሆንም የክልል ጥያቄውን የመሳሰሉ ትላልቅ ህዝባዊ ጥያቄዎች  እስከ ኣሁን ድረሰ ምላሻ ተነፍጎበት ይገኛል። ይባስ ብሎም ሰሞኑን የሃዋሳን ከተማ በፌደራል መንግስት እንዲተዳደር ሁኔታን የሚያመቻች የከተሞች መሬት ኣስተዳደር ኣዋጅ ጸድቋል።  የዛሬ ኣመት የተጻፈውን የድጋፍ ጥር ደብዳቤ ከታች ያንቡ፦   Appeal to:-  Mr. Ban Ki -Moon,  United Nation’s Secretary General,  United Nations, 760 United Nations Plaza  Manhattan, NY 10017, USA  Mr. José Manuel Barroso  President of the European Commission  1049 Brussels, Belgium  Mrs. Inkosazana Dlamini Zuma,  African Union’s Secretary Gene

በተለያዩ የሲዳማ ከተሞች በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ማህበራት ተደራጅተው ያሉ የሲዳማ ወጣቶች የመንግስት ትኩረት ያሻቸዋል ተባለ

Image
በሃዋሳ ከተማ በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ኢንዱስትሪ ስር የታቀፉ የሲዳማ ወጣት ልጆች በቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ መሆናቸውን ሪፖርተራችን ሰሞኑን ከሃዋሳ ከተማ ያጠናቀረው ዘገባ ኣመልክቷል። የሲዳማ ወጣቶች በድንጋይ መፍጨት ስራ፤ በኮብል ስቶን ስራ፤ ቢም እና ፕረካስት ስራ የብረታብረት እና የእንጨት ስራ እና በመሳሰሉት የስራ መስኮች በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ኢንዱስትሪ በማህበር በመደራጀት በመስራት ላይ ሲሆኑ፤ በራሳቸው ማለትም ብቻቸውን ተደራጅተው ካቋቋሙት ማህበራት በተጨማሪ ከሌሎች ብሄር እና ብሄረሰቦች ልጆች ጋር ተደራጅተው በመስራት ላይ መሆናቸው ተሰሞቷል። በሃዋሳ ከተማ ውስጥ ካሉት በተጨማሪ በሁሉም የሲዳማ ከተሞች በመስል መልኩ የማህበራት በመደራጀት በተለያዩ የስራ መስኮች የገንዘብ እና የስልጣና ድጋፎችን ኣግኝተው የራሳቸውን እና የቤተሰቦቻቸውን ኑሮ ለማሻሻል በመጣር ላይ ናቸው። ወጣቶቹ በጥቃቂን እና ኣነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው ስራ መስራታቸው መልካም ሆኖ ሳለ በምሰሩት ስራ ያሳዩት ወጤት ብዙም ኣጥጋብ ኣይደለም። በእርግጥ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የወጡትን ጨምሮ ብዙ የተግባር ስራ ልምድ የሌላቸው ጊዜያቸውን ባልቧለ ቦታ ያሳልፉ የነበሩት ወጣቶች ወደ ስራ ገብተው ውጤታማ መሆን መጀመራቸው የምካድ ባይሆንም፤ እያስመዘጋቡ ያሉትን ውጤት ከሌሎች ክልል ማህበራት የስራ ውጤቶች ጋር ሲወዳደር ልዩነቱ የእትዬ ሌሌ ነው። ከዚህ ባሻገር በስራ ላይ ውጤት በማጣታቸውም የተነሳ እስከ መበተን የደረሱም ኣሉ። እንደ ጥቻ ወራና ዘጋባ ከሆነ በሃዋሳ ከተማ ሲዳማውያን ብቻ ተደራጅተው ካቋቋሟቸው ማህበራት መካከል ሁለቱ በኣያያዝ ችግር የተነሳ ፈርሰው ከዚህ በፊት ለስራ በከታማዋ ማዘጋጃ የተሰጣቸውን የስራ ቦታ ሊ

የገና በዓልና ተያያዥ ኩነቶች

Image
በአገራችን ከሚከበሩ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል ገና አንዱ ነው፡፡ ይህ በዓል በክርስትና አማኞች ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ ነው፡፡ ከፈረንጆቹ ገና በአንድ ሳምንት ዘግይቶ የሚከበረው ይህ ሃይማኖታዊ በዓል፣ በሁሉም የክርስቲያን ቤተ እምነቶች በኩል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ይከበራል፡፡ የቱሪስት መስህብ በሆነው በደብረ ሮሃ ላስታ ላሊበላ ያለው አከባበር ደግሞ ከሁሉም የተለየና የሚማርክ ነው፡፡ በበዓሉ ዋዜማ ካህናቱ በሚያቀርቡት ኅብረ ዜማ ይደምቃል፡፡ ከላሊበላ አቢያተ ክርስቲያናት አንዱ በሆነው በቤተ ማርያምና በዙሪያው ባለው የማሜ ጋራ ዝማሬው በጥንግ ድርብና በጧፍ ታጅቦ ይከበራል፡፡ የሃይማኖት አባቶች እንደሚገልጹት፣ በጋራው ላይ የሚያሸበሽቡት ካህናት የመላዕክት፣ ከጋራው ሥር የሚያሸበሽቡት ካህናት ደግሞ የሰው ልጆች ምሳሌዎች ናቸው፡፡  ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ካህናትና ሰዎች በአንድነት ኢየሱስ ክርስቶስን ያመሰገኑበት ምሳሌ መሆኑ፣ በስፋት ይነገራል፡፡ የገና ባህላዊ በዓልነቱ በአብዛኛው በገጠራማው የአገራችን ክፍል የሚስተዋል ቢሆንም የተወሰኑ የባህሉ ቅሪቶች በአንዳንድ ከተሞችም አይጠፉም፡፡ በዓሉን በባህላዊ ጭፈራ፣ በገና ጨዋታ፣ ባህላዊ ልብስ ለብሶ ማክበር የተለመደ ነው፡፡  ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የሚለው ብሂል እንደሚያስረዳው፣ ሁሉም ወጣት ከቤቱ ወጥቶ በሜዳ ላይ ጨዋታ፣ በደስታና በሃሴት ያከብረዋል፡፡ እንደሌሎች በዓላት ሁሉ በገና በዓል ድፎ መጋገር፣ ሰንጋ መጣል፣ ጠጅና ጠላ መጎንጨት የተለመደ ነው፡፡ እንደ ፈረንጆቹ የበዛ ባይሆንም፣ በዚህ ጊዜ ስጦታ መስጠት የበዓሉ ዓቢይ መገለጫ ነው፡፡ ሕግ የኅብረተሰብን ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ትስብር የሚገዛ እንደመሆኑ መጠን እነ

ሲዳማውያን በቅርበት ልከታተሉት የምገባ የመሬት ምዝገባ አዋጅ ጸደቀ፤ ኣዋጁ ኣንድ ወጥየኢኮኖሚ ማኀበረሰብ ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል

የፍትሕ ሚኒስትሩ የተቃወሙት የመሬት ምዝገባ አዋጅ ይሁንታ ተቀባይነት አገኘ፤ ኣዋጁ ከክልሎች ሥልጣን ጋር የሚጋጭ ይዘት ኣለው   የፌዴሬሽን ምክር ቤት የከተማ መሬት ምዝገባ አዋጅን ለማፅደቅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን የይሁንታ ጥያቄ በፍትሕ ሚኒስትሩና በሌሎች ሁለት አባላት ተቃውሞ አፀደቀ፡፡ የምክር ቤቱ አባል የሆኑት የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አብዱላዚዝ አህመድ፦የቀረበው ረቂቅ አዋጅ መሬትን ብቻ መመዝገብ የሚመለከት ሳይሆን፣ ከመሬት ጋር ተያያዥ የሆኑ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን አብሮ መመዝገብ የሚያካትት በመሆኑና ይህ ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ባለመሆኑ ይሁንታው መጠየቁን ጠቁመዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የቀረበለት የከተማ መሬት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ የተለያዩ አንቀጾች ከክልሎች ሥልጣን ጋር የሚጋጭ ይዘት ያለው በመሆኑና አንድ ወጥ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ሲባል ነው የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ይሁንታ የጠየቀው፡፡  ረቂቅ አዋጁ በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ከተሞች መሬትንና በመሬት ላይ ያሉ ቋሚ ይዞታዎችን የመመዝገብ፣ የባለቤትነት መብትና የመጠቀም መብት ዕውቅናና ዋስትናን የሚሰጥ ነው፡፡ ነገር ግን ሕገ መንግሥቱ መሬትና የተፈጥሮ ሀብቶችን አጠቃቀምና አጠባበቅ የተመለከቱ ሕጐች የማውጣት ሥልጣን ለሕዝብ ተወካዮች ቢሰጥም፣ ክልሎች ደግሞ በፌዴራል መንግሥት የሚወጣውን ሕግ መሠረት በማድረግ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን አላቸው፡፡ የቀረበው የመሬት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ በተወሰነ ሁኔታ የክልሎችን ሥልጣን የሚጋፋ ቢሆንም፣ አንድ ወጥ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብን ለመፍጠር እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ ይህንን አዋጅ በማፅደቅ ተግባራዊ ለማድረግ ክልሎች የሚወከሉበት

Very Nice Ethiopian music 2013 Teferi Lembo Sidama

Image
Very Nice Ethiopian music 2013 Teferi Lembo Sidama