ሲዳማውያን በቅርበት ልከታተሉት የምገባ የመሬት ምዝገባ አዋጅ ጸደቀ፤ ኣዋጁ ኣንድ ወጥየኢኮኖሚ ማኀበረሰብ ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል
የፍትሕ ሚኒስትሩ የተቃወሙት የመሬት ምዝገባ አዋጅ ይሁንታ ተቀባይነት አገኘ፤ ኣዋጁ ከክልሎች ሥልጣን ጋር የሚጋጭ ይዘት ኣለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የከተማ መሬት ምዝገባ አዋጅን ለማፅደቅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን የይሁንታ ጥያቄ በፍትሕ ሚኒስትሩና በሌሎች ሁለት አባላት ተቃውሞ አፀደቀ፡፡ የምክር ቤቱ አባል የሆኑት የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አብዱላዚዝ አህመድ፦የቀረበው ረቂቅ አዋጅ መሬትን ብቻ መመዝገብ የሚመለከት ሳይሆን፣ ከመሬት ጋር ተያያዥ የሆኑ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን አብሮ መመዝገብ የሚያካትት በመሆኑና ይህ ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ባለመሆኑ ይሁንታው መጠየቁን ጠቁመዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የቀረበለት የከተማ መሬት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ የተለያዩ አንቀጾች ከክልሎች ሥልጣን ጋር የሚጋጭ ይዘት ያለው በመሆኑና አንድ ወጥ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ሲባል ነው የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ይሁንታ የጠየቀው፡፡ ረቂቅ አዋጁ በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ከተሞች መሬትንና በመሬት ላይ ያሉ ቋሚ ይዞታዎችን የመመዝገብ፣ የባለቤትነት መብትና የመጠቀም መብት ዕውቅናና ዋስትናን የሚሰጥ ነው፡፡ ነገር ግን ሕገ መንግሥቱ መሬትና የተፈጥሮ ሀብቶችን አጠቃቀምና አጠባበቅ የተመለከቱ ሕጐች የማውጣት ሥልጣን ለሕዝብ ተወካዮች ቢሰጥም፣ ክልሎች ደግሞ በፌዴራል መንግሥት የሚወጣውን ሕግ መሠረት በማድረግ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን አላቸው፡፡ የቀረበው የመሬት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ በተወሰነ ሁኔታ የክልሎችን ሥልጣን የሚጋፋ ቢሆንም፣ አንድ ወጥ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብን ለመፍጠር እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ ይህንን አዋጅ በማፅደቅ ተግባራዊ ለማድረግ ክልሎች የሚወከሉበት