በሃዋሳ ከተማ ውስጥ ሲዳማውያን በኢኮኖሚው ዘርፍ ብቁ ተወዳደር መሆን ኣልቻሉም፤በንግድ ስራ ከሌላው ብሄር እኩል ለመስራት ብዙ የልምድ ማነስ ይታይባቸዋል
እንደምታወቀው ኣብዘኛውን ቁጥር የምይዘው የሲዳማ ህዝብ የምኖረው በገጠር ነው። ሲዳማ ወደ ከተማ መግባት የጀመረው የኢህኣዴግ መግባትን ከተትሎ ነው። በወቅቱ የሲዳማውያን በገዛ ከተሞቻቸው ውስጥ ገብተው መኖር እንዲጀምሩ በምል የዞኑ መንግስት ብዙ እድሎችን በመፍጠር የህዝቡን ወደ ከተማ መግባት እና ወደ ከተሜነት መለወጥን ኣበረታቷል፤ ምንም እንኳን እንደታለመለት ሳይሆን ወደ ሃዋሳ እና ወደሌሎች የሲዳማ ከተሞች የገባው የገጠሩ ህዝብ በመንግስት የተሰጣቸውን መሬት ለሌላ ብሄር ተወላጅ ባለሃብቶች በመሸጥ እጅ ነካሽ ብሆኑም። ለኣብነት ያህል ከዛሬ ኣስር እና ኣስራም ኣምስት ኣመት ጀምሮ በተለይ በሃዋሳ ከተማ ውስጥ የሲዳማውያን በኢኮኖሚው የበላይነት እንዲኖራቸው ሲባል ለንግድ የምሆኑ ግንባር የሆኑ ቦታዎች በዞኑ መንግስት እና በከተማዋ ኣስተዳደር ለበርካታ ሲዳማውያን የተሰጠ ሲሆን፤ የተሰጣቸው መሬት ላይ የንግድ ቤቶችን በመገንባት የእድሉ ተጠቃሚ ከመሆን ኣብዛኛዎቹ የተሰጣቸውን መሬት ከላይ እንዳነሳሁት ለሌላ ብሄር ተወላጂ ባላሃብቶች በመሸጥ ሌሎቹን ጠቅመዋል ሲጠቅሙም ይታያል። በከተማዋ ግንባር ቀደም የሆኑ ቦታዎች ወይም በኣሁኑ ጊዜ ትላልቅ የንግድ ቤቶች ተሰርቶባቸው ብዙ ገንዝብ በማስገባት ላይ ያሉ ቦታዎች የዛሬ ኣምስት እስከ ኣስር ኣመታት በፊት ባለቤቶቻቸው እኔማናቸው ከተባለ መልሱ መቶበመቶ ሲዳማዎች እንደሆኑ ብዙ ሳይደከም የደረስበታል። በርግጥ በሃዋሳ ከተማ ውስጥ የሲዳማ ባለሃብት የለም ማለት ኣይደለም። በከተማዋ ውስጥ በመገንባት ላይ ከምገኙ ህንጻዎች ውስጥ በሲዳማ ባላሃብቶ በመገንባት ላይ ያሉ በርካታ ናቸው፤ ነገር ግን እንደከተማዋ ባላቤት ፤ ካለው የኢኮኖሚ ጡንቻ እና የዞኑ እና የከተማ ኣስተዳደር ከፈጠረላቸውም ምቺ የስራ እድል ኣን