Posts

Ethiopia: The Question of Identity

... there are some paradoxes, which are still difficult to explain. For example, the Harari, whose total population, according to the 1994 census result, is 131,139, are allowed to establish their own regional state. The state has no administrative zones or weredas and even the total numbers of kebeles of the city are 19 while the rural part of the state has 17 farmers associations. However, in contrast, the Sidama whose population is more than three million were given a zonal status within the Southern region. Whenever one thinks of the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (FDRE) a couple of things pops to mind. One is the controversial Article 39 where nations and nationalities were given the right to self determination up to secession. That was enshrined on the country's supreme legal document 19 years ago. Almost as memorable as the article itself is the display of extreme jubilation by one elderly member of the Constituent Assembly. The joy and exc

የሲዳማ እግር ኳስ ክለቦች በዚህ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ውድድሮች ድል ቀንቶቸዋል

Image
አዲስ   አበባ   ፣   ህዳር   29   ፣   2006 ( ኤፍ . ቢ . ሲ )   ዛሬ አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች የተለያዩ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተካሂደዋል። አዲስ አበባ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ተገናኝተው ጊዮርጊስ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በተመሳሳይ መከላከያ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 0 አሸንፏል። አርባ ምንጭ ላይ የተገናኙት ወላይታ ዲቻና አርባ ምንጭ ከነማ 0 ለ 0 ተለያይተዋል። አሰላ ላይ ሙገር ሲሚንቶን የገጠመው ሀዋሳ ከነማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፥ ይርጋለም ላይ በተመሳሳይ ሲዳማ ቡና መብራት ሀይልን 1 ለ 0 አሸንፏል።

‹‹የፖለቲካ ባህሉ መሠረት እንዲይዝ ብዙ ትግል ይጠይቃል››

Image
አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ፣ የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን አባል የነበሩ አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከሃያ ዘጠኙ የሕገ መንግሥት አርቃቂ ... ኮሚሽን አባላት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ (የአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) በፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት በዲግሪ የተመረቁት አምባሳደር ታዬ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ነበር ሥራ የጀመሩት፡፡ ይሁንና ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ በቆየው አገልግሎታቸው በዲፕሎማትነት፣ በቆንስላ ጄነራልነት፣ በአምባሳደርነትና በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ውስጥ አገልግለዋል፡፡ በተለያዩ አገሮች ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ውስጥ የሠሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ስዊዲንና አሜሪካ ይገኙበታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡  ሰለሞን ጎሹ  የዛሬ 19 ዓመት ኅዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም. ፀድቆ በሥራ ላይ የዋለውን የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የማርቀቅ ሒደትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ አምባሳደር ታዬን አነጋግሯቸዋል፡፡  ሪፖርተር፡- እርስዎ አባል የነበሩበት የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን አሁን በሥራ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥት በማርቀቁ ሒደት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ የሽግግሩ ዘመን ቻርተር የሽግግር መንግሥቱ ሕገ መንግሥት በማርቀቅ እንደሚያበቃ ይገልጻል፡፡ አጠቃላይ ሒደቱ ምን ይመስል ነበር? አወቃቀሩስ ምን ይመስል ነበር? በማርቀቅ ሒደቱ ተጨማሪ ሚና ከነበራቸው ሌሎች ተቋማት ጋርስ የነበራችሁ ግንኙነት እንዴት ነበር? አምባሳደር ታዬ ፡- የሽግግር መንግሥቱ ዋነኛ ተግባር ሕገ መንግሥት አዘጋጅቶ ሥልጣኑን በሕዝብ ለተመረጠ አካል
Image
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ ) ትምህርት ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም ክልልች የሚገኙ 499  የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የኢንተርኔት ተጠቃሚ ሊያደርግ ነው። በሚኒስቴሩ የትምህርት አይሲቲ ማእከል ሃላፊው ዶክተር ገበየሁ ወርቅነህ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ፥ ሚኒስቴሩ 422 አዳዲስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤቶችን ደግሞ የፕላዝማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከኢትዮቴሌኮም ጋር በጋራ እየሰራ ነው ብለዋል። የኢንተርኔት አገልግሎቱ  ፕላዝማው  የመቋረጥ እድል ቢያጋጥመው እንኳን  ተማሪዎቹ ከትምህርት ሚኒስቴር ዋናው ማእከል የሚተላለፈውን ትምህርት በአማራጭነት እንዲከታተሉበት ታሳቢ ያደረገ ነው። ኢትዮ ቴሌ ኮም በክልሎች የሚሸፈን ቢሆንም ለፕላዝማዎቹ 78 ሚሊየን እንዲሁም ለኢንተርኔት አገልግሎቱ ደግሞ 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር  ውለታ ገብቷል። በኢትዮቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ የፕላዝማውም ይሁን የኢንተርኔት አገልግሎቱ  ከግማሽ በላይ መከናወኑን ነው የተናገሩት።

ከሞጆ ሀዋሳ ለሚገነባው መንገድ የአፍሪካ ልማት ባንክ የ2.4 ቢልዮን ብር ሰጠ

Image
ከሞጆ ሀዋሳ ለሚገነባው አውራ መንገድ ከአፍሪካ ልማት ባንክ 2.4 ቢልዮን ብር በላይ ብድርና እርዳታ መገኘቱን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ ከሞጆ ሀዋሳ ለሚገነባው አውራ መንገድ  የ2.4 ቢልዮን ብር  በላይ  ብድርና ስጦታ ስምምነ ቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትር አቶ ሶፊያን አህመድ ና  የአፍሪካ ልማት ባንክ ተጠሪ ሚስ ጆሰፊን ንጉር ጋር ዛሬ ህዳር 27/2006   ተፈራርመዋል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትር አቶ ሶፊያን አህመድ እንዳሉት ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር የተፈረመው ስምምነት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አካል ለሆነው የመንገድ ልማት የሚውል ነው፡፡ አቶ ሶፍያን እንዳሉት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ባለቤትነት የሚገነባው የሀዋሳ ሞጆ መንገድ ወጭው ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍና በመንግስት የሚሸፈን ይሆናል፡፡ የመንገድ ፕሮጀክት ስራው ሲጠናቀቅ ወደ ደቡባዊ የሀገሪ ቱ ክፍል የሚደረገው የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ የሚደግፍ ይሆናል ም  ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክም ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑንም ሚንስትሩ ገልፀዋል፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ ተጠሪ ሚስ ጆሰፊን ንጉር በበኩላቸው  ከአፍሪካ ልማት ባንክ ተጠቃሚ የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ ግንባር ቀደ ም  መሆኗን አስታውሰው በቀጣይም ባንኩ የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወ/ገብርኤል ስምምነቱ  በሁለት ክፍሎች ለሚገነባው 201 ኪሎ ሜትሮችን ለሚሸፍነውና በአንድ ጊዜ 6 መኪኖችን ማሳለፍ የሚችለው ዘመናዊ የሞጆ ሞያሌ አውራ መንገድ አ