Posts

Organic Ethiopian Sidama

Image
       

የአትሌቶቹ ሪዞርት ሆቴል በሐዋሳ ሥራ ጀመረ

Image
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መዲና የሆነችው ሐዋሳ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሆቴልና የሪዞልት መዳረሻ እየሆነች ትገኛለች፡፡ በከተማዋ በርካታ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችና ሪዞልቶች ተገንብተዋል፡፡ በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ ባለፈው ቅዳሜ፣ ኅዳር 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ተመርቆ ሥራውን የጀመረው የገዛኸኝና እልፍነሽ ሆቴልና ሪዞልት፣ ለከተማዋ ተጨማሪ በመሆን የሆቴሎችና ሪዞልቶችን ቁጥር ከመጨመሩም በላይ ለሐዋሳ አዲስ የቱሪስት መዳረሻ ሆኗል፡፡ በሲዲኒ ኦሊምፒክ አሸናፊዎቹ ገዛኸኝ አበራና በባለቤቱ እልፍነሽ ዓለሙ ባለቤትነት የተገነባው ይህ ሆቴልና ሪዞልት 25 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ የሸፈነ ሲሆን፣ ግንባታው አጠናቅቆ አገልግሎት ላይ ለማዋል ብቻ 150 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጐበታል፡፡ አጠገቡ በመገንባት ላይ የሚገኘው ባለ አራት ፎቅ ሆቴል ሲጠናቀቅ ደግሞ በአጠቃላይ 200 ሚሊዮን ብር እንደሚፈጅ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ወቅት አትሌት ገዛኸኝ አበራ ተናግሯል፡፡ ሥራ የጀመረው የገዛኸኝና እልፍነሽ ሆቴልና ሪዞልት 40 መኝታ ክፍሎች ሲኖሩት፣ ከእነዚህ ውስጥ ራሱን የቻለ ቪላ፣ የራሱ ግቢ፣ ሳሎንና ዕቃ ቤት መመገቢያ ቤቶች አዳራሾችና በግቢው ውስጥ እንግዶች ለምግብነት የሚገለገሉባቸው የተለያዩ የአትክልና ፍራፍሬ እጽዋቶች ተተክለዋል፡፡ በአዘቦትና በበዓላት ቀኖች ኪራያቸው የሚለያይ ሆኖ፣ የአንዱ ቪላ ከፍተኛውና ዝቅተኛው የቀን ኪራይ ዋጋ ሁለት ሺሕ ብር ነው ተብሏል፡፡ ቀሪዎቹ ክፍሎች ጥንድና ነጠላ አልጋ ያላቸው ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችና ሪዞልቶች ሊኖሯቸው የሚገቡትን ሁሉ አሟልቶ የያዘ መሆኑ ባለኰከብ ሆቴል መገንባቱ ተነግሯል፡፡ የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑ፣ የደቡ

‹‹ድኅረ ምርጫ 97 በኢትዮጵያ ያለው ዲሞክራሲያዊ ምህዳር ጠቧል›› አና ጐሜዝ፣ የአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ አባል

Image
ምርጫ 97ን ተከትሎ የአውሮፓ ኅብረትን የምርጫ ታዛቢ ቡድንን የመሩት አና ጐሜዝ ምርጫውን ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ በኢትዮጵያ መንግሥትና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላይ የሰላ ትችትና ወቀሳ በመሰንዘር ይታወቃሉ፡፡  ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ በ26ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያን፣ ፓስፊክ እና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ የመጡትን አና ጐሜዝን በዴሞክራሲ፣ በእስረኞች አያያዝ፣ በሰብአዊ መብት አጠባበቅ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ  ነአምን አሸናፊ  አነጋግሯቸዋል፡፡    ሪፖርተር፡- ምርጫ 97ን ተከትሎ በእርስዎና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት ጥሩ የማይባል ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ያቀረቡት የቪዛ ጥያቄ እንዴት ነበር? ቪዛ መስጠት ያለመፈለግ አልያም ሌላ ነገር አጋጥሞዎታል?  አና ጐሜዝ ፡- በፍጹም፡፡ ምንም ዓይነት ክልከላ ወይም እምቢታ አላስተናገድኩም፡፡ ለነገሩ የአውሮፓ ኅብረት የሰብአዊ መብተት ንኡስ ኮሚቴ ባለፈው ሐምሌ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት በአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ አምባሳደር እኔም መሄድ እፈልግ እንደሆን ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ እኔም መሄድ ብፈልግም ባልፈልግም ቪዛ አትሰጡኝ ምን ያደርጋል አልኩት፡፡ እርሱ ግን የለም እንሰጥሻለን አለኝ፡፡ እሺ ለአሁን የሥራ ባልደረቦቼ ይጓዙ የእኔ ጊዜው ሲደርስ አመለክታለሁ አልኩ፡፡ ስለዚህ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የአፍሪካ ፓስፊክ ካሪቢያንና የአውሮፓ ኅብረት ጥምር ስብሰባ ላይ ለመካፈል የቪዛ ጥያቄ አቀረብኩ፤ እነርሱም ያለምንም ቅድመ ሁኔታና ያለምንም ችግር ቪዛውን ሰጥተውኛል፡፡ በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በማለፋቸው የተለየ የፖለቲካ አተያይ እየተፈጠረ

‹‹በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሥራ ይልቅ ለወሬና ለአሉባልታ ጊዜያቸው የሚያጠፉ አሉ››

Image
አቶ ዱቤ ጅሎ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር አገሪቱ በአትሌቲክሱ የምትሳተፍባቸው በርካታ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ከፊት ለፊቷ ይጠብቃታል፡፡ ወቅቱ ደግሞ የውድድር ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ በጀት ዓመት ተጠናቆ ቀጣዩ የተጀመረበት ነው፡፡ ስፖርቱን በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ግን ዝምታን መርጧል፡፡ በሌላ በኩል በአንድም ሆነ በሌላ የሚመለከታቸው አካላት የብሔራዊ ፌዴሬሽኑን ዝምታ እንዳልወደዱት የሚናገሩ አሉ፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ተቋሙ ባለፈው መስከረም 22 እና 23 ቀን 2006 ዓ.ም. 17ኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ድሬዳዋ ላይ ባከናወነበት ወቅት፣ አገሪቱ እስከዛሬ ከተለመዱት የውድድር ዓይነቶች በተጨማሪ አዳዲስ የሜዳ ተግባራትን ጨምሮ በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ዕቅድ እንዳላት፣ ለዚያ ደግሞ ከሙያተኞች ምርጫ እስከ አትሌቶች ምልመላ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ስምምነት ላይ መድረሱ ነው፡፡ የአገሪቱ የስፖርት መገናኛ ብዙሃኑ እግር ኳሱ ላይ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ እስከ ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የተጓዘበትን መንገድ ብቻ ትኩረት ማድረጉ አትሌቲክሱን ጨምሮ የተቀረው እንዲዘነጋ ሆኗል ይላሉ፡፡ ይህም ለስፖርቱ ዘርፍ አደገኛ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን በመያዝ  ደረጀ ጠገናው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር ከሆኑት አቶ ዱቤ ጁሎ ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡  • የውድድር ዓመቱ ሩብ ዓመት ተገባዷል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ እርስዎ ከሚመሩት የቴክኒክ ክፍል ጭምር ዝምታን መርጧል የሚሉ ቅሬታዎች ይቀርባሉ፡፡  መግለፅ የምችለው ቴክኒኩን በተመለከተ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ባለፈው ዓመት በርካታ

የሲዳማ ዞን ኣስተዳደር ለወጣቶች የስራ እድል ፈጥራለሁ ኣለ

በሲዳማ ዞን ዘንድሮ ከ72 ሺህ የሚበልጡ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል   ሐዋሳ ህዳር 20/2006 በሲዳማ ዞን በተያዘው ዓመት ከ72 ሺህ የሚበልጡ ስራ አጥ ወጣቶች በገጠር ስራ እድል ፈጠራ እና ልማት ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ ገለጹ፡፡ የዞኑ የገጠር ስራ እድል ፈጠራና ልማት ጽህፈት ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂደዋል፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ ከግል ኮሌጆችና አስርኛ ክፍል ላጠናቀቁ ዜጎች ሰፊ የስራ እድል ተዘጋጅቷል፡፡ ሃገራዊም ሆነ ክልላዊ የምጣኔ ሃብታችን እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የገጠር ስራ እድል ፈጠራና ልማት እንቅስቃሴ ለማሳካት የሚያስችሉ ጠንካራ ስልቶች ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የባለድርሻ አካላት ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ ሀገሪቱን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ ለማሰለፍ በመንግስት በኩል ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ልማታዊ እንቅስቃሴዎች አንዱ ለዜጎች ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባዋል ብለዋል፡፡ ለዘርፉ ወቅታዊ ድጋፍና ክትትል ማድረግ በግብርና የሚመራው ክፍለ ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ ለማሸጋገርና ልማታዊ ባለሃብቶችን ለመፍጠር ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ስራ አጥነትንና ድህነትን ለመቅረፍና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም መረባረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ከመሰረቱ ለመቅረፍ የአመራርንና የባለሙያውን አመለካከት ከመቀየር አኳያ ከ100 ሺህ ለመበልጡ የዞን፣ የወረዳና ለቀበሌ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና