የቀድሞ ሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን (SDC) እህት የልማት ድርጅቶች የት ደረሱ?
ለሲዳማ ህዝብ ልማት እና ብልጽግና እንዲያመጡ ተብለው የተቋቋሙ የቀድሞ የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን (SDC) እህት የልማት ድርጅቶች በዞኑ መንግስት ትኩረት በመነፈጋቸው የተነሳ ፈርስዋል፤ በመፍረስም ላይ ናቸው የሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽን (SDC) ፦ ለ ሲዳማ ህዝብ የልማት ስራዎች ለመስራት ቀርቶ ድርጅቱ በራሱ በሁለት እግሩ መቆም ኣልቻለም ፉራ ኮሌጅ፦ ከምመለከተው ኣካል ትኩረት በመነፈጉ የተነሳ ባጋጠመው የትምህርት ጥራት ጉድለት ኣብዛኛዎቹን የትምህርት ክፍሎች በመዝጋት ላይ ያለ ኮሌጅ ሆኗል ሬድዮ ሲዳማ፦ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ ለመንግስት የፖለቲካ ማካሄጃነት በመዋል ላይ ያለ ጋራምባ ኮንስትራክሽ እና ኣዳሬ ኢንጅኔሪንግ፦ ተበትነው እና ፈርሰው ታሪክ የሆኑ ሲዳማ ማክሮፋይናስ፦ በኦሞ ማክሮፋይናንስ የታፈነ ክፍል ኣንድ ኤስዲስ በኣይርሽ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የተቋቋመ እና በሲዳማ ውስጥ በርካታ የልማት ተግባራትን ስያከናውን የቆየ ድርጅት ነው። ይሄው ድርጅት በወቅቱ በርካታ እህት ድርጅቶችን በስሩ ኣቋቁሞ ይስራ የነበረ ሲሆን ካቋቋማቸው ድርጅቶች መካከል በኣሁኑ ጊዜ ኣብዛኛዎቹ ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ በማገልግል ላይ ናቸው፤ የቀሩት ደግሞ ፍርስዋል። እንደ ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ዘገባ ከሆነ፦ ከሲዳማ ልማት ፕሮግራምነት ወደ ሲዳማ ልማት ኮርፕሬሽነትን የተቀየረው SDC ፤ በወቅቱ የሲዳማ ህዝብ ኩራት ሆኖ ለሲዳማ ህዝብ ልማት የምቆረቆሩ ግለሰቦች እንደንብ የምሯሯጡበት የነበረ ሲሆን፤ በኃላ ላይ በመንግስት ጠልቃ ገቢነት የተነሳ የስራ ኣቅሙ የተመታ እና የላሸቀ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በኣሁኑ ወቅት ስፋፊ የእርሻ መሬት በኮንትራት መልክ በመያዝ በተለይ በቆሎን በመዝራት ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ነ