Posts

በመልካም አስተዳደር ከ52 የአፍሪካ አገራት ኢትዮጵያ 33ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

Image
ከ11 የምስራቅ አፍሪካ አገራት ደግሞ በ8ኛ ላይ ተቀምጣለች መልካም አስተዳደር ከ100% ሞሪሺየስ - 80 ቦትስዋና - 78 ኬፕቨርዴ - 77 ሲሸልስ - 78 ደቡብ አፍሪካ - 71 ሶማሊያ - 8 የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን የ2013 የመልካም አስተዳደር ውጤታማነት ደረጃን “Ibrahim Index of African Governance (IIAG)” ይፋ ያደረገው ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር፡፡ በመልካም አስተዳደር ምርጥ ተብላ ከአፍሪካ በአንደኝነት ደረጃ የተቀመጠችው ሞሪሺየስ ስትሆን የመጨረሻዋ አገር ሶማሊያ ናት፡፡ ኢትዮጵያ ከ52 የአፍሪካ አገራት 33ኛ ደረጃ ተሰጥቷታል፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን የመልካም አስተዳደር ሁኔታ በአራት መስፈርቶች የገመገመው የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን፤ ባለፉት 10 ዓመታት በሰው ሃብት ልማት ላይ ከፍተኛ መሻሻል መታየቱን ገልፆ፤ በዋናነት በጤና እና በትምህርት መስኮች ለውጥ መመዝገቡን አመልክቷል፡፡ ኢትዮጵያ በመልካም አስተዳደር ከ52 የአፍሪካ አገራት 33ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከ100 ነጥብ 47.6 በማግኘት ሲሆን የአፍሪካ አማካይ ነጥብ 51.6 ነው ይላል ፋውንዴሽኑ፡፡ ኢትዮጵያ ከ11 የምስራቅ አፍሪካ አገራት ጋር ተወዳድራም በ8ኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠች የጠቆመው የፋውንዴሽኑ መረጃ፤ በዚህ የአፍሪካ ቀጠናም ኢትዮጵያ የሚጠበቀውን የ47.9 አማካይ ነጥብ አለማግኘቷን አመልክቷል፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት በመልካም አስተዳደር ያላትን ደረጃ ያሻሻለችው በ5.1 ብቻ ነው ይላል፤ መረጃው፡፡ የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን “ኢብራሂም ኢንዴክስ ኦፍ አፍሪካን ጋቨርናንስ” ሪፖርት፤ የአፍሪካ አገራት በአጠቃላይ በመልካም አስተዳደር መሻሻል እንዳሳዩ ጠቁሟል፡፡ አገራቱ የተመዘኑት የመልካም አስተዳደር መገለጫ ናቸው ተብለው በሚታ

የሰብዓዊ መብት አፈጻጸምን የሚከልሰው ዕቅድ

ዕውቁ ኖርዌያዊው ተመራማሪ ሼትል ትሮንቮል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) በኢትዮጵያ ላይ ያወጣውን ሪፖርት ተመርኩዞ፣ ‹‹Human Rights Violations in Federal Ethiopia: When Ethnic Identity is a Political Stigma›› በሚል ርዕስ በ2000 ዓ.ም. አንድ የምርምር ጽሑፍ አሳትመው ነበር፡፡ ተመድ በ1999 ዓ.ም. ያወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ ብሔርን መሠረት ያደረገ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚፈጸም ይከሳል፡፡ ፕሮፌሰር ትሮንቮል በጥናታቸው የተመድ ሪፖርት ድምዳሜ ትክክል እንደሆነ ይከራከራሉ፡፡  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ ለትሮንቮል በጻፉት የታተመ ምላሻቸው በኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እንደሚደረግና የመብት ጥሰቱ ክስ ስህተት እንደሆነ፣ ጥሰት አለ ከተባለም ብሔርን መሠረት ያደረገ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደማይፈጸም ተከራክረዋል፡፡ በ2001 ዓ.ም. ለንባብ በበቃው ምላሻቸው አቶ ጌታቸው እንደ ሼትል ትሮንቮል ያሉ የውጭ አገር ተመራማሪዎች ስለ ኢትዮጵያ ማኅበራዊ፣ ሕጋዊና ፖለቲካዊ ውስብስብ ጉዳዮች በድፍረት ለማሳተም ለራሳቸው ነፃነት የሚሰጡት፡ በአገሪቱ ጥቂት ቀናትን በዛ ካለም ወራትን ካሳለፉ በኋላ መሆኑን ተችተው ነበር፡፡ እነዚህ ተመራማሪዎች በውጭ ጸሐፍት የተጻፉ የምርምር ሥራዎችን ብቻ በማጣቀስ ከባድ ድምዳሜ ላይ እንደሚደርሱም አመልክተዋል፡፡  ፕሮፌሰር ትሮንቮል ለአቶ ጌታቸው ምላሽ በሰጡት ሌላ ምላሽ ስለኢትዮጵያ ከአቶ ጌታቸው የተሻለ ግንዛቤ እንዳላቸው ገልጸው ነበር፡፡ የመመረቂያ ጽሑፋቸው በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ላይ እንደነበር ያሰታወሱት ትሮንቮል፣ ከ1980ዎቹ መጀመሪያ ጀምረው በኢትዮጵያ ስላለው የፖለቲካና

ቡና ለመጠጣት ተመራጩ ሰዓት - ዘ ቴሌግራፍ

Image
ቡና በመጠጣት በአነቃቂው ንጥረ ነገር አማካኝነት ውሎዎን ነቃ ብለው ለማሳለፍ ከፈለጉ ተመራጩ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 5፡30 ያለው ነው ሲሉ የነርቭ ስርዓት ተመራማሪዎች የገለጹት፡፡ አንድ ሲኒ አሪፍ ቡና ከምንም ነገር በፊት በጠዋት መጠጣት ጥሩ     ቢሆንም ትንሽ ረፈድ ሲል መጠጣቱ ደግሞ የበለጠ ጥሩ ነው ብለዋል በዘርፉ ጥናት ያከናወኑ ሳይንትስቶች፡፡ ይህም የሆነው ኮርቲሶል የተባለውና ሰውነትን ለመቆጣጠር የሚረዳው ዋናው ሆርሞናችን ከቡናው ንጥረ-ነገር ካፌን ጋር በሚኖረው መስተጋብር ውስጣዊ ሰርዓቱንና መነቃቃትን ስለሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡ በደማችን ውስጥ የሚኖረው ኮርቲሶል ከእንቅልፍ በነቃን ቅጽበት መጠኑ ከፍተኛ ሲሆን ለአንድ ሰዓት ያህል ማለትም በአማካኝ ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ሆኖ ይዘልቃል፡፡ ኮርቲሶል መመንጨት ዝቅ በሚል ሰዓት ማለትም ረፈድ ሲል ቡና መጠጣቱ አዋጭ ነው ይላሉ በቤተሳይዳ ሜሪላንድ የጤና ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የነርቭ ስርዓት ተመራማሪው ስቴቨን ሚለር፡፡ የኮርቲስል ሆርሞን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ባለበት ጊዜ ቡና መጠጣቱ ግን የቡናውን አነቃቂ ንጥረ ነገር ካፌንን እንዲላመዱት ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ማነቃቂያ እንዲፈልጉ ሊያደርግ ይችላል ብለዋል ስቴቨን፡፡ ሌሎች ተመራማሪዎች ደግሞ ከሰዓት በኋላ ቡና መጠጣት ከምሳ በኋላ የሚከሰተውን ቀልብ ያለመሰብሰብ ችግር ይፈታል ይላሉ፡፡ ስቴቨን ሚለር በደማችን የሚኖረው የኮርቲስል መጠን ምሽት 1 ሰዓት እና ከ11፡30 እስከ 12፡30 ባሉት ሰዓታትም   እንደሚጨምር   ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ትክክለኛው የቡና መጠጫ ሰዓት ይህ ነው ለማለት እንደሰዎቹ የኮርቴስል መጠን የመጨመርና መቀነስ ሂደትና ከእንቅልፋቸው እንደሚነሱበት ሰዓት ከሰው ሰው እንደሚለያ

Land Grabs In Africa – A Double-Edged Sword

Image
VENTURES AFRICA – Foreign investors are taking as much as they can from an impoverished nation, including its crops, land and the hard work of an Ethiopian population, to serve their own interests above others. According to the Food and Agriculture Organisation (FAO), 14.56 million hectares of Ethiopia’s 100 million hectare land mass is arable land, most of it cultivated by small hold, subsistence farmers. International investors have taken note and are rushing to this country, once synonymous with starvation, to take advantage of the government’s new push to improve its agricultural production capacity. But many fear the government’s sale of arable land to foreign nationals will create a modern form of agricultural colonialism. One such arrangement, launched in 2009 under Saudi Arabia’s King Abdullah initiative and forming part of a $100-million investment scheme in Ethiopian agriculture, had farmers grow teff (a North African cereal grass), white wheat, maize and white sorghum,

ኢትዮጵያውያን የመንግስትን ስለላ አይፈሩም፤ ሁለመናቸው በመንግስት እጅ ነው

የአሜሪካ የስለላ ተቋም፣ አለምን ከዳር ዳር በሚያዳርስ የመረጃ መረብ፣ የውጭ ዜጎችን (የጠቅላይ ሚኒስትሮችና የፕሬዚዳንቶች ጭምር) የስልክና የኢሜይል ልውውጦችን የቱን ያህል በስፋት እንደሚሰልል ሲታይ ጉድ ያሰኛል። በእርግጥ የስለላ ተቋሙ የአሜሪካ ዜጐችን በዘፈቀደ አልሰልልም ብሏል፡፡ የዜጐች የግል ሕይወትና የመልእክት ልውውጥ በመንግስት መነካት እንደሌለበት በአገሪቱ ሕገመንግስት ታውጇላ። የዜጐችን የስልክ እና የኢሜይል መልእክት የምበረብረው፣ በተጠርጣሪዎች ላይ በማተኮርና ፍርድ ቤትን በማስፈቀድ ብቻ ነው ይላል - የአሜሪካ የስለላ ተቋም። ታዲያ “ፍርድ ቤት” ሲባል፣ የወትሮው አይነት አይደለም። በሚስጥር የሚሰራ ልዩ ፍርድ ቤት ነው። ማዘዣ ወረቀቱም በሚስጥር የሚጠበቅ ስለሆነ፣ ከጊዜ በኋላ የፍርድ ቤቱን ውሳኔዎችና ትዕዛዞች መመርመር ያስቸግራል። ፍርድ ቤትን ማስፈቀድ በኢትዮጵያ አይሰራም በእውነቱ፣ እንዲህ አይነቱ ድብቅ የፍርድ ቤት አሰራር፣ ከታላቋ የነፃነት አገር (ከአሜሪካ) የሚጠበቅ አይደለም። ለማንኛውም፣ የስለላ ተቋሙ “የፍርድ ቤት” ማዘዣ በማቅረብ ባለፉት አምስት አመታት የተለያዩ መረጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡ ጉግል፣ ያሁ፣ ሆትሜይል፣ ፌስቡክ እንዲሁም ኤቲኤንድ ቲ የመሳሰሉ የኢንተርኔት እና የስልክ ኩባንያዎችም፣ የመቶ ሺ ገደማ ደንበኞች መረጃ ለስለላ ተቋሙ ለማስረከብ መገደዳቸውን ገልፀዋል። ኩባንያዎቹ የሕግ ግዴታ ሆኖባቸው እንጂ፣ የአንድም ሰው መረጃ አሳልፈው መስጠት አይፈልጉም - እንጀራቸው ነዋ። በደንታ ቢስነት የደንበኞችን መረጃ እያወጣ ለመንግስት የሚዘረግፍ ኩባንያ፣ የቱንም ያህል ግዙፍ ቢሆን መንኮታኮቱና በአጭር መቀጨቱ አይቀርም። ደንበኞቹ ይሸሹታል፤ ፊታቸውን ወደ ሌላ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ በማዞር ጀርባቸውን ሲሰጡት፣ በኪሳራ ይፈራር