Posts

ቡና ለመጠጣት ተመራጩ ሰዓት - ዘ ቴሌግራፍ

Image
ቡና በመጠጣት በአነቃቂው ንጥረ ነገር አማካኝነት ውሎዎን ነቃ ብለው ለማሳለፍ ከፈለጉ ተመራጩ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 5፡30 ያለው ነው ሲሉ የነርቭ ስርዓት ተመራማሪዎች የገለጹት፡፡ አንድ ሲኒ አሪፍ ቡና ከምንም ነገር በፊት በጠዋት መጠጣት ጥሩ     ቢሆንም ትንሽ ረፈድ ሲል መጠጣቱ ደግሞ የበለጠ ጥሩ ነው ብለዋል በዘርፉ ጥናት ያከናወኑ ሳይንትስቶች፡፡ ይህም የሆነው ኮርቲሶል የተባለውና ሰውነትን ለመቆጣጠር የሚረዳው ዋናው ሆርሞናችን ከቡናው ንጥረ-ነገር ካፌን ጋር በሚኖረው መስተጋብር ውስጣዊ ሰርዓቱንና መነቃቃትን ስለሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡ በደማችን ውስጥ የሚኖረው ኮርቲሶል ከእንቅልፍ በነቃን ቅጽበት መጠኑ ከፍተኛ ሲሆን ለአንድ ሰዓት ያህል ማለትም በአማካኝ ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ሆኖ ይዘልቃል፡፡ ኮርቲሶል መመንጨት ዝቅ በሚል ሰዓት ማለትም ረፈድ ሲል ቡና መጠጣቱ አዋጭ ነው ይላሉ በቤተሳይዳ ሜሪላንድ የጤና ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የነርቭ ስርዓት ተመራማሪው ስቴቨን ሚለር፡፡ የኮርቲስል ሆርሞን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ባለበት ጊዜ ቡና መጠጣቱ ግን የቡናውን አነቃቂ ንጥረ ነገር ካፌንን እንዲላመዱት ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ማነቃቂያ እንዲፈልጉ ሊያደርግ ይችላል ብለዋል ስቴቨን፡፡ ሌሎች ተመራማሪዎች ደግሞ ከሰዓት በኋላ ቡና መጠጣት ከምሳ በኋላ የሚከሰተውን ቀልብ ያለመሰብሰብ ችግር ይፈታል ይላሉ፡፡ ስቴቨን ሚለር በደማችን የሚኖረው የኮርቲስል መጠን ምሽት 1 ሰዓት እና ከ11፡30 እስከ 12፡30 ባሉት ሰዓታትም   እንደሚጨምር   ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ትክክለኛው የቡና መጠጫ ሰዓት ይህ ነው ለማለት እንደሰዎቹ የኮርቴስል መጠን የመጨመርና መቀነስ ሂደትና ከእንቅልፋቸው እንደሚነሱበት ሰዓት ከሰው ሰው እንደሚለያ

Land Grabs In Africa – A Double-Edged Sword

Image
VENTURES AFRICA – Foreign investors are taking as much as they can from an impoverished nation, including its crops, land and the hard work of an Ethiopian population, to serve their own interests above others. According to the Food and Agriculture Organisation (FAO), 14.56 million hectares of Ethiopia’s 100 million hectare land mass is arable land, most of it cultivated by small hold, subsistence farmers. International investors have taken note and are rushing to this country, once synonymous with starvation, to take advantage of the government’s new push to improve its agricultural production capacity. But many fear the government’s sale of arable land to foreign nationals will create a modern form of agricultural colonialism. One such arrangement, launched in 2009 under Saudi Arabia’s King Abdullah initiative and forming part of a $100-million investment scheme in Ethiopian agriculture, had farmers grow teff (a North African cereal grass), white wheat, maize and white sorghum,

ኢትዮጵያውያን የመንግስትን ስለላ አይፈሩም፤ ሁለመናቸው በመንግስት እጅ ነው

የአሜሪካ የስለላ ተቋም፣ አለምን ከዳር ዳር በሚያዳርስ የመረጃ መረብ፣ የውጭ ዜጎችን (የጠቅላይ ሚኒስትሮችና የፕሬዚዳንቶች ጭምር) የስልክና የኢሜይል ልውውጦችን የቱን ያህል በስፋት እንደሚሰልል ሲታይ ጉድ ያሰኛል። በእርግጥ የስለላ ተቋሙ የአሜሪካ ዜጐችን በዘፈቀደ አልሰልልም ብሏል፡፡ የዜጐች የግል ሕይወትና የመልእክት ልውውጥ በመንግስት መነካት እንደሌለበት በአገሪቱ ሕገመንግስት ታውጇላ። የዜጐችን የስልክ እና የኢሜይል መልእክት የምበረብረው፣ በተጠርጣሪዎች ላይ በማተኮርና ፍርድ ቤትን በማስፈቀድ ብቻ ነው ይላል - የአሜሪካ የስለላ ተቋም። ታዲያ “ፍርድ ቤት” ሲባል፣ የወትሮው አይነት አይደለም። በሚስጥር የሚሰራ ልዩ ፍርድ ቤት ነው። ማዘዣ ወረቀቱም በሚስጥር የሚጠበቅ ስለሆነ፣ ከጊዜ በኋላ የፍርድ ቤቱን ውሳኔዎችና ትዕዛዞች መመርመር ያስቸግራል። ፍርድ ቤትን ማስፈቀድ በኢትዮጵያ አይሰራም በእውነቱ፣ እንዲህ አይነቱ ድብቅ የፍርድ ቤት አሰራር፣ ከታላቋ የነፃነት አገር (ከአሜሪካ) የሚጠበቅ አይደለም። ለማንኛውም፣ የስለላ ተቋሙ “የፍርድ ቤት” ማዘዣ በማቅረብ ባለፉት አምስት አመታት የተለያዩ መረጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡ ጉግል፣ ያሁ፣ ሆትሜይል፣ ፌስቡክ እንዲሁም ኤቲኤንድ ቲ የመሳሰሉ የኢንተርኔት እና የስልክ ኩባንያዎችም፣ የመቶ ሺ ገደማ ደንበኞች መረጃ ለስለላ ተቋሙ ለማስረከብ መገደዳቸውን ገልፀዋል። ኩባንያዎቹ የሕግ ግዴታ ሆኖባቸው እንጂ፣ የአንድም ሰው መረጃ አሳልፈው መስጠት አይፈልጉም - እንጀራቸው ነዋ። በደንታ ቢስነት የደንበኞችን መረጃ እያወጣ ለመንግስት የሚዘረግፍ ኩባንያ፣ የቱንም ያህል ግዙፍ ቢሆን መንኮታኮቱና በአጭር መቀጨቱ አይቀርም። ደንበኞቹ ይሸሹታል፤ ፊታቸውን ወደ ሌላ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ በማዞር ጀርባቸውን ሲሰጡት፣ በኪሳራ ይፈራር

የገዛኸኝና እልፍነሽ ሆቴልና ሪዞርት በዱላ ቅብብል ውድድር ይመረቃል

Image
ማራቶን የማዘጋጀት ሃሳብ አላቸው                 በሀዋሳ ከተማ የተገነባውን ገዛኸኝና እልፍነሽ ሆቴልና ሪዞርት ህዳር 14 በይፋ ሲመረቅ ልዩ የ10 ኪሎሜትር የዱላ ቅብብል ውድድር እንደሚካሄድ ታወቀ፡፡ በምረቃው ስነስርዓት ላይ በክብር እንግድነት እንዲገኙ ኡጋንዳዊው የኦሎምፒክ እና የዓለም ሻምፒዮን የማራቶን ድርብ አሸናፊ ስቴፈን ኪፕሮች እና ኬንያዊ አትሌት ጄፈሪ ሙታይ ተጋብዘዋል፡፡ በሌላ ዜና ባልና ሚስቶቹ ማራቶኒስቶች አትሌት ገዛኸኝ አበራ እና አትሌት እልፍነሽ አለሙ በሚቀጥለው ዓመት አንድ የማራቶን ውድድር በኢትዮጵያ ለማዘጋጀት ማሰባቸውን ሲያስታወቁ ተተኪ አትሌቶችን ለማግኘት የአገር ውስጥ ውድድሮች መብዛታቸው አስፈላጊ እንደሆነ ስላመኑበት የነደፉት እቅድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ አትሌት ገዛኸኝ አበራ እና አትሌት እልፍነሽ አለሙ ትናንት በዋና ፅህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ የሆቴልና ሪዞርት ምረቃው ከአትሌቲክስ ውድድር ጋር ማያያዝ ያስፈለገው ተተኪ አትሌቶች የእነሱን አርዓያ እንዲከተሉ ለማነሳሳት በማሰባቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አትሌት እልፍነሽ አለሙ‹‹ ማንኛውም ሰው ዓላማዬ ብሎ ከሰራ ለየትኛውም ደረጃ ይደርሳል፡፡ በአሁን ዘመን ያሉ አትሌቶች ደከመን፣ ሰለቸን፤ ከሳን ፤ ጠቆርን ሳይሉ በትጋት መስራት አለባቸው፡፡ በስፖርቱ እኛ የደረስንበት ስኬት ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ከእኛ በላይ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ማወቅ አለባቸው›› ብላለች፡፡ አትሌት ገዛኸኝ በበኩሉ ‹‹እኛ ሮጠን ሆቴሉን ሰርተናል፤ አትሌቱም እንደማንኛውም ህብረተሰብ በትጋት ከሰራ ይሳካለታል፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡ በሆቴልና ሪዞርቱ ምረቃ ላይ የሚካሄደው የ10 ኪሎሜትር የዱላ ቅብብል ውድድሩ መነሻውና መድረሻው ገዛኸኝና እልፍነሽ ሆቴልና ሪዞርት እንደሆነ የገለፀው አትሌ

አባባ ተስፋዬ - በሐዋሳው ተረት ቤት

Image
“ወጣቶች፤ ሀገራችሁን ውደዱ፤ አንብቡ!”            በሐዋሳ ከተማ ሐይቁ ዳርቻ በሚገኘው “ሌዊ ሪዞርት” የተሰራው “የተረት ቤት” ጥቅምት 23 ቀን 2006 ዓ.ም ተመርቋል፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመርያው እንደሆነ የተነገረለት “የተረት ቤት”፤ ለበርካታ አስርት ዓመታት በሬዲዮና በቴሌቪዥን ተረት በመንገር በሚታወቁት የ90 አመቱ አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) ስም የተሰየመ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት የተረት ቤቱ ሲመረቅ በክብር እንግድነት የተገኙት አባባ ተስፋዬ፤ “የጥንቸልና የዔሊ ውድድር” የተሰኘ ታሪክ በመናገር ተረት ቤቱ በይፋ ሥራ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል፡፡ በምረቃው ዕለት ንግግር ያደረጉት የሌዊ ሪዞርት ባለቤት አቶ ወንድይፍራው እንደሻው፤ የተረት ቤቱን መሰራት አስመልክተው ሲናገሩ፤ “የልጆችን የንባብ ልምድ ለማዳበርና በየሳምንቱ ለልጆች ቁምነገር በተረት መልክ የምናስተላልፍበት ነው” ብለዋል፡፡ ተረት ቤቱ ከቢዝነስ ጋር የተገናኘ አይደለም ያሉት አቶ ወንድይፍራው፤ “በውጭ ፊልሞችና ታሪኮች እየተመሰጡ ላሉ ልጆቻችን ታሪካችንን እና ባህላችንን ለማስተላለፍ አስበን ነው” በማለት የተረት ቤቱን ዓላማ ተናግረዋል፡፡ በአዋሳው የተረት ቤት ምረቃ ወቅት የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ መልካሙ ተክሌ ከአባባ ተስፋዬ ጋር አጭር ቆይታ በማድረግ የልጅነት ሕይወታቸውን ያስታወሳቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የለቀቁበትን ሁኔታና ዳግም የመመለስ ሃሳብ እንዳላቸው እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን አንስቶ ተጨዋውተዋል፡፡ እነሆ፡- በልጅነትዎ ተረት እየሰሙ ነው ያደጉት እንዴ? ተረት አይደለም በልጅነቴ የተነገረኝ፡፡ ቤተሰቦቼ እርግጡን እየነገሩ ነው ያሳደጉኝ፡፡ ቤተሰባችን ለንጉሣውያን ቤተሰብ ቀረብ ያለ ነው፡፡ የተወለድኩት ባሌ አካባቢ ነው፡፡ ጥሩ ነገር ስለመስራት፣ ትእ