Posts

IMF: Ethiopian economy needs revamp to avert slowdown

Addis Ababa - Ethiopia's economy has reached a crossroads and, to prevent growth rates from falling, needs to be restructured to encourage more private sector investments, the International Monetary Fund said on Wednesday. Economic output should grow 7.5 percent in each of the next two fiscal years, to July 2014 and 2015, down slightly from the 8.5 percent in 2011/12, Jan Mikkelson, the IMF's representative in Ethiopia, told reporters. It expects year-on-year inflation - which dipped to 6.9 percent in September from 7.0 percent in August - to remain in single digits. The government has reported double-digit GDP growth for much of the past decade, but some economists say those figures are inflated. It said in July it expected the economy to maintain a growth rate of 11 percent in 2013/14. Growth has been propelled by huge public spending on infrastructure, while an expansion in services and agriculture has also boosted the economy. Ethiopia's exports include coff

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ2005 ዓ.ም ሪፖርት እንደሚያመለክተው በዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ይጨምራል፤

Image
የወባ በሽታና የመከላከል ጥረቶች የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ 2005  ዓ . ም ሪፖርት እንደሚያመለክተው በዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ይጨምራል፤ ከሁለት ሺ ሜትር በታች በሆኑ የወይና ደጋና ቆላማ አካባቢዎች ሁሉ ይተላለፋል  -  የወባ በሽታ። በአብዛኛው ከክረምት ወራት በኋላ ከመስከረም እስከ ህዳር ባለው ወቅት ስርጭቱ የሚጨምር ሲሆን በአንዳንድ ቦታዎች ከበልግ ዝናብ ተከተሎ ባሉ ወራትም ይከሰታል። ስለ ወባ በሽታ አጠቃላይ ግንዛቤ ለማስረጽ ይረዳ ዘንድ እንዲሁም በሽታውን በመከላከል በኩል ስለሚደረጉት ጥረቶች መረጃ ለማግኘት ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጎራ ብለን ነበር። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የወባ መከላከልና መቆጣጠር ቡድን መሪ የሆኑት ወይዘሪት ህይወት ሰለሞን ስለወባ በሽታና የመከላከል ጥረቱን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተውናል። « የወባ በሽታ ፕላስሞድየም የሚባል በአይን የማይታይ ረቂቅ ጥገኛ ተህዋስ በደም ውስጥ መኖር፣ ማደግና መራባት ምክንያት የሚከሰት በሽታ ነው። ይህ በሽታ በአለም ላይ በብዙ ቦታዎች ይከሰታል። በአገራችንም ሰባ አምስት በመቶ በሚሆነው የቆዳ ስፋት የወባ በሽታ ይታያል። ስልሳ ስምንት በመቶ የሚሆነው ህዝብም ለበሽታው ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ይገኛል »  ይላሉ ወይዘሪት ሕይወት። የወባ በሽታ አኖፊለሰ በመባል በምት ታወቀው እንስት የወባ ትንኝ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ተህዋስ ነው። ትንኟ የምታስተላልፈው የበሽታው መንስኤ የሆነውን ተህዋስ ነው፡፡ በሃገራችን ሁለት ዋና ዋና የወባ ተህዋስ ዝርያዎች አሉ የሚሉት ቡድን መሪዋ ፕላዝሞዲየም ፋልሲፓረም እና ፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ በመባል እንደሚ ታወቁ ይናገራሉ። በሽታው አኖፊለስ በመባል በምትታወቀው እንስቷ የወባ

በደቡብ የአመራር አካላት ለስፖርት ትኩረት እንዲሰጡ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳሰቡ፤ በኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ የሲዳማ እግር ኳስ ክለቦች ነጥብ ኣልባ ጉዞ ቀጥሏል

Image
የሲዳማ እግር ኳስ ክለቦች የሆኑት ሃዋሳ ከነማ እና ሲዳማ ቡና በሁለተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜዬር ሊግ ጫዋታ በተገጣሚዎቻቸው በመሸነፋቸው በሊግ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻ ደረጃዎችን ይዘው ይገኛሉ። በሌላ በኩል፤ የስፖርት ልማቱን በማጠናከር ጤናማና አምራች ዜጋ ለማፍራት የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት ትኩረት ሰጥቶ ሊሠሩ እንደሚገባ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሳሰቡ። የደቡብ ክልል የስፖርት ምክር ቤት  17 ኛው መደበኛ ጉባዔ ከትናንት በስቲያ በሃዋሳ ተካሂዷል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ደሴ ዳልኬ ጉባዔውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት፤ ጤናማና አምራች ዜጋ ለማፍራት ስፖርት ያለው ጠቀሜታ የጎላ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ለዘርፉ ዕድገት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል፡፡ « ውጤታማ የሆኑ ተተኪ ስፖርተኞችን የማፍራት፣ በጥናትና ምርምር ሥራዎች የክልሉን የስፖርት ዕድገት የመደገፍና ለኅብረተሰቡ አስፈላጊውን አገልግሎት የመስጠት ተልዕኮ ስኬታማ እንዲሆን የአመራሩ ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ጠንክሮ መሥራት ይገባል »  ብለዋል። በክልሉ የዘርፉን ዓላማ ለማስፈጸም በፋይናንስ፣ በአደረጃጀትና በአመራር የስፖርቱ ልማት ሕዝባዊ መሠረት እንዲኖረው የማድረግ፣ ከመንግሥት ድጎማ ተላቅቆ ራሱን እንዲችል ማድረግ ይጠበቃል። ኅብረተሰቡ በሚያመቸው ሁኔታ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተሳታፊ እንዲሆን ማስቻል፣ እንዲሁም የሴቶችን እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሥራዎች በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባም አቶ ደሴ ጠቁመዋል፡፡ በክልሉ የስፖርት ልማት በማፋጠን የኅብረ ተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ምርጥ ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት የሚያግዙ የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች፣ የሕግ ማዕቀፎች፣ የል

ሰሞኑን በደቡብ መገናኛ ብዙሃን ሲዳማን በተመለከተ የተሰራጩ ዜናዎች

በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ በተያዘው በጀት ዓመት 48 ኪ.ሜትር የመንገድ ሥራ ለማከናወን ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የወረዳው መንገድ ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡  የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አበባየሁ በየነ እንደገለጹ በወረዳው 162 ኪ.ሜ ቀበሌን ከቀበሌ፣ ወረዳን ከወረዳ የሚያገናኝ መንገድ ለመሥራት ዕቅድ ተይዟል፡፡  በ2005 ዓ.ም 58 ኪ.ሜትር የመንገድ ሥራ በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ኘሮግራም ለመስራት ታቅዶ ወደ ሥራ የተገባ መሆኑን ተናግረው ከዚህም፣ በ3 ኪሎ ሜትር መንገድ አፈር የማልበር ስራ በ3 ኪ.ሜትር ድንጋይ የማንጠፍ ተግባር የተከናወነ ሲሆን 15.8 ሜትር በግል ተቋራጮች በኩል በተፈጠረ ክፍተት በተያዘለት ጊዜ አለመጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡  ባለፈው ዓመት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተሰራው የመንገድ ሥራ በገንዘብ ሲተመን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሆኑን  አስረድተዋል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት 48 ኪ.ሜትር ቀበሌን ከቀበሌ የሚያገናኝ መንገድ ለመሥራት ዕቅድ እንደተያዘ ጠቁመው ይህ ሥራም፣ ለሴቶች፣ ለሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡  በዚህ ሥራም 22 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግና ከ7 መቶ በላይ ሰዎች ያሳትፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡ ሪፖርተራችን አካሉ ጥላሁን ከበንሳ ቅርንጫፍ እንደዘገበው፡፡ በዘንድሮው የምርት ዘመን ከሁለት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት መታቀዱን የሲዳማ ዞን የሸበዲኖ የወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ በወረዳው ከሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች ፣ የቀበሌ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በ2ዐዐ5 ዓ/ም የበልግና የመኸር እርሻ እንዲሁም በ2ዐዐ6 የመሰኖ ልማት ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ለ

በሲዳማ ዞን ዘንድሮ ከ51 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ይለማል

Image
ሃዋሳ ጥቅምት 27/2006 በሲዳማ ዞን በዘንድሮ የበጋ ወራት ከ51 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ ። በመምሪያው የግብርና ልማት እቅድ፣ ዝግጅትና ከትትል የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ ደርቤ በትራ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የመስኖ የሚካሄደዉ በዞኑ 19 ወረዳዎች በመስመር መዝራትን ጨምሮ ሌሎች የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነው፡፡ በመስኖ ከሚለማው መሬት 9 ነጥብ አራት ሚሊዮን ኩንታል የሚደርስ የስራስር፣ የአገዳ እህሎች፣ የጥራጥሬ ሰብሎችና የተለያዩ የጓሮ አትክልት ምርት እንደሚገኝ አስታዉቀዋል ። ለዚሁ መስኖ ልማቱ 6ሺህ 491 የሞተር ፓምፖች፣ ከ2ሺህ 900 በላይ የእጅ ጉድጓድ ውሃ ።7 ሺህ 950 ምንጮችና ወንዞች በባህላዊ ዘዴ መጥለፍ ጥቅም ላይ እንደሚዉሉ ገልጠዋል ። ለመስኖ ልማቱ አገልግሎት ላይ የሚውል ከ38 ሺህ ኩንታል በላይ የቦቆሎ፣የቦሎቄ፣ አኩሪ አተርና የጓሮ አትክልት ምርጥ ዘር እንዲሁም 34 ሺህ 580ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮቹ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በመስኖ ልማቱም 230 ሺህ የሚጠጉ አርሶ አደሮች የሚሳተፉ ሲሆን ከመካከላቸዉ 30 በመቶ የሚሆኑት ሴት አርሶ አደሮች እንደሚሆኑ አስታዉቀዋል ። ዘድደሮ በመስኖ የሚለማዉ መሬት ካለፈው ዓመት በ13 ሺህ ሄክታር ፣ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀዉ ምርት ድግሞ በ3 ሚሊዮን ኩንታል ብልጫ ይኖረዋል ብለዋል ። የዞኑ አርሶ አደሮች ቀደም ሰል የዝናብ ወቅትን ጠብቀዉ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚያካሂዱት የእርሻ ስራ ዉጤታማ ባለመሆኑ የመስኖ ልማት በመጠቀም በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ በማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ቁልፍ አማራጭ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል ። እቅዱን ስኬታማ እን