ሰሞኑን በደቡብ መገናኛ ብዙሃን ሲዳማን በተመለከተ የተሰራጩ ዜናዎች
በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ በተያዘው በጀት ዓመት 48 ኪ.ሜትር የመንገድ ሥራ ለማከናወን ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የወረዳው መንገድ ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አበባየሁ በየነ እንደገለጹ በወረዳው 162 ኪ.ሜ ቀበሌን ከቀበሌ፣ ወረዳን ከወረዳ የሚያገናኝ መንገድ ለመሥራት ዕቅድ ተይዟል፡፡ በ2005 ዓ.ም 58 ኪ.ሜትር የመንገድ ሥራ በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ኘሮግራም ለመስራት ታቅዶ ወደ ሥራ የተገባ መሆኑን ተናግረው ከዚህም፣ በ3 ኪሎ ሜትር መንገድ አፈር የማልበር ስራ በ3 ኪ.ሜትር ድንጋይ የማንጠፍ ተግባር የተከናወነ ሲሆን 15.8 ሜትር በግል ተቋራጮች በኩል በተፈጠረ ክፍተት በተያዘለት ጊዜ አለመጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተሰራው የመንገድ ሥራ በገንዘብ ሲተመን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት 48 ኪ.ሜትር ቀበሌን ከቀበሌ የሚያገናኝ መንገድ ለመሥራት ዕቅድ እንደተያዘ ጠቁመው ይህ ሥራም፣ ለሴቶች፣ ለሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህ ሥራም 22 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግና ከ7 መቶ በላይ ሰዎች ያሳትፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡ ሪፖርተራችን አካሉ ጥላሁን ከበንሳ ቅርንጫፍ እንደዘገበው፡፡ በዘንድሮው የምርት ዘመን ከሁለት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት መታቀዱን የሲዳማ ዞን የሸበዲኖ የወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ በወረዳው ከሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች ፣ የቀበሌ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በ2ዐዐ5 ዓ/ም የበልግና የመኸር እርሻ እንዲሁም በ2ዐዐ6 የመሰኖ ልማት ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ለ