በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ስር የተጠቃለሉት የገጠር ቀበሌያት የልማት ያለህ እያሉ ነው፤ በቀበሌያቱ ውስጥ በባለሃብቶች የሚካሄደው የመሬት ወረራ ኣሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል
የሃዋሳ ዙሪያ የገጠር ቀበሌዎች ለከተማይቱ ቅርብ ከመሆናቸው ኣንጻር በልማት በኩል ሊያገኙ የሚገባቸውን ያህል ትኩረት ኣላገኙም። በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር በቱላ ክፍለ ከተማ ስር የተጠቃለሉት የሃዋሳ ዙሪያ የገጠር ቀበሌያት ቁጥር 14 ነው። በጊዜው የደኢህዴን ካድሬዎች ቀበሌያቱ ከሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ሰር ከተጠቃለሉ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት በመስበክ የየቀበሌያቱን ነዋሪዎች መቆሚያ እና መቀመጫ በማሳጣት ነበር እንዲጠቃለሉ የተደረጉት። በርግጥ በርካታ ሰዎች በጉዳዩ ላይ ደሰተኛ ባይሆኑም ለልማት እና ለለውጥ ጉጉ ስለነበሩ ደጋፋቸውን ከመስጠት ኣልተቆጠቡም። እንዳውም የቀበሌያቱን ከሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ስር መሆንን ኣስመልክተው ከብት ኣርደው ደግሰዋል። የሆነ ሆኖ ሰሞኑን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና የቀበሌያቱን ነዋሪዎች በማነጋገር ያሰባሰበው መረጃ እንደምያመለክተው፤ በወቅቱ የቀበሌያቱን በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር መጠቃለልን የደገፉትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በካድሬዎቹ የተገባላቸው የልማት ስራ ኣለመሰራቱን ኣመልክተዋል። በርግጥ ኣንዳንድ የልማት ስራዎች እየተሰሩ ያሉ ብሆኑም እየተሰሩ ያሉት የልማት ስራዎች በየትኛዎቹን መሰል የገጠር ቀበሌዎች እየተሰሩ ያሉ መሆናቸው ኣስራርተዋል። ኣያይዘውም የዛሬ 20 ኣመት ከዳቶኦዳሄ ( ከሃዋሳ ከተማ መግቢያ ላይ ከጥቁር ውሃ ቀጥሎ ካለው ቀበሌ ማለት ነው ) ተነስታ የውሃ ጀርካኗን ተሸክማ ከ 5 እስከ 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዛ ከሃዋሳ ከተማ ቀበሌያት ውሃ ቀድታ ለምትመለሰዋ የዳቶኦዳሄ እማወራ ኣሁንም የተለወጠ ነገር የለም ብለዋል። እንደነዋሪዎቹ ገለጻ ከሆነ፤ የቀበሌዎቹ ከከተማ ኣስተዳደር ስር መሆናቸውን ተከትሎ በተለይ ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ በርካታ ችግሮች ኣጋጥሞቸዋል። በየቀበሌያቱ ያለው መሬት ተ