Posts

የሲዳማ ዞን መንግስት ለዞኑ ቡና ነጋዴዎች የገንዘብ ብድር ሊያመቻች ይገባል ተባለ

Image
በሲዳማ ወቅቱ የቡና ነው፤ በርካታ የቡና ንግድ እንቅስቃሴ የምታይበት ጊዜ ነው። የሲዳማ ቡና ኣምራቾች በቡና ምርታቸው ገንዘብ የሚያገኙበት እና ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት የምልኩበት፤ ለቤተሰቦቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁሶች ጨምሮ ማንኛውንም ኣቅም የፈቀደውን ለማድረግ የገንዘብ ኣቅም የሚኖራቸውን ወቅት ነው። ሆኖም ኣንድችግር ኣለ ይላል የጥቻ ወራና ዘገባ፤ ይሄውም የቡና ዋና ካለፈው ኣመት ኣንጻር ስነጻጸር በመውረዱ ነው። ለቡና ዋጋ መውረድ እንደምክንያት ከምነሱት ጉዳዮ ኣንደኛው የቡና ነጋደዎች በብዛት ወደ ቡና ንግዱ ኣለመግባታቸው ሲሆን፤ ለዚህም ቢሆን ምክንያቱ ባንኮች ብድር ባለመልቀቃቸው ነው ተብሏል። እንደ ዘገባው ከሆነ፤ባንኮቹ ለሲዳማ ቡና ነጋዴዎች ብድር ለመገደባቸውም እንደምክንያት የሚያነሱት ባለፈው ኣመት ለነጋደዎቹ ያበደሯቸውን ገንዘብ በገቡት ውል መሰረት በወቅቱ ባለመመለሳቸው ነው። በዚህ በሲዳማ ውስጥ ከፍተኛ የገበያ ልውውጥ በምካሄድበት በዚህ ወቅት ባንኮች ብድር መገደባቸው እና ማዘገየታቸው ብዙዎችን ነጋዴዎችን ያዛዘነ ጉዳይ ሲሆን፤ የዞኑ መንግስት በጉዳዩ ላይ ጠልቃ በመግባት መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በዝምታ ማየቱ ኣነጋጋሪ ሆኗል። ሆኖም ሰሞኑን ባንኮች ለኣንዳንድ የቡና ነጋደዎች ትንሽ ገንዘብ ማበደራቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ብድሩን ያገኙትም በመንግስት ልማታዊ ባለሃብት የምባሉት መሆናቸው ታውቋል። ዘንድሮ ቡና ኣምራች ኣርሶ ኣደሮችን ኣንድኪሎ ቡና በስድስት ብር ከሃምሳ ሳንቲም በመሸጥ ላይ ቢሆኑም በቡና ዋና ደስተኞች ኣለመሆናቸውን በመናገር ላይ ሲሆኑ እንደምክንያት የሚያነሱትም ባለፈው ኣመት በተመሳሳይ ወቅት ኣንድ ኪሎ ቡና ከስምንት ብር እስከ ኣስራ ሁለት ብር የሸጡ በመሆኑ እና ዘንድሮ

የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ሁለተኛ ወጥቶ ተሸላሚ ሆነ

Image
ዩኒቨርሲቲው የስራ አጥነትን ችግሮች ለማቃለል መንግስት እያከናወነ ያለውን ተግበር ለማገዝ በሀገረ ሰላምና ዳሌ ወረዳ 60 ስራ አጥ ወገኖችን በንብ ማነብ ቴክኖሎጂ ስልጠና በመስጠትና የንብ ማንቢያ ዘመናዊ ቀፎዎችን በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል  በሲዳማና ጌዴኦ ዞኖች በሚገኙ የማልጋና ቡሌ ወረዳዎች አርሶ አደሩ የተሻሻለ ዝርያ ያለውን የቢራ ገብስ በማምረት ተጠቃሚ እንዲሆን አዳዳስ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ እያበረከተ ካለው አስተዋጽኦ በተጨማሪ የሚመረተው የቢራ ገብስ ገበያ እንዲያገኝ ከአሰላ ብቅል ፋብሪካ ጋር የገበያ ትስስር መፍጠሩ ተገልጸዋል ሃዋሳ ጥቅምት 22/2006 የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በማሀበረሰብ አቀፍ የምርምር ስራዎችና በሌሎች መስኮች ባከናወነው ተግባርና ባበረከተው አስተዋጽኦ በሀገር ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሁለተኛ ወጥቶ ተሸላሚ ሆነ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ባለፉት አራት ዓመታት ለተማሪዎች ተከታታይ የምዝና ስርዓት በመዘርጋቱ የተማሪዎች ውጤት መሻሻል አሳይቷል፡፡ ቀደም ሲል ዩኒቨርሲቲው በአንድ ሴሚስተር ሁለት ጊዜ ብቻ ፈተና ይሰጥ እንደነበር አስታውሰው ተግባራዊ ባደረገው የሞጁለር ትምህርት ስርዓት በሴሚስተር ከአራት በላይ ተከታታይ ፈተና በመስጠት የተማሪዎችን ዕውቀት መገምገም እንደተቻለም ጠቁመዋል፡፡ በዚህም በተለይ በከፍተኛ ደረጃ ይባረሩ የነበሩ የሴት ተማሪዎችን ቁጥር ከአንድ በመቶ በታች ዝቅ እንዲል ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በአንድ መቶ ኪሎ ሜትር ዙሪያ የሚገኘውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ማህበረሰብ አቀፍ የምርምር ስራዎችን ለማከናወን 10 የቴክኖሎጂ መንደሮችን በመከለል በግብርና፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ እንክብካቤና

ሁሉም ችግር በመንግሥት ስለማይሳበብ ኅብረተሰቡም የድርሻውን ይወጣ!

Image
ሕገ መንግሥቱን፣ የተለያዩ ሕጎችን፣ ደንቦችንና መመርያዎችን በመከተል መንግሥት ሊፈጽማቸው የሚገቡ ተግባሮችና ሊፈታቸው የሚገባ ችግሮች አሉ፡፡ የሚጠበቅበትን ባለመፈጸሙና ችግሮችን ባለመፍታቱ  ብዙ መንግሥትን ጊዜ እንወቅሳለን፡፡ አሁንም ለወደፊቱም እየተከታተልን እንጠቁማለን፣ እንወቅሳለን፡፡ መብታችንም ግዴታችንም ነውና፡፡ ነገር ግን ሁሉም ችግር ወደ መንግሥት የሚወረወርና በእሱ የሚሳበብ አይደለም፡፡ የግል ዘርፉ፣ የሚመለከታቸው አካላትና በአጠቃላይ ሕዝቡ የድርሻቸውን ባለመወጣታቸው የሚከሰቱ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ መንግሥት የድርሻውን አልተወጣም ተብሎ እንደሚወቀሰው ሁሉ፣ የግል ዘርፉም የድርሻውን ሳይጫወት ሲቀር ሊወቀስና ሊመከር ይገባዋል እንላለን፡፡ ምን ማለታችን እንደሆነ ለማሳየት በርካታ ምሳሌዎች ለመጥቀስ እንችላለን፡፡ ለጊዜው በጥቂት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ እናተኩር፡፡  1.የግሉ ዘርፍ ግብር መክፈል አለበት መብትም ግዴታም ነው በግል የሥራ ዘርፍ የተሰማራ ዜጋና የውጭ ኢንቨስተር ግብር መክፈል ያለበት ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ክፈል ስለሚል ብቻ አይደለም፡፡ ገና ከገቢዎች ጋር ግንኙነት ሳይፈጠር የሥራ ፈቃድ ሲወጣ ጀምሮ የግል ዘርፉ ግብር መክፈል እንዳለበት ያውቃል፡፡ ለማትረፍ እሠራለሁ፣ ካተረፍኩት ላይ እከፍላለሁ ብሎ ተዋውሎ ነው የሥራ ፈቃድ የሚወስደው፡፡ ስለሆነም ለምን ግብር ክፈል ተባልኩ የሚባል ነገር አይነሳም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ግብር ካልተከፈለ ልማት የለም፡፡ መንግሥት የመንገድ፣ የሆስፒታል፣ የትምህርት ቤት፣ የስልክ፣ የኤሌክትሪክ፣ የውኃ፣ ወዘተ መሠረተ ልማቶችን ማከናወን የሚችለው በቂ በጀት ሲኖረው ነው፡፡ ለበጀቱ ትልቁ ድጋፍ ደግሞ ግብር ነው፡፡ ስለሆነም የግሉ ዘርፍ ግብር ካልተከፈለ ልማት የለም ብ

በወቅታዊ የሲዳማ ዞን የፖለቲካ ኣጀንዳ፧ ሲዳማ ዞን መንግስት የሚያካህዳቸውን የልማት ስራዎች ምርጫ ተኮር ከመሆን ኣልፈው ለህዝቡ እድገት እና ብልጽግና መሆን ኣለባቸው

Image
New Photo from Internet በሲዳማ ዞን የየወረዳ ካቢኔዎች በየወረዳው የሚገኙትን ቀበሌዎች በመከፋፈል ወቅታዊ የዞኑ መንግስት ኣጀንዳ በሆነው የግብርና ስራ ላይ ከየቀበሌዎቹ ነዋሪዎች ጋር በመምክር ላይ መሆናቸው ታውቋል። በምክክሩ ላይ ኣርሶ ኣደሮቹ በ 2006 ዓም ለማምረት እና ለመስራት በሚፈልጉትን ስራ እና ምርት በማቀድ እያንዳንዳቸው በጽሁፍ እንዲያቀርቡ በመደረግ ላይ ነው ሲሆን፤ ከዚህም ባሻገር በሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በኣርሶ ኣደሮቹ ለተነሱ ጥያቄዎች በካቢኔ ኣባላት ማብራርያ እየተሰጠባቸው ነው። ካቢኔዎቹ ከኣርሶ ኣደሮቹ ጋር ባደረጉት ውይይት በባለፈው ዓመት ማለትም በ 2005 ዓም የምርት ዘመን በታዩ ድክመቶችን እና ጥንካሬዎችን የመረመሩ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ድክመቶቹን በማረም ጥንካሬዎችን የበለጠ በማጠናከር በምቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥተዋል ተብሏል። በውይይቱ ላይ ካቢኔዎቹ እንዳሉት ከሆነ፤ የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮች በእጃቸው ያለው ሃብት መሬት፤ የሰው ኃይል እና ውሃ በመሆኑ እነዚህን በማቀናጄት የበለጠ ምርታማነትን ማረጋገጥ ይቻላል። በምቀጥሉት የበጋ ወራት የግብርና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ልደርሱ የምችሉ የግብርና ምርቶችን እንዲያመርቱ የምደረግ ሲሆን፤ ለዚህም ውሃ ከማሳቸው ኣጠገብ ያላቸው ኣርሶ ኣደሮች ከዚሁ የውሃ ሀብት እንዲጠቀሙ፧ ውሃ ከማሳቸው ኣጠገብ የሌላቸው ደግሞ የውሃ ጉርጓድ እንድቆፍሩ መክረዋል። ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና በወቅታዊው የሲዳማ ፖለቲካ ላይ ያናገራቸው ስማቸውን እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሲዳማ ፖለቲካ ተንታኝ የካቢኔዎቹ የልማት ዘማቻ ድብቅ ኣጀንዳ ያጋለጡ ሲሆን፤ የሲዳማን ኣርሶ ኣደሮች ምርታማነትን ለማሳደግ ካቢኔዎቹ በማድረግ ላይ ካሉት እንቅስ

ካላ ደሴ ዳልኬ በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ ኣባያ ቢሳሬ ቀበሌ ነዋሪ በሆኑ የሲዳማ ተወላጆች ላይ በኣከባቢው ነዋሪዎች የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዲቆሙ ትዕዛዝ ሰጡ

Image
ካላ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ከኣንድ ወር በፊት በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ ኣባያ ቢሳሬ ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የሲዳማ ተወላጆች ላይ በኣከባቢው ነዋሪዎች የተለያዩ ወንጀሎች እንደተፈጸሙባቸው እና ቤት ንብረታቸውን በእነዚሁ ሰዎች መቃጠሉን ብሎም ኣከባቢውን በኣስቸኳይ እንዲለቁ በምል የማስፈራሪያ ዛቻ እንደደረሳቸው በቪድዮ የተደገፈ መረጃ በማቅረብ የሲዳማ ዞን መንግስት እና የቦርቻ ወረዳ ኣስተዳደር መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጥሪ ማቅረባችን ይታወሳል። በጉዳዩ ላይ ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ታማኝ ምንጭ ጠቅሶ ከሃዋሳ እንደዘገበው፤ እነዚሁ በቤትንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የሲዳማ ተወላጆች 18 ተወካዮችን መርጠው ወደ ሃዋሳ በመላክ ለደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ለካላ ደሴ ዳልኬ ኣቤቶታ ኣቅርበዋል። የተጎጂዎቹን ተወካዮች በቢሮቸው ተቀብለው ያነጋገሩት የክልሉ ፕሬዚዳንት ካላ ደሴ፤ በኣስቸኳይ ጉዳይ ኣጣሪ ቡድን በመሰዬም እና ቡድኑን ወደ ቀበሌው በመላክ የወንጀሉ መፈጸም ኣለመፈጸም እንድጣራ ማድረጋቸው ታውቋል። ኣጣሪ ቡድኑ ባቀረበው ሪፖርት በሲዳማ ተወላጆች ላይ ወንጀል መፈጽሙን በማረጋገጡ፤ ካላ ደሴ ዳልኬ በኣከባቢው ነዋሪዎች የወደሙ ቤቶች እንድገነቡ እና በኣከባቢው ተወላጆች በሲዳማዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በኣስቸኳን እንዲቆሙ ትዕዛዝ መስጠታቸው ተገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት በኣከባቢው ያለውን ችግር የመፍታት ስራ በመሰራት ላይ ሲሆን፤ ህዝቡም በመረጋጋት ላይ ነው ተብሏል። ኣዲሱ የክልሉ ፕሬዚዳንት ካላ ደሴ ዳልኬ ተጎጂዎቹ ያቀረቡትን ኣቤቶታ በመስማት እና በኣስቸኳይ መፍትሄ በማፈላለግ ሀላፊነታቸውን በመወጣታቸው እና ለተጎጂ የሲዳማ ተወላጆች ኣጋሪነታቸውን በማሳየታቸው መደሰታቸውን