የቀድሞው የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ተፈሪ ፍቅሬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 19 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ተፈሪ ፍቅሬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተከሳሹ የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ከ2002 እስከ 2005 ዓመተ ምህረት ያገለገሉት አቶ ተፈሪ ፍቅሬ የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና አቃቢ ህግ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ክስ መስርቶባቸዋል ። በግለሰቡ ላይ የተከፈተው የክስ መዝገብ ተከሳሹ የተሰጣቸውን የመንግስት ሃላፊነት ያለአግባብ ተጠቅመው የማይገባ ጥቅም ለማግኘትና ለሌሎች ለማስገኘት በማሰብ ፤ በቀድሞው ወረዳ 23 ቀበሌ 12 በውጭ ምንዛሬ ተከራይቶ የነበረውን የቤት ቁጥር 106 የመንግስት ቤት ለኢትዮጵያውያን እንዲከራይ ግምት እንዲሰራ በታዘዘው መሰረት በባለሙያዎች 1 ሺህ 998 ብር ተመን ከወጣለት በኋላ ፤ የኤጀንሲውን የተለመደ አሰራር በመጣስና የባለሙያዎችን የኪራይ ግምት ውድቅ በማድረግ ለአንዲት ግለሰብ ተመኑን ቀንሰው አከራይተዋል። በዚህም ከ2002 እስከ 2005 ዓመተ ምህረት መንግስት ከቤቱ ማግኘት የነበረበትን 17 ሺህ 420 ብር በማሳጣትና በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰው ተከራይን ያለአግባብ ተጠቃሚ አድርገዋል ይላል ። በቀድሞው ወረዳ 21 ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር 112/40 የሆነውን የመንግስት መኖሪያ ቤት ባሰፋ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት፥ ለመኖሪያነት አገልግሎት በጨረታ አሸንፎ 7 ሺህ 650 ብር እየከፈለ ይኖርበት የነበረውን ቤት፤ ተከሳሹ ከተከራይ ድርጅቱ ጋር በመመሳጠር ቤቱ ለመኖሪያ ቤትነት እንደተሰጠ እየታወቀ ለስራ አልተመቸኝም በማለት እንዲያመለክቱ አድርገው ፤ የኤጀንሲውን መመሪያ ወደጎን በመተው በዚ