Posts

በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ተሳታፊ የሆኑት የሲዳማ እግር ኳስ ክለቦች በመጀመሪያ ጫዋታዎቻቸው ሽንፈት ኣስተናግደዋል

Image
New በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ተሳታፊ የሆኑት የሲዳማ ቡና እና ሃዋሳ ከነማ የእግር ኳስ ክለቦች በመጀመሪያ ጫዋታዎቻቸው ሽንፈት ኣስተናግደዋል። በትናንትናው እለት መከላከያን የገጠመው የሲዳማ ቡና 3 ለ 1 የተሸነፈ ሲሆን ሃዋሳ ከነማ በበኩሉ መብራት ኃይልን ገጥሞ 2 ለ1 ተሸንፏል። ሁለቱም  የሲዳማ ክለቦች የዘንድሮውን ፕሪሚዬር ሊግ በሽንፈት መጀመራቸው ለኣመቱ ውድድር ያደረጉት ዝግጅት ጥንካሬን በተመለከተ በኣንዳንድ የክለቦቹ ደጋፊዎች ዘንድ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው ኣድርጓል። በምቀጥሉት ጫዋታዎች ኣቋማቸውን ኣስተካክለው ነጥብ እንደምሰበስቡ እና ወደ ቀድሞ ጥንካሬያቸው እንደምመለሱ ይጠበቃል። 

የባለፈው ኣመት የሲዳማ ብሎም የኣገሪቱ የቡና ኤክስፖርት ምን ይመስል ነበር

Image
Price Discrepancy Stunts Coffee Exports For over four years now, the headquarters of the Ethiopian Commodity Exchange (ECX), located in the Chelelk-Alsam Tower on Chad Street, has shone with the price ticker board displaying the country is own commodity prices. The prices displayed on the ticker board which is wrapped around the waist of the building appear in green, yellow and red, respectively indicating increases, stability or plunges. The prices for different varieties of coffee, however, which take up most of the space on the board, are, drawing a lot of frustration from exporters these days. They say it does not reflect international market conditions. Whereas the board was initially intended to help the traders in price discovery, that, say traders, is no longer the case. One such exporter is Adem Kedir, for whom coffee trading is not just a business, but a family heritage in which his father and brothers are also employed. After starting out helping in his father’s

የፍቼ ጫምባላላ በዓል የሲዳማ ብቻ ሳይሆን የዓለም ቅርስ ሊሆን ይገባል፤

Image
የሲዳማ ዞን ከምድር ወገብ በስተሰሜን አካባቢ ይገኛል። በሰሜናዊ ምስራቅና በደቡባዊ ምስራቅ የኦሮሚያ ክልል በደቡብ ጌዲኦ ዞንና የኦሮሚያ ክልል፣ በምእራብ በኩል ደግሞ የወላይታ ዞን ያዋስኑታል። ዞኑ በሶስት የአየር ንብረቶች የሚካተት ሲሆን  30 በመቶ ደጋ፣  60  በመቶ ወይና ደጋ፣ 10  በመቶ በቆላ ይሸፈናል። የዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት  7 ሺ  200  ካሬ ኪሎ ሜትር ሲሆን በ 19  የገጠር ወረዳዎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተዋቀረ ነው። በ 1999  ዓ . ም በተካሄደው የህዝብና የቤቶች ቆጠራ መሰረት በዞኑ የሚገኘው የሲዳማ ህዝብ ብዛት  3 ነጥብ 2 ሚሊዮን እንደሚሆን ተገምቷል። የሲዳማ ብሄር በሰሜናዊ ምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል ተጠቃሽ ሲሆን በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ነው። የሲዳማ ብሄር የራሱ የሆነ የጊዜ አቆጣጠር ቀመር ያለው ሲሆን ቀመሩን ተከትሎ የፍቼ የዘመን መለወጫ በዓል በድምቅት ይከበራል። የፍቼ በዓል የሚከበርበትን ቀን  « አያንቶ » ( የተመረጡ አዛውንቶች )  ክዋክብት በጨረቃ ዙሪያ የሚያደርጉትን ኡደት በመቃኘት ይወስናሉ። በጎሳ መሪው  ( ሞቴው )  ውሳኔ መሰረት የበዓሉ ቀን ከታወጀ በኋላ ሁሉም በየፊናው ዝግጅቱን ያጧጡፋል። በዓሉም እስከ ሁለት ሳምንታት ለሚደርስ ጊዜ በየአካባቢው በሚገኙ  « ጉዱማይሌዎች » ( አደባባዮች )  በድምቀት ይከበራል። ጉዱማይሌ በዞኑ በሚገኙ መንደራት ሁሉ የሚገኝ ሲሆን ትልቅ ክብር የሚሰጠው ቦታ ነው። አራስ የመታረሻ ጊዜዋ አብቅቶ ከመውጣቷ በፊት ከልጇ ጋር በቅድሚያ የምታየው ጉዱማይሌውን ነው። ሙሽሮች ከሰርጋቸው ማግስት ጀምሮ ጉዱማይሌን ሳያዩ ወደአዲሱ ኑሯቸው አይቀላቀሉም። የሲዳማ ብሄር ተወላጆች እንደየእድሜያቸውና በ

ሥራችሁም እንደ አፋችሁ ይሁን!

Image
የሕገ መንግሥቱን የበላይነት በሚመለከት ሰሞኑን ጠቃሚና ዓበይት ቃላት ከባለሥልጣናት አንደበት ሲነገሩ እየተደመጡ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ኢሕአዴግና የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ሕገ መንግሥቱን በማክበር አርዓያ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡ ፓርላማውም ይህን መቆጣጠር አለበት በማለት በአፅንኦት ሲገልጹ ተደምጠዋል፡፡  የመንግሥት መሪና ሥልጣን የያዘው ገዥ ፓርቲ ሊቀመንበር እንደመሆናቸው መጠን፣ እንደ ፓርቲም እንደ መንግሥትም ሕገ መንግሥቱን እናክብር ቁጥጥር ሊደረግብንም ይገባል ማለታቸው ጎሽ! የሚያሰኝ ነው፡፡  የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳም ተመሳሳይ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡ ፓርላማው ሕገ መንግሥቱ መከበሩን ሊቆጣጠር ይገባል ብለዋል፡፡ ኢሕአዴግ እንደ ገዥ ፓርቲና እንደ መንግሥት መሪ በአርዓያነት ሕገ መንግሥቱን ሊተገብር ይገባል፣ ለሕጎች ተገዥ መሆን አለበት፡፡ ይህንን በተግባር ለመተርጎም የሚያዳግተው አይሆንም፣ አርዓያም ይሁን በማለት በአፅንኦት ገልጸዋል፡፡  የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃንም በቅርቡ ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ልዩ ስብሰባ እንዲዘጋጅ በማድረግ ለሁለት ቀናት በተደረገ ውይይት በአፅንኦት ያነሱት ጉዳይ አለ፡፡ መገናኛ ብዙኃን ስለሕገ መንግሥቱ ኅብረተሰቡን ማስተማር እንዳለባቸውና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ መንግሥቱን የማስተግበር የበላይ ኃላፊነት የተሰጠው ስለሆነ፣ በቅርብ እየተገናኙ ስህተትንና ጉድለትን እያሳዩ ሥራቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል፡፡ በተግባር ሥራ ላይ ያልዋለ ሕገ መንግሥት ሊያስከትለው የሚችለውን አደጋም አስረድተዋል፡፡ በአጭሩ  ሲታይ ከመንግሥት መሪ፣ ከገዥው ፓርቲ ኃላፊ፣ ከተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔና ከፌዴሬሽን ምክር አፈ ጉባዔ ሕገ መን

ጥቂት ስለ ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ

Image
ሲዳማ ቡና  ሙሉ ስም ፡  ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ  ምስረታ ፡  1999 ስታዲየም ፡   ይርጋለም ስታዲየም  ሀዋሳ ስታዲየም የክለቡ የወቅቱ አሰልጣኝ ፡  ታረቀኝ አሰፋ   ዳኜ ክለቡ ያገኛቸው ክብሮች ፡  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ ሻምፒዮን 2001 ሲዳማ ቡና በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ እየተሳተፈ ያለ ክለብ ነው፡፡ ክለቡ ከተመሰረተ ጥቂት አመታት ብቻ ቢቆጠሩም በብሔራዊ ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ በፕሚየርሊጉም ጥሩ ተፎካካሪ እየሆነ ይገኛል፡፡ ምስረታ  ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የተመሰረተው በ 1999 ዓ/ም ነበር በደቡብ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ላይ ሲዳማ ዞንን በመወከል ሥስት ክለቦች ይሳተፋሉ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ዳራ ከነማ ነበር፡፡ ዳራ በውድድሩ ለፍፃሜ በመድረስ ውጤታማ ይሆናል፡፡ ይህም ክልሉን በመወከል ሀዋሳ ላይ ወደተካሄደው የኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከተሳተፉ አራት ቡድኖች አንዱ ለመሆን አበቃው፡፡ በዚህ ውድድር ቀዳሚዎቹን አራት ደረጃዎች የሚይዙ ቡድኖች ወደ ብሔራዊ ሊግ ሲያልፉ ዳራም ሦስተኛ ደረጃን አግኝቶ ስለነበር ብሔራዊ ሊጉን ተቀላቀለ፡፡ እናም ዳራ ከተማን ብቻ ይወክል የነበረው ክለብ መላውን የሲዳማ ዞንን እንዲወከል በማሰብ ሲዳማ የሚለውን ስያሜ አገኘ፡፡ ሲዳማ ቡና በብሔራዊ ሊግ ሲዳማ ቡና ሁለት አመት በብሔራዊ ሊግ አሳልፏል፡፡ በመጀመሪያው አመት ቆይታው በ 2000 አራተኛ ደረጃን ይዞ ነው ያጠናቀቀው፡፡ በሁለተኛው አመት 2001 ውድድሩ በሁለት ምድብ ተከፍሎ ሲካሔድ በምድብ ሁለት የነበረው ሲዳማ በመጨረሻው ጨዋታ ከአየር ሀይል ጋር ያለ ግብ በመለያየት ከምድቡ ከሜታ አቦ ቢራ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡ በዚህ ጨዋታ ቢሸነፍ ኖሮ ይህን ደረጃ አያገኝም፡፡ በቀጣይ