ጥቂት ስለ ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ
ሲዳማ ቡና ሙሉ ስም ፡ ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ምስረታ ፡ 1999 ስታዲየም ፡ ይርጋለም ስታዲየም ሀዋሳ ስታዲየም የክለቡ የወቅቱ አሰልጣኝ ፡ ታረቀኝ አሰፋ ዳኜ ክለቡ ያገኛቸው ክብሮች ፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ ሻምፒዮን 2001 ሲዳማ ቡና በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ እየተሳተፈ ያለ ክለብ ነው፡፡ ክለቡ ከተመሰረተ ጥቂት አመታት ብቻ ቢቆጠሩም በብሔራዊ ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ በፕሚየርሊጉም ጥሩ ተፎካካሪ እየሆነ ይገኛል፡፡ ምስረታ ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የተመሰረተው በ 1999 ዓ/ም ነበር በደቡብ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ላይ ሲዳማ ዞንን በመወከል ሥስት ክለቦች ይሳተፋሉ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ዳራ ከነማ ነበር፡፡ ዳራ በውድድሩ ለፍፃሜ በመድረስ ውጤታማ ይሆናል፡፡ ይህም ክልሉን በመወከል ሀዋሳ ላይ ወደተካሄደው የኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከተሳተፉ አራት ቡድኖች አንዱ ለመሆን አበቃው፡፡ በዚህ ውድድር ቀዳሚዎቹን አራት ደረጃዎች የሚይዙ ቡድኖች ወደ ብሔራዊ ሊግ ሲያልፉ ዳራም ሦስተኛ ደረጃን አግኝቶ ስለነበር ብሔራዊ ሊጉን ተቀላቀለ፡፡ እናም ዳራ ከተማን ብቻ ይወክል የነበረው ክለብ መላውን የሲዳማ ዞንን እንዲወከል በማሰብ ሲዳማ የሚለውን ስያሜ አገኘ፡፡ ሲዳማ ቡና በብሔራዊ ሊግ ሲዳማ ቡና ሁለት አመት በብሔራዊ ሊግ አሳልፏል፡፡ በመጀመሪያው አመት ቆይታው በ 2000 አራተኛ ደረጃን ይዞ ነው ያጠናቀቀው፡፡ በሁለተኛው አመት 2001 ውድድሩ በሁለት ምድብ ተከፍሎ ሲካሔድ በምድብ ሁለት የነበረው ሲዳማ በመጨረሻው ጨዋታ ከአየር ሀይል ጋር ያለ ግብ በመለያየት ከምድቡ ከሜታ አቦ ቢራ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡ በዚህ ጨዋታ ቢሸነፍ ኖሮ ይህን ደረጃ አያገኝም፡፡ በቀጣይ