ከቱሪስት ከተማነት እስከ ታላላቅ የስፖርት ውድድሮች መናኸሪያነት_ሀዋሳ
ከሃምሳ ዓመት በላይ ያስቆጠረችው የደቡብ ክልል መዲና ሐዋሳ ከኢትዮጵያ ከተሞች በቁንጅናዋ፣ በዕቅድ ከመከተሟም ጋር ተዛምዶ ለብዙ ነገር ትመረጣለች፡፡ ከቱሪስት ከተማነት እስከ ታላላቅ የስፖርት ውድድሮች መናኸሪያነት ትታጫለች፡፡ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሐዋሳ ስሙን መትከል የፈለገው በቢዝነስ ሥራ ብቻ አይደለም፡፡ በታላቁ ሩጫ ዓመት ጠብቆ የሚጐበኛትን የደቡብ መናገሻ፣ አሁን ደግሞ ለአገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን ማራቶን መሽቀዳደሚያ አውራና ተመራጭ አድርጓታል፡፡ ኃይሌ በሐዋሳ ያልተለመደውንና በስሙ የተሰየመውን የማራቶን ውድድር በከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት አንበሽብሾታል፡፡ በሁለቱም ጾታ አሸናፊዎቹ እያንዳንዳቸው የ100 ሺሕ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ የመጀመሪያው ‹‹ኃይሌ ማራቶን›› ጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. በደቡቧ መናገሻ ሐዋሳ እንደሚደረግ ይፋ በሆነ በጥቂት ወራት ከ16 አገሮች ከ200 በላይ ተሳታፊዎች በውድድሩ ለመሳተፍ ቅድመ ምዝገባ ማከናወናቸውን የገለፀው ዝግጅት ክፍሉ፣ በሚቀጥለው ዓመት ከተወዳዳሪ ቁጥር ጀምሮ የተሻለና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ አበረታች ተሞክሮ ተገኝቷል ብሏል፡፡ በአገሪቱ ለታላላቅ አትሌቶች መገናኛ እንደሆነ የሚነገርለት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣ በ10 ሺሕ ተሳታፊዎች ጀምሮ በአሁኑ ወቅት በተመሳሳይ የሩጫ ውድድሮች ከዓለም ምርጥ አሥሩ አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡ ዘንድሮም 37 ሺሕ ተሳታፊዎች ለማወዳደር ዝግጅቱን አጠናቆ እንደሚገኝ መገለጹ ይታወሳል፡፡ ውድድሩ ከአዲስ አበባ አልፎ በመላ አገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ተወዳጅና ተናፋቂ እስከመሆን ደርሷል፡፡ 42 ኪሎ ሜትር 195 ሜትር የሚሸፍነው ማራቶን በአውሮፓና በሌሎች ታላላቅ አገሮች ካልሆነ እንዲህ እንደ አሁኑ በኢትዮጵያ ይደረጋል