ሳውዝ ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል-የሀዋሳ ፈርጥ
ለግንባታው 246 ሚ. ብር ወጥቷል የኦሎምክፒክ ደረጃ ያለው መዋኛ፣ ሲኒማ ቤቶች፣ ናይት ክለብ … ይገነባሉ 8 ሰዎች የሚይዘው ጃኩዚ ውሃ የማያበላሸው LCD ቲቪ አለው ሳውዝ ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል በደቡብ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ 275 ኪ.ሜ ላይ በሀዋሳ ከተማ ተገንብቶ በቅርቡ ሥራ የጀመረ አዲስ ዘመናዊ ሆቴል ነው፡፡ “ሀዋሳ፣ የቱሪስት መዳረሻ እየሆነች ነው፡፡ የውጭ አገርና የአገር ውስጥ ቱሪስቶች፣ በግል፣ በቡድን፣ በቤተሰብ የሚመጡባት ከተማ ሆናለች፡፡ እንግዶቻችን ሲመጡ የሚያርፉበት ብቻ ሳይሆን፣ በቆይታቸው የሚዝናኑበትና የተሟላ ምቾት የሚያገኙበት ዘመናዊ ሆቴል አዘጋጅተን እየጠበቅናቸው ነው” ይላሉ፤ የሳውዝ ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤት ተወካይ አቶ መኳንንት አሰፋ፡፡ “በአካባቢያችን ከሚገኙ ሆቴሎች የምንለይበት ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ 4 ባር እና 4 ሬስቶራንቶች የተለያየ መጠቀሚያ ዕቃዎችና (ፋሲሊቲ) ዋጋ ያላቸው 5 ዓይነት መኝታ ክፍሎች፣ … አሉን፡፡ ስለዚህ እንግዳው ሳውዝ ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል ገባ ማለት፣ በፈለገው ቦታ፣ በፈለገው ሁኔታ መዝናናት፣ በፈለገው ደረጃና ዋጋ ክፍሎችን መያዝ ይችላል፡፡ “ለምሳሌ ስታንዳርድ፣ ትዊን፣ ፋሚሊ፣ ዴሉክስ፣ ኤግዚኩቲቭ ዴሉክስ ሱት ቤድሩም፣ የተሰኙ ክፍሎች አሉን፡፡ እንግዳው እንደአቅሙ መከራየት እንዲችል አማራጮች ቀርበውለታል፡፡ ከቁርስ እስከ እራት የሚስተናገድበት ኦል ዴይ ሬስቶራንት አለ፡፡ በቡድን (ግሩፕ) የሚመጡ ሰዎች እየተወያዩ ምሳም ሆነ እራት የሚበሉበት ፕራይቬት ዳይንግ ሩም፣ ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ በተገኘባት ስፍራ ማንኪራ የተሰየመ ማንኪራ ጋርደን ካፌ፣ አናት (ቴራስ) ላይ እስከ 200 ሰዎች መያዝ የሚችል ሬስቶራንት አለን፡፡ “አራተኛ ፎቅ ላይ ታቦር ተራራን፣ ቅ