Posts

ስለ ኢትዮጵያ ብሮድካስተር ምን ያህል ያውቃሉ? ኣንጋፋው ሬድዮ ሲዳማ በኣገሪቱ የማህበረሰብ ሬድዮ ዝርዝር ውስጥ ኣልተካተተም፤ ምስጥሩ ምን ይሁን?

Image
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ባወጣው የኣገሪቱ የብሮድካስቲንግ ሚዲያ ዝርዝር ውስጥ 16 የማህበረሰብ ሬድዮዎች የተካተቱ ሲሆን፤ በኣገሪቱ የማህበረሰብ ሬድዮ ስርጭት በመጀመር በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ቀዳሚ የሆነው ሬድዮ ሲዳማ በዝርዝሩ ውስጥ ኣልተካተተም። ሬድዮ ሲዳማ፤ እኣኣ በ1990 ዎቹ ላይ በኣይሪሽ መንግስት ድጋፍ በይርጋኣለም ከተማ በቀድሞው ፉራ የልማት ምርምር ማዕከል ውስጥ በ954 ኪሎሄርዝ መካከለኛ ሞገድ ስርጭት መጀመሩ የሚታወስ ነው። ሬድዮ ጣቢያው ከስኞ እስከ ኣርብ በኣብዘኛው የትምህርት ፕሮግራሞችን የምያስተላልፍ ሲሆን፤ ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ኣየር ላይ ያውላል። ሬድዮ ሲዳማ የሲዳማን ባህል እና ቋንቋ በማሳደግ በኩል ከፍተኛ ሚና ያለው ሲሆን፤ ከኣራት እስከ ስድስት ሚሊዮን ለሚቆጠረው የሲዳማ ህዝብ በቋንቋው ባህሉ የተተረከለት፤ የተዘፈነለት፤ በቋንቋው ድራማ የመሳሰሉ የሰነ ጥበብ ስራዎች የተሰሩለት ብሎም በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮቹ ላይ በቋንቋው እንድወያይ እድል የተከፈተለት በሬድዮ ሲዳማ ነው። ጣቢያውን በባለበትነት ያስተዳድር የነበረው የቀድሞው የሲዳማ ልማት ፕሮግራም በኃላ ላይ ደግሞ የሲዳማ ልማት ኮፔሬሽን በመንግስት ጠልቃ ገብነት በሲዳማ ያካህዳቸው የነበሩት የልማት ስራዎች ሲቋረጥ፤ ሬድዮ  ሲዳማ የባጄት ችግር ኣጋጥሞት ያስተላልፋቸው የነበሩትን ፕሮግራሞች በኣግባቡ ማስተላለፍ ኣለመቻሉ ይታወሳል። በወቅቱ ፕሮግራሞችን በመደጋገም ኣድማጮችን እስከ ማሰልቸት ደርሶ ነበር። በኃላ ላይ ሬድዮ ጣቢያው በሲዳማ ዞን ትምህርት መምሪያ ስር የሆነ  ሲሆን እስከ ኣሁን ድረስ የቀድሞ ዝናውን በሲዳማ ህዝብ ዘንድ መመለስ ኣልቻለም።  የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ወደፊት በሬድ

የዝናብ ስርጭቱ በጥቅምትና ህዳር ወር የመከሰት እድሉ ሰፊ በመሆኑ የሲዳማ አርሶ አደር ጥንቃቄ ያድርግ

አዲስ አበባ መስከረም 30/2006 በመላው አገሪቱ ሰሞኑን እየታየ ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ የዝናብ ስርጭት እየቀነሰ ቢሆንም በጥቅምትና ህዳር ወር የመከሰት እድሉ ሰፊ በመሆኑ አርሶ አደሩ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አሳሰበ። ኤጀንሲው እንዳለው ከመስከረም 20 ቀን ጀምሮ አብዛኛውን የሃገሪቱን ክፍል የሸፈነ የዝናብ ስርጭት እምብዛም ያልተለመደ ነው። በቀጣይም እንደባለፈው ሳምንት የተስፋፋ ዝናብ ባይጠበቅም በአንዳንድ አካባቢዎች ያልተጠበቀ ዝናብ ሊከሰት ስለሚችል የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰብ ረገድ አርሶ አደሩ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል። የኤጀንሲው የሚቲዎሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክተር አቶ ድሪባ ቆሪቻ በተለይ ለኢትዮጰያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት በመላው አገሪቱ ባለፉት ዘጠኝ ቀናት ከባድ የሚባል የዝናብ መጠን ተመዝግቧል። በተለይም በአማራ ፣ ኦሮሚያ ፣ ደቡብና ሃረሪ ክልሎች እንዲሁም በሶማሌ ክልል ሰሜናዊ አጋማሽ ድሬዳዋን ጨምሮ ይህ ያልተለመደ ዝናብ ያለማቋረጥ መዝነቡን ተናግረዋል። የአማራ መካከለኛው ምስራቅ፣ ደቡብ ኦሮሚያ እና የደቡብ ክልል ሰሜናዊ አጋማሽ ከበድ ያለ ዝናብን ያስተናገዱ አካባቢዎች እንደነበሩ አስታውቀዋል። በእነዚህ አካባቢዎች በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ከ40 እስከ 80 ሚሊ ሜትር ዝናብ መመዝገቡን ገልጸዋል። የወቅቱ ዝናብ ዘግይተው ለተዘሩ ሰብሎች ጥቅም እንደሚኖረው አቶ ድሪባ ተናግረው እርጥበቱ በተለይ ሽምብራና ምስር የመሳሰሉትን እህሎች ቶሎ ለመሰብሰብ ከማገዝ ባለፈ በቂ የእንስሳት መኖ እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል። በቆላም አካባቢ ለሚገኙ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ለመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ለግጦሽ የሚሆን ሳር ለማግኘት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አቶ ድሪባ ተናግረዋል። በተጨማሪ በተለያዩ የአገ

ዋሊያዎቹ በሁሉም ረገድ መዘጋጀታቸው ተገለጸ

የእግር ኳስ ቤተሰቡም ሆነ ሙያተኞች በዋሊያዎቹ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላትም ተመሳሳይ ስሜት አላቸው፡፡ ከተጨዋቾቹ አንዳንዶቹ ለናይጀሪያውያን ተገቢውን ክብር እንደሚሰጡ፣ ነገር ግን ደግሞ የመጀመሪያውን ጨዋታ በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት ማድረጋቸው ጨዋታውን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ አቅሙም ብቃቱም እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡  እሑድ ጥቅምት 3 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም ስለሚደረገው የኢትዮጵያና ናይጀሪያ ግጥሚያ የታላላቅ መገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ስቧል፡፡ ናይጀሪያውያን ከዋሊያዎቹ ጠንካራ ፉክክር እንደሚጠብቃቸውም እየተዘገበ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ አቶ ሰውነት ቢሻው፣ ቡድናቸው እዚህ የደረሰው እጅግ ብዙ ፈታኝ ወቅቶችን አልፎ በመሆኑ ወደፊትም ይህ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ይገልጻሉ፡፡ ለእሑዱ ጨዋታም ቢሆንም ተጨዋቾቻቸው በሥነ ልቦናውም ሆነ በአካል ብቃቱ ዝግጁ ስለመሆናቸው በተደጋጋሚ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡  ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ለደቡብ አፍሪካው ዊትስ ከሚጫወተው ጌታነህ ከበደ ውጪ አዲስ ሕንፃ፣ ሽመልስ በቀለና ሳላዲን ሰይድ ዋሊያዎቹን እንደተቀላቀሉ ተነግሯል፡፡ የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የእግር ኳስ ቤተሰቦች በበኩላቸው፣ በዋሊያዎቹ የፀና እምነት እንዳላቸው ገልጸው ‹‹ሥጋታችን›› ሲሉ የተናገሩት፣ በአዲስ አበባ ስታዲየም ታድመው ጨዋታውን መከታተል ይችሉ ዘንድ የትኬት አሻሻጡን በተመለከተ ነው፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ካለፈው ስህተቱ እርምት ወስዶ የትኬት መሸጪያ መስኮቶች በጊዜ እንዲከፈቱና ተመልካቹም በጊዜ ትኬቱን ገዝቶ ከአላስፈላጊ መጉላላት እንዲታደጋቸው ጠይቀዋል፡፡  ምንጭ፦  http://www.et

ዩኤን ኤድስ 2030 የኤድስ ማብቂያ ሊሆን ይችላል አለ

የተባበሩት መንግስታት የኤድስ ድርጅት (UNAIDS) ከቀናት በፊት የለቀቀው ሪፖርት እ.ኤ.አ በ2030 ኤችአይቪ ኤድስ በቁጥጥር ስር ሊውል የሚችልበት ዕድል መኖሩን አስታውቋል፡፡ ሪፖርቱ እንደሚያሳየው በህጻናትና አዋቂዎች አዳዲስ የኤችአይቪ ኢንፌክሽኖች ከ2001 ወዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንድ ሶስተኛ ቀንሰዋል፡፡  ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኤችአይቪ የተያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር 2.3 ሚሊዮን ሲሆን ይህ በ2001 ከታየው አዳዲስ ኢንፌክሽን 33 በመቶ መቀነሱን ያሳያል፡፡ በዚሁ ዓመት በቫይረሱ የተያዙ ህጻናት ቁጥር 260 ሺህ ሲሆን ከ2001 ጋር ሲነጻጸር የ52 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ የአዳዲስ ኢንፌክሽኖች ቁጥር የቀነሰው በስፋት እንዲዳረስ በተደረገው በፀረ-ኤችአይቪ መድሃኒት ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡  የፀረኤችአይቪ መድሃኒት ተደራሽነት ከ2005 ወዲህ በኤችአይቪ ምክንያት የሚደርስ ህልፈተ ህይወትም 30 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል፡፡  ከ2011 እስክ 2012 ባለው ጊዜ ውስጥ 20 በመቶ ለሚሆኑት ሰዎች (9.7 ሚሊዮን) ፀረኤችአይቪ መድሃኒት ተደራሽ መሆኑን የዩኤን ኤድስ ዳይሬክተር ሚሼል ሲዲቤ ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱ በ2015፤ 15 ሚሊዮን ሰዎችን የፀረ-ኤችአይቪ ተጠቃሚ ለማድረግ ግብ እንዳለው ይታወቃል፡፡ በሪፖርቱ እንደተመለከተው በ2012 ዓለም ላይ ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች ቁጥር 35.3 ሚሊዮን ነበር፡፡  ከኤችአይቪ ህክምና ጋር በተያያዘ የታዩ ዘርፈ ብዙ ለውጦችን መሠረት በማድረግ የዩኤን ኤድስ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሉዊስ ሎሬስ የኤችአይቪ ኤድስ ማብቂያ ከ2030 በፊት እንደሚሆን ግምታቸውን መስጠታቸውንም የተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡  ‹‹የኤችአይቪ ወረ

Ethiopia To Strengthen Cooperation With Foreign Universities - The delegation of university officials from the U.S. has visited Hawassa University

ADDIS ABABA, Oct 11 (BERNAMA-NNN-ENA) -- Ethiopia will strengthen cooperation with foreign universities as part of efforts to to build the country's human resource, says Minister of Foreign Affairs Dr. Tedros Adhanom. At a meeting here Thursday with a visiting delegation of university officials from the U.S. , he said such cooperation could contribute to the efforts of the country towards human resource development. The government is striving to produce skilled human resources with a view to attain the goals set out in the country's Growth and Transformation Plan, he said. Dr. Tedros added that it was important for Ethiopia to establish a partnership with U.S. universities specialising in science and technology to develop its human resource as science and technology is a priority in Ethiopia's higher education. Delegation leader Tibor P.agy, who is Vice-Provost for International Affairs at Texas Tech University, said universities in the U.S. wished to further strengthen co