‹‹በኢሕአዴግ ውስጥ መከፋፈል አለ የተባለው ምኞት ነው›› ተባለ
-የሃይማኖት አክራሪነት ትግል ፖለቲካዊ ነው አሉ -የተቃዋሚዎች የሰላማዊ ሠልፍ ጥያቄ ከቀጠለ እንደሚቆም ገለጹ -በኬንያ የደረሰው ጥቃት በኢትዮጵያ ላይ እንደደረሰ ይሰማናል ብለዋል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሕልፈት ተከትሎ በ2005 ዓ.ም. መስከረም ወር ላይ በይፋ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሾሙት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥልጣን ቆይታ አንድ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ የአንድ ዓመት የሥልጣን ቆይታቸው ከተቆጠረ ሁለት ሳምንታት በኋላ ባለፈው ዓርብ ለአገር ውስጥና ለውጭ የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ይህ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ወደ ሥልጣን የመጡበትን አንደኛ ዓመት ለማስታወስ ባይሆንም፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ እንዲሁም በአኅጉራዊና በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ በመስጠት ከጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በዋናነት ካነሷቸው ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዋነኞቹ በኢትዮጵያ የሃይማኖት አክራሪነትና ሽብርተኝነት፣ በኢሕአዴግ ውስጥ አለ ስለሚባለው አለመግባባትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች በሰላማዊ ሠልፍ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ይገኙበታል፡፡ በኢኮኖሚ ረገድ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በተጠናቀቀው ዓመትም ፈጣን ዕድገት ማስመዝገቡን፣ የግል ባለሀብቶች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው ዘርፎች ለመሳተፍ አለመፈለግ፣ መሠረታዊ በሚባሉት የመጠጥ ውኃ፣ የሞባይል ስልክና የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎቶች የሚስተዋሉ የአገልግሎት መቆራረጦች ሊቀረፍ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋዜጠኞች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ዕድል ከመስጠታቸው በፊት ባለፈው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አገሪቱ ስላስመዘገበቻቸው ውጤቶች አጠር ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በእሳቸው ማብራ