Posts

ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆኑ

Image
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2006 ዓ.ም. ባደረጉት የጋራ ስብሰባ በቱርክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ ያሉትን ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን በፕሬዚዳንትነት ሰየሙ፡፡ አዲሱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ፣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካይነት ቃለ መሐላ ከፈጸሙ በኋላ ሥልጣኑን የተረከቡት፣ በሁለት ዙር ለ12 ዓመታት ፕሬዚዳንት ከነበሩት ከአቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ነው፡፡ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ የስድስት ዓመት የፕሬዚዳንትነት የሥራ ዘመናቸውን በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ አቀባበል ካደረጉላቸው በኋላ መጀመራቸው ታውቋል፡፡   በቀድሞው ወለጋ ጠቅላይ ግዛት አርጆ ወረዳ በ1949 ዓ.ም. የተወለዱት ዶ/ር ሙላቱ፣ የመጀመርያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርጆና በአዲስ አበባ ከተሞች የተከታተሉ ሲሆን፣ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከቻይና ቤጂንግ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካል ኢኮኖሚ ፍልስፍና በ1974 ዓ.ም.፣ በዓለም አቀፍ ሕግ የማስተርስ ዲግሪያቸውን በዚያው ዩኒቨርሲቲ በ1980 ዓ.ም. አግኝተዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በ1983 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ሕግ በዶክትሬት ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ የኦሮምኛ፣የአማርኛ፣እንግሊዝኛ፣ቻይናኛና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎች ተናጋሪ የሆኑት ተሰያሚው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቆንስልነትና በዳይሬክተርነት፣ በጃፓንና በቻይና በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት፣ በኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ምክትል ሚኒስትርነት፣ በግብርና ሚኒስትርነትና በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤነት ያገለገሉ ሲሆን፣ፕሬዚዳንት እስከሆኑበት ዕለት ድረስ በቱርክ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር

በልማት “ማሳበብ” ከልማታዊ መንግስት አይጠበቅም!

Image
በመንግስት “ሳንባ” መተንፈስ ለ“ቲቢ” ያጋልጣል                 ፖለቲካዊ ወጋችንን የምንጀምረው በቀልድ ነው፡፡ ግዴለም ባትስቁም አልቀየማችሁም፡፡ ፈገግ ካላችሁ መች አነሰኝ! (ኑሮ “ሃርድ” ሲሆን ሳቅም ይገግማል አሉ) ይልቅስ ሳልረሳው ቀልዱን ቶሎ ልንገራችሁ፡፡ - ፡፡ አንድ የሰው አገር ሰው (ፀጉረ ልውጥ ማለቴ አይደለም!) ከጅቡቲ እየተጫኑ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡትን የመኪኖች መዓት በትዝብት ሲመለከት ይቆይና እነዚህ ሁሉ መኪኖች የት ነው የሚገቡት?” ሲል ይጠይቃል፡፡ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊም (መሬት ይቅለላቸውና!) “የሌሎቹን አላውቅም…አይሱዙ ግን ገደል ነው የሚገባው” አሉ (አሉ ነው!)  በነገራችሁ ላይ… በመዲናዋ የሚርመሰመሰው የመኪና ብዛት እኮ ከነዋሪው እኩል ሊሆን ትንሽ ነው የቀረው፡፡ አንዳንዴ ሳስበው ግን ባለሀብቱም ሆነ ሌላው ትንሽ ገንዘብ እጁ ላይ ከተረፈው ዝም ብሎ መኪና የሚያስጭን ነው የሚመስለኝ። (ጀት ለማስጫን አቅም የለችማ!?) እናላችሁ… የመዲናዋ ተሽከርካሪዎች ከህዝቡ በልጠው መፈናፈኛ ከማጣታችን በፊት “አራርቆ መግዛት” የሚል ፖሊሲ ቢቀረጽ ሸጋ ይመስለኛል፡፡ (“አራርቆ መውለድ” እንደሚባለው) ትራፊክ ፖሊስና መንገድ ትራንስፖርት ጥናት አላደረጉ ይሆናል እንጂ የመኪና አደጋ እንዲህ ህዝብ የሚፈጀው የተሽከርካሪው ቁጥር ያለቅጥ በዝቶ ሊሆን ይችላል እኮ! (“የመኪና ምጣኔ” ሳያስፈልገን አይቀርም!)   እኔ የምላችሁ…ባለፈው ሳምንት የኢቴቪ “ዓይናችን” ፕሮግራም ላይ ከመንጃ ፈቃድ አወጣጥና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ት/ቤቶች አሰራር ጋር በተገናኘ የተጠየቁት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የሰጡትን ምላሽ ሰምታችሁልኛል? ሃላፊዋ የተናገሩትን በአማርኛ ተርጉሞ ለነገረኝ (የገባው ካለ ማለቴ ነው) ወሮታ

ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰልፍ ላይቀጥል ይችላል አሉ

Image
ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚያደርጓቸው የተቃውሞ ሰልፎች ተደጋጋሚና መንግስት አቋም የያዘባቸውን ጉዳዮች የሚያነሱ እንደሆኑ የጠቆሙት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፤ መንግስት ለእያንዳንዱ ሰልፍ ጥበቃ ማድረግ ስለማይችል ሰልፎቹ በተለመደው መልኩ ላይቀጥሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት በጽ/ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች የራሳቸው የፓርቲዎቹ ሳይሆኑ የሌሎች ሃይሎች እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡ ፓርቲዎቹ ሰልፍ ማካሄድ ህገመንግስታዊ መብታቸው መሆኑን የጠቀሱት ጠ/ሚኒስትሩ፤ መንግስት በተደጋጋሚ ጥበቃ ሲያደርግ ቢቆይም፣ በሰልፎቹ የሚነሱት ጥያቄዎች ፋይዳ ቢስ ከመሆናቸውና ከፓርቲዎቹ ብዛት አንፃር መንግስት በቀጣይ ለሰልፎች ጥበቃ ለማድረግ የሚቸገርበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል አስረድተዋል፡፡  ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ መንግስት በተደጋጋሚ ምላሽ የሰጠባቸውን ጥያቄዎች መላልሰው የሚያቀርቡት በመንግስት ላይ ጫና በመፍጠር አቋሙን ለማስቀየር በማሰብ ሊሆን ይችላል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ ይሄ ግን በፍፁም የማይሳካ ሃሳብ ነው ብለዋል፡፡ “ግንቦት ሰባት” በቅርቡ መንግስትን ለመጣል ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ በይፋ መግለፁን በተመለከተ ተጠይቀው ሲመልሱም፣ የፓርቲው አመራሮችና ደጋፊዎች ተጨባጭ ያልሆነ ህልም ውስጥ ሆነው የተናገሩት ነገር እንደሆነና ከህልማቸው ሲነቁ እውነታውን እንደሚገነዘቡት ጠ/ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ መከፋፈልና የሃይል መጠባበቅ አለ የሚለውን መረጃ በተመለከተም “ይህ የአንዳንድ አፍራሽ ሃይሎች ከንቱ ምኞትና ተጨባጭ ያልሆነ አሉባልታ ነው” ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&am

Abyssinia Ballooning to Launch Flight in Hawassa, Sidama

Image
Abyssinia Ballooning, Ethiopia’s first hot air balloon company is planning to start flying from Debre Zeit, Awassa and Bahir Dar soon in addition to its Addis Ababa flight. Abyssinia Ballooning is set to keep building its balloon fleet and expects its second-passenger balloon before the end of 2013. In February 2012, the innovative recreational company made its first flight over Addis Ababa. Since the beginning of Abyssinia Ballooning’s operation, more than 30 balloon flights have followed and over 300 Ethiopians and foreigners have enjoyed ballooning in Ethiopia. Abyssinia Ballooning (AB) is an initiative of the Dutch ballooning company Virgin Balloon Flights (a licensee of the renowned Virgin brand of the Englishman Sir Richard Branson) and a local Ethiopian business partner. Research on feasibility of flight areas in Ethiopia started early as the end of 2010. When the flight areas turned out to be good to fly balloons an extensive business plan was written and

ኢትዮጵያን ለቀጣይ ስድስት ዓመታት የሚያገለግሏት ፕሬዝዳንት ሰኞ ይመርጣሉ

Image
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 24 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው ሰኞ የህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች በሚያካሂዱት የጋራ ስብሰባ የ2006 በጀት ዓመት የስራ ዘመናቸውን በይፋ ይጀምራሉ ። በዚሁ    እለት    ላለፉት 12 ዓመታት ኢትዮጵያን በርዕሰ ብሄርነት የመሯት ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስም የምክር ቤቶቹ በይፋ መከፈትን ያበስራሉ። በመክፈቻው እለትም ፕሬዚዳንት ግርማ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ በመሆናቸው በክብር ይሰናበታሉ ። ምክር ቤቱም በዕለቱ ከሚያከናውናቸው መርሃ ግብሮች መካከል እሳቸውን የሚተካ አዲስ ፕሬዝዳንት መምረጥ ይሆናል ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ፥ ከተሰናባቹ   ፕሬዚዳንት    ንግግር በኋላ    የአዲስ ፕሬዝዳንት እጩ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ድምፅ ይሰጥባቸዋል ። በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት ለፕሬዝዳንትነት እጩ የማቅረብ ስልጣን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን ፥ የሃገሪቱ ርዕስ ብሄር ለመሆን እጩው የግድ የምክር ቤቱ አባል እንዲሆን አይጠበቅበትም። በመሆኑም የምክር ቤት አባል ያልሆነም ርዕሰ ብሄር ሊሆን ስለሚችል በእጩነት ሊቀርብ እንደሚችል ነው አፈ ጉባኤው ያስረዱት ። ምክር ቤቱ ምርጫውን ካከናወነ በኋላም አዲሱ ፕሬዝዳንት ወንበራቸውን ከተሰናባቹ ፕሬዝዳንት በመረከብ ለኢትዮጵያ ህዝብ ንግግር በማድረግ ስራቸውን ይጀምራሉ። የአዲሱ ፕሬዝዳንት ንግግርም የዓመቱ ዋና ዋና ስራዎችን በማካተት በመንግስት የወደፊት ስራዎች ላይ ያተኩራል ተብሎ ይጠበቃል። ተሰናባቹ    ፕሬዚዳንት ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ላለፉት 12 ዓመታት ያህል ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል። በእነዚህ የስራ ዘማናቸው ታዲያ በህገ