Posts

ኣብዛኛው ተማሪ ኣንደኛ ምርጫ የሆነውን ትምህርት ኣይነት እና ዩኒቨርሲቲ በማያገኝበት ሁኔታ፤ ዩኒቨርሲቲን እና የትምህርት ክፍል መቀያየርን መከልከል ምን ይሉታ?

Image
ዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት ክፍል መቀያየር አይቻልም - ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች አድራሻቸውን ጭምር በመጠቀም የዩኒቨርሲቲ እንቀያየር ማስታወቂያ ሲለጥፉ ይስተዋላል። ይህ ጉዳይ በተለይም በአዲስ አበባ አራት ኪሎ አካባቢ በስፋት ይስተዋላል ፤ አዲስ ገቢ ተማሪዎችም ይህን አካባቢ በብዛት ያዘወትሩታል። ተማሪዎቹ እንደሚሉት ከተለያዩ ሰዎች በሚያገኙት መረጃ መሰረት ዝውውሩን ለመጠየቅ ይነሳሳሉ። የተመደቡበት ቦታ ምቹ አይደለም በሚል ፣ ከቤተሰብ መራቅ ባለመፈለግ ፣ የተመደቡበት የትህርት ክፍል ከምርጫቸው ጋር አይጣጣምም የሚሉት ለዝውውሩ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ። ተማሪዎቹ ከሚለጥፏቸው ማስታወቂያዎች በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲ የሚቀያየሩ ተማሪዎችን እናገናኛለን የሚሉ እና በአጋጣሚው ለመጠቀም የሚሞክሩ ግለሰቦችም ይስተዋላሉ። የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ የዩኒቨርሲቲም ሆነ የትምህርት ክፍል ዝውውር አይፈቀድም ይላል። በሚኒስቴሩ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ሳሙኤል ፥ ተማሪዎቹ ባስመዘገቡት ውጤት እና በሞሉት ምርጫ መሰረት የተመደቡ በመሆኑ ጉዳዩ አይታሰብም ባይ ናቸው። አያይዘውም አዲሶቹም ሆኑ ነባሮቹ ተቋማት በሚገባ እና በሚሰጡት ትምህርት አግባብ የተደራጁ በመሆናቸው የትም ቢመደቡ ተማሪዎቹ ስጋት እንዳይገባቸውም ነው የተናገሩት። ከዚህ ባለፈ ግን የሚቀያየሩ ተማሪዎችን እናገናኛለን ከሚሉ ህገ ወጦችም ራሳቸውን ይጠብቁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። http://www.fanabc.com/index.php?option=com_content&view=article&id=5579:2013-09-30-07-42-38&a

ባህልን የመጠበቅ የመንግሥት ግዴታ

Image
አገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ባህሎች ባለቤት ናት፡፡ የብሔርና የሃይማኖት ብዙኅነት ያበዛቸው የተለያዩ ባህሎች የኢትዮጵያውያን መታወቂያ ናቸው፡፡ ኅብረተሰብን ኅብረተሰብ ከሚያስብሉት ምክንያቶች አንዱ ባህል ሲሆን፣ ባህሉ የማይታወቅለት ኅብረተሰብ በሌሎች አገሮችም የመታወቁ ነገር አነስተኛ ነው፡፡ አንዲት አገር ለምትከተለው ሁለንተናዊ የዕድገት አቅጣጫ ባህል የራሱ የሆነ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የምንመለከተው አወንታዊ ተፅዕኖ ያላቸውን ባህሎች የሕግ መሠረት ነው፡፡ እነዚህ ባህሎች ለኅብረተሰቡ ቀጣይ ሕልውና መሠረት የሆኑ፣ የአገሪቱን ልማት የሚያግዙና በዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባላቸው መስፈርቶች ለግለሰቦች ጠቃሚ የሆኑ ናቸው፡፡ በዚህ ሳምንት እየተከበረ ያለውን የመስቀል በዓል መነሻ በማድረግ በዓላትን ተከትለው የሚታዩ ባህሎችን የሕግ መሠረት መመልከት የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ነው፡፡ በዓላት ብዙ ብዙ ክፍል ቢኖራቸውም በአገራችን ባህል ላይ ሰፊ ተፅዕኖ ያደረጉት ሃይማኖታዊ በዓላት ስለመሆናቸው በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ ቁሳዊ የባህል ክፍሎችን ብንመለከት አለባበስ፣ አመጋገብ፣ ለጌጥ የምንጠቀምባቸው ዕቃዎች፣ በዓላቱ የሚከበሩባቸው ቦታዎች ወዘተ. ሃይማኖታዊ መሠረት አላቸው፡፡ የመስቀልን በዓል መነሻ አድርጎ ከሚታዩት ባህሎች ውስጥ በአልባሳት ላይ የሚታዩ ጥልፎች፣ በሰውነት ላይ የሚቀረፁ ጌጦች፣ በደረትና በጆሮ የሚንጠለጠሉ የመስቀል ጌጦች ይገኙበታል፡፡ በደቡብ ብሔሮችና ብሔረሰቦች የተለመዱት የመስቀል በዓል አከባበሮችን ተከትሎ የሚታዩት የአመጋገብ ባህል ተጨማሪ አስረጅ ነው፡፡ ግዙፋዊ ያልሆኑም ባህሎች ከሃይማኖት በመነጩ ባህሎች ይስተዋላል፡፡ ሕዝቡ በኅብረት በመሆን በየሰፈሩ ትናንሽ ደመራ መደመሩ፣ ለንግድ ወጥተው የነበሩ የኅብረ

Ethiopians demonstrate against anti-terrorism law

Image
Ethiopians have taken to the streets of the capital Addis Ababa. They’ve protested what they termed as an intentional move by the government to criminalize them through the anti-terrorism law. The protesters claim that only citizens who have expressed opinions against the government have been subject to the law since it was adopted in 2009. The New York-based independent Committee to Protect Journalists says more than 10 journalists have been charged under Ethiopia’s anti-terrorism law, and that the country has the highest number of exiled journalists in the world.   Human Rights Watch has also expressed concerns over the law for what it calls the overly broad definition of “terrorist acts.”   The law’s provisions on support for terrorism contain a vague prohibition on “moral support” under which journalists have been convicted. Since 2011, eleven journalists have reportedly been convicted. The protesters demand that the government redefines who a terrorist is.   The ri

INFANT MORTALITY IN THE RURAL SIDAMA ZONE, SOUTHERN ETHIOPIA: EXAMINING THE CONTRIBUTION OF KEY PREGNANCY AND POSTNATAL HEALTH CARE SERVICES

Image
http://www.google.com/url?sa=i&rct=j&q=&esrc=s&source=images&cd=&cad=rja&docid=Qll9yHLE2i6WeM&tbnid=WZR7Jjs1w1Lb1M:&ved=0CAQQjB0&url=http%3A%2F%2Fwww.msf.org.uk%2Fcountry-region%2Fethiopia&ei=EmJIUsTIB5DK9QTVo4HoBA&bvm=bv.53217764,d.eWU&psig=AFQjCNEu-ZFaU-fIpp51n14qm0ynB7DyDg&ust=1380561760755591 Summary Objectives: This study is aimed at examining the contribution of selected pregnancy and postnatal health care services to Infant Mortality (IM) in Southern Ethiopia. Method: Data were collected from 10 rural villages of the Sidama Zone, Southern Ethiopia, using a structured interview schedule. The 1,094 eligible women respondents were selected using a combination of simple random and multi-stage sampling techniques. The main outcome variable of the study (IM) was measured by reported infant deaths during the twelve months preceding the survey, and was estimated at 9.6% or 96 infant deaths per 1,000 births. Pregnancy and

በሲዳማ ዞን የገጠር ቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ እንቅስቃሴ ጥሩ ሆኖ በጥራት ላይ ትኩረት ብሰጠው

Image
በሲዳማ  ዞን ውስጥ ከኣንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ገንዘብ መንገድ መስራቱ እየተነገረ ያለ ሲሆን ፤ የመንገዶቹ ጥራት ግን ትኩረት የተሰጠበት ኣይመስልም። ሰሞኑን የዞኑ መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ይፋ ያደረገውን መረጃ ከታች ያንብቡ፦ አዋሳ መስከረም 19/2006 በሲዳማ ዞን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከአንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ በአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የገጠር ቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ መካሄዱን የዞኑ መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ገለጸ፡፡ በፕሮግራሙ ከ30 ሺህ ለሚበልጡ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፈጠሩ ተገልጿል፡፡ የመምሪያ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ዳንኤል ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ሀገራዊና ክልላዊ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ተከትሎ በዞኑ ሁሉም የገጠር ቀበሌ ደረጃቸውን በጠበቁና ክረምት ከበጋ በሚያገለግሉ መንገዶች ለማገናኘት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ፕሮግራሙ በዞኑ ገጠርና ከተማ ፣በአምራችና አገልግሎት ሰጪ እንዲሁም በግብርናና ኢንዱስትሪ ዘርፎች መካከል የሚኖረውን ትስስር በማጠናከር አርሶ አደሩ ምርቱን ለገበያ በማቅረብ ከምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዞኑ እስካሁን 927 ኪሎ ሜትር የገጠር ቀበሌዎችን ክረምት ከበጋ የሚያገለግል መንገድ መኖሩን ጠቁመው ሽፋኑን ከፍ ለማድረግ በበጀት ዓመት ከአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ባላይ መንገድ ግንባታ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ 25 በመቶ በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሸፈን በመሆኑ ከ154 ሺህ በላይ ህዝብ በስራው በመሳተፍ 850 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የጠረጋና ምንጣሮ ስራ ማከናወናቸውን ገልጸው ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ ከወጪ ማዳኑን አስረድተዋል፡፡ በዚሁ ስራ ከተሳተፉት የህብረተሰብ ክፍ