ወጣቱን በማብቃት ላይ መሠራት አለበት
የኢትዮጵያ የሕዝብ ብዛት ከ85 ሚሊዮን በላይ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አገሪቱ ካላት የሕዝብ ብዛት ውስጥ ከሁለት ሦስተኛ በላዩ ወጣቶች ናቸው፡፡ ይህ በሚገባ የሚሠራበት ከሆነ እጅግ መልካም አጋጣሚ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ምክንያቱም ወጣቶች የማኅበረሰቡ የጀርባ አጥንት መሆናቸውን በማስመስከራቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደ አገር ይህንን የወጣት ኅብረተሰብ ፍሬያማ በማድረግ ልታተርፍበት ትችላለች፡፡ መንግሥት ይህንን በመገንዘብ የወጣቶች ፖሊሲ ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን መንግሥት የአገሪቱን ወጣቶች አቅም በሚገባ አደራጅቶ እየተጠቀመበት ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ ስለዚህ መንግሥት ይህን ግዙፍና ጠንካራ የሆነ የኅብረተሰብ አካል እንዴት ሊጠቀምበት እንደሚችል ማሰብ ይገባዋል፡፡ እንደ አሜሪካ ባሉ የዓለማችን ኃያላን አገሮች ወጣቶች ያላቸው ተፅዕኖ ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለአብነት እንኳን በዓለማችን በሰፊው የሚታወቀው የፌስቡክ ማኅበረሰብ ድረ ገጽ መሥራችና ባለቤት ወጣት አሜሪካዊ ነው፡፡ የ29 ዓመቱ ማርክ ዘከርበርግ በፌስቡክ ድረ ገጽ በኩል ከአንድ ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን ማፍራት ችሏል፡፡ በዚህም ከአሜሪካ አልፎ በዓለማችን ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰብ አድርጐታል፡፡ እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ለዚህ ወጣት ጉዞ መሳካት በርካቶች እጃቸው አለበት፡፡ ለአብነት የፌስቡክን ባለቤት አነሳን እንጂ በአሜሪካ ለአገርም ሆነ ለሕዝባቸው ኩራት የሆኑ በርካታ ወጣቶች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ወጣቶች ከአገራቸው አልፈው በዓለማችን ላይ እንደዚህ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ ያስቻላቸው ዓቢይ ጉዳይ ደግሞ፣ ለወጣቶች ምቹ የሆነ ፖለሲ በአገራቸው በመኖሩ ነው፡፡ ታዲያ እኛም እንደ አገር ከዚህ ልንማር የምንች