‹‹ልማታዊ መንግሥትን ከፌዴራል ሥርዓት ጋር ማጣጣም እጅግ አስቸጋሪ ተግባር ነው›› ፕሮፌሰር ክርስቶፈር ክላፓም
‹‹ልማታዊ መንግሥትን ከፌዴራል ሥርዓት ጋር ማጣጣም እጅግ አስቸጋሪ ተግባር ነው›› ፕሮፌሰር ክርስቶፈር ክላፓም መስከረም 13 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ፋኩልቲ የእሸቱ ጮሌ አዳራሽ “Federalism and the Developmental State” በሚል ርዕስ በዕውቁ የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ክርስቶፈር ክላፓም የቀረበው ጥናት “Perspectives of Diversity in Ethiopia” የተሰኘውና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ጥናት ማዕከል፣ በፍሬድሪክ ኤበርት ስቲፍቱንግና በጎተ ኢንስቲትዩት የሚዘጋጀው የውይይት መድረክ አካል ነበር፡፡ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ እንዲጀመር ፕሮግራም ለተያዘለት ፕሮግራም ታዳሚዎች ከ11 ሰዓት ጀምሮ ቦታ መያዝ ጀመሩ፡፡ የጥናቱ አቅራቢ ፕሮፌሰር ክርስቶፈር ክላፓም በወጣትነት ዘመናቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ ላይ የሚያተኩሩ ዘርፈ ብዙ መጻሕፍትንና የምርምር ሥራዎችን ያሳተሙ ስለሆኑ ብቻ አልነበረም፣ ይልቁንም የጥናታቸው ርዕስ የበርካታ ሰዎችን ስሜት የሳበ ነበር፡፡ ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም እንደ መንግሥት አወቃቀር በኢትዮጵያ የበርካታ ዓመታት ተሞክሮ ቢሆንም፣ ኢሕአዴግ ሕጋዊ ይዞታ በመስጠትና በፈቃደኝነት ወደ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ እንዳመጣው በመግለጽ ነው ፕሮፌሰሩ ንግግራቸውን የጀመሩት፡፡ ልዩነቱ ከኢሕአዴግ ውጪ ያሉት መንግሥታት ፌዴራሊዝምን ቢያንስ በባሕሪ ደረጃ የተቀበሉና የአካባቢ አገዛዞችን ዕውቅና ሳይሰጡ ኢትዮጵያን መምራት አስቸጋሪ ስለነበረባቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክ እ.ኤ.አ. ከ1855 ጀምሮ ኢትዮጵያን ከመሩት መንግሥታት መካከል የአሁኑ መንግሥትን በአገዛዝ ዓ