Posts

ዘመን ሲለወጥ ያልተለወጡት ድንጋጌዎች

ሕግና ኅብረተሰብ ጠንካራ ቁርኝት አላቸው፡፡ ኅብረተሰብ በሌለበት ሕግን ማሰብ፣ ሕግ በሌለበት በሥርዓት የሚኖር ኅብረተሰብን ማሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡ ይህ ግንኙነት አንዳንድ ጊዜ በመቀዳደም ሊፈጸም ይችላል፡፡ ሕግ ኅብረተሰብን ዘመናዊ ለማድረግና ለመለወጥ እንደ መሳሪያነት ሊያገለግል ይችላል፡፡ በእንዲህ ዓይነት ጊዜ የሕጉ ዓላማ ኅብረተሰቡ ያልደረሰበትን ለውጥ ማስገኘት ነው፡፡ በተቃራኒው ከኅብረተሰቡ የሚወጡ እሴቶችና ባህሎችን ወደ ሕግ ደረጃ በማሳደግም የኅብረተሰቡን ሕልውና ማስቀጠል ይቻላል፡፡ እነዚህ የተሳሰሩ ግንኙነቶች ኅብረተሰቡ ከሕግ መጠቀም የሚቻልበትን ሁኔታ የሚያሰፋ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ በሆነ መልኩ ሕጉ ከኅብረተሰቡ ዕድገት ወደ ጓላ ከቀረ ሕጉ ከወረቀት ያለፈ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ ይህን ችግር በአገራችን የተወሰኑ ሕግጋት እናስተውለዋለን፡፡  የፍትሐ ብሔር ሕጋችንን ጨምሮ አገራችን በአሁኑ ወቅት የምትጠቀምባቸው ሕግጋት በ1950ዎቹ ከውጭ አገሮች በተወሰነ ማሻሻያ የገቡ ናቸው፡፡ ሕግጋቱ በጊዜው ሲወጡ አፄው የነበራቸው ዓላማ አገሪቱን ዘመናዊ ሕግጋት ከሚከተሉ አገሮች ማመሳሰል ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ሕግጋት ለአገሪቱ ባህል ሰፊ ቦታ አልሰጡም በሚል ትችት የሚቀርብባቸው ቢሆንም፣ አገሪቱን ላለፉት 50 ዓመታት በማስተዳደር ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ድንጋጌዎች አብዛኛዎቹ አሁንም ድረስ የአገሪቱ ዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር ለመምራት በቂ ቢሆኑም የተወሰኑት ድንጋጌዎች ከኅብረተሰቡ ባህል፣ ወግና ዘመናዊ አስተሳሰብ ጋር የማይጣጣሙ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ባለፉት አሥር ዓመታት የተሻሻሉ አሉ፡፡   በዚህ ረገድ የቤተሰብ ሕጉ፣ የወንጀል ሕጉ፣ የመሬት ሕግ፣ የማኅበራት ሕግ ወዘተ. በዘመናዊ አስተሳሰብ በመቃኘት እንዲሻሻሉ ተደርገዋል፡፡ እስካሁንም

ሥራን የማይንቀው ዳያስፖራ

በጌታቸው ንጋቱ ዘመን በተለወጠ ቁጥር የተቻለኝን ሁሉ በማድረግ በአገር ምድር ከዘመድ አዝማድ ጋር አዲስ ዓመትን ለማክበር ከምኖርበት አገር አቀናለሁ፡፡ ከአገር ከወጣሁ ጀምሮ አንድም ዓመት የዘመን መለወጫን ከኢትዮጵያ ውጪ አሳልፌ አላውቅም፡፡ ዘመድና ጓደኛም ስለ አሜሪካ ኑሮ ይጠይቃሉ፡፡ እኔም የተቻለኝን ሁሉ እመልሳለሁ፡፡ ከሁሉም ግን አንድ የሚገርመኝ ጥያቄ ከአንዲት ጓደኛዬ ነው የመጣው፡፡ ‹‹ኑሮ በአሜሪካ እንዴት ነው? መቼም አሜሪካ የሚኖር ሰው ምንድነው የምትሠራው አይባልም፡፡ ሁሉም ተጠግርሮ ነው የሚኖረው፤›› አለችኝ፡፡  ጓደኛዬ ስለ ሥራና የሥራ ክቡርነት ያላትን አመለካከት ለማረቅ ብሞክርም ይህ የአንድ ሰው ብቻ ሳይሆን የብዙዎች የግንዛቤ ችግር ስለመሰለኝ ይህንን ለመጻፍ ተነሳሁ፡፡  1.ሥራ ክቡር ነው ቢያንስ በሐሳብ ደረጃ ሥራ ክቡር ነው እንላለን፤ ነገር ግን ስንቶቻችን ነን ሥራ ክቡር ነው፤ ብለን በተሰማራንበት የሥራ መስክ ውጤታማ ለመሆን የምንጥረው የሚለው አጠያያቂ ነው፡፡  ሥራ ክቡር ነው የሚለው አባባል በሰሜን አሜሪካ በተግባር ላይ ውሎ የሚታይ አባባል ነው፡፡ የምትሠራው ሥራ ሳይሆን በምትሠራው ሥራ ምን ያህል ውጤታማ ነህ፤ ታክስህን በሥነ ሥርዓት ትከፍላለህ፤ የክሬዲት (ብድር) አጠቃቀምህ ምን ይመስላል፤ ሰላማዊና ጠንካራ ሠራተኛ ነህ ወይ? የሚለው ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡  አንዳንዶች ከአገር ወጥተው ኑሯቸውን በአሜሪካ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ታክሲ በማሽከርከራቸው፤ ሆቴል በማስተናገዳቸው ወይም ‹‹ፓርኪንግ ሎት›› ውስጥ በመሥራታቸው ከአገር ቤት ባሉ ጓደኞቻቸው ትችት ሲሰነዘርባቸው ስሰማ አንዳንዶች ስለ ሥራ ባላቸው ግምት አዝናለሁ፡፡  ከቅርብ ሳምንታት በፊት በመሀል ዋሽንግተን ዲሲ አንዲት ወጣት ነጭ አሜሪካዊት በባር

Ethiopia Free to protest, just a bit Could political demonstrations in Ethiopia herald greater freedom?

Image
A RARE flicker of political protest graced the streets of Ethiopia’s otherwise regimented capital, Addis Ababa, on June 2nd. Demonstrators marched peacefully through the city, many carrying pictures of imprisoned loved ones. Later they gathered on Churchill Avenue, the capital’s main thoroughfare, where they were told that a new struggle had begun. Yilekal Getachew, chairman of the opposition Semayawi (Blue) party, demanded the release of political prisoners and railed against unemployment and corruption. Campaigners claim that as many as 10,000 people attended; government officials say the number was nearer 4,000. Whatever the true figure, it was the biggest demonstration in Ethiopia since 2005, when protests amid claims of election rigging were violently suppressed, leaving nearly 200 unarmed protesters dead and thousands arrested. Related topics Since then the political opposition has been eviscerated. Its leaders have been jailed or have gone into exile, the media h

የሲዳማ ክልል ጥያቄን ተከትሎ በዞኑ ብሎም በዓለም ኣቀፍ ደረጃ የተነሳውን ህዝባዊ ንቅናቄ ለመቀልበስ በኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ የተመራው የክልሉ እና የዞኑ ኣስተዳደር በንጽሃን የሲዳማ ተወላጆች ላይ ያደረሰው የሰብኣዊ መብት ረገጣና እስር በ2005 ዓበይት የፖለቲካ ጉዳዮች ኣልተካተተም

የሲዳማ ክልል ጥያቄን ተከትሎ በዞኑ ብሎም በዓለም ኣቀፍ ደረጃ የተነሳውን ህዝባዊ ንቅናቄ ለመቀልበስ በኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ የተመራው የክልሉ እና የዞኑ ኣስተዳደር በንጽሃን የሲዳማ ተወላጆች ላይ ያደረሰው የሰብኣዊ መብት ረገጣና እስር በሪፖርተር ጋዜጣ የ2005 ዓበይት የፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ ኣልተካተተም። ጋዜጣው በኣገሪቱ በተከሰቱ ኣበይት የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ያቀረበውን ዘገባ ከታች ያንቡ፦ በ2005 ዓ.ም. የተከሰቱ ዓበይት የፖለቲካ ጉዳዮች በዋነኛነት ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሹመት፣ ከሙስሊሞች ጥያቄ መባባስ፣ ከሙስና ተጠርጣሪዎች የፍርድ ሒደት፣ ከመድበለ ፓርቲ ሥርዓቱ ፈተናዎች፣ ከኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ሥራዎች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ የሥልጣን ሽግግርና የመንግሥት የመዋቅር ለውጥ የቀድሞውን ሊቀመንበር ሕልፈተ ሕይወት ተከትሎ ኢሕአዴግ መስከረም 5 ቀን 2005 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ አቶ ኃይለ ማርያምን አዲሱ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡ በዚሁ የኢሕአዴግ ስብሰባ ፓርቲው የመንግሥት ኃላፊዎች የሆኑ አባላቱ የሥልጣን ዘመን በአሥር ዓመት መገደቡንና የዕድሜ ጣሪያውም 65 ዓመት መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ከሆኑ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ ይጠበቁ የነበሩት አቶ ኃይለ ማርያም፣ ፓርላማው በይፋ ጠቅላይ ሚኒስትር ያደረጋቸው መስከረም 11 ቀን 2005 ዓ.ም. ነበር፡፡ ሕወሓት በሊቀመንበርነትና በምክትል ሊቀመንበርነት የመረጣቸው አቶ ዓባይ ወልዱና ዶ/ር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል የኢሕአዴግ የንደፈ ሐሳብ መጽሔት የሆነው አዲስ ራዕይ፣ በ2001 ዓ.ም. ሐምሌ ወር እትሙ ካስቀመጠው የመተካካት ፖሊሲና በትጥቅ ትግሉ የተሳተፉ ከፍተኛ አመራሮችን የማሰናበት ዕቅድ ጋር አብሮ እንደማይሄድም የ

አገልግሎት አሰጣጥ ሲሳከርና ሲቋረጥ ከመንግሥት ማብራሪያና ይቅርታ ይጠበቃል

Image
በማደግ ላይ ባሉትም ሆነ በበለፀጉት አገሮች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ፣ የውኃ አቅርቦት መስተጓጎልና የኢንተርኔት አገልግሎት አለመኖር ያጋጥማል፡፡ መጠኑና ደግግሞሹ በእጅጉ ሊለያይ ይችላል እንጂ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን ከፍተኛ ሕዝባዊ ጥያቄ እያስነሳ ያሉ የአገልግሎት አቅርቦት መሳከርና መቋረጥ እያጋጠሙ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ውኃ ለቀናት መጥፋት የተለመደ እየሆነ ነው፡፡ ለሳምንትና ለወር ተቋርጦብናል የሚሉ አሉ፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል በቀን ሦስቴና አራቴ ይቋረጣል፡፡ መደበኛ ስልኮች ይቋረጣሉ፣ ሞባይል ስልኮች አይሠሩም፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎትም ብርቅ እየሆነ ነው፡፡ የብሮደባንድ፣ የዋይፋይና የኢቪድዮ ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ የተለመደ ሆኗል፡፡ ለተፈጠሩት ችግሮች ከአቅም በላይ የሆኑና ያልተገመቱ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ግን ቀርበው በግልጽ ማስረዳት አለባቸው፡፡ ችግሮቹ እስኪስተካከሉ ለሚያጋጥሙ የአገልግሎት መቋረጦች መንግሥት ሕዝቡን  በይፋ ይቅርታ መጠየቅ አለበት፡፡  በኤሌክትሪክ ኃይል መጥፋት ምክንያት የበርካታ ፋብሪካዎች ማሽኖች እየተበላሹና ከባድ ኪሳራ እያስከተሉ ናቸው፡፡ ምርትም እየተቋረጠ ነው፡፡ በኤሌክትሪክ ኃይል መጥፋት ምክንያት በርካታ የቤት ዕቃዎች እየተቃጠሉና እየተበላሹ ናቸው፡፡ ፍሪጆች፣ ቴሌቪዥኖችና የኩሽና ዕቃዎች እየተቃጠሉ ቤተሶበችን ለከፍተኛ ኪሳራ እያደረጉ ናቸው፡፡ በተደጋጋሚ፡፡ በዚህ ሰዓት ኢንተርኔት ከፍቼ መልዕክቶችን አያለሁ የሚል ሐሳብ ተረት ተረት እየሆነ ነው፡፡ በዚህም በርካታ የቢዝነስ ሥራዎች እየተስተጓጎሉ ናቸው፡፡ ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን በመቋረጡ ምክንያት በርካታ ቢዝነሶች እየተጎዱ ናቸው፡፡ ውኃ፣ ኤሌክትሪክና ስልክ በሌሉበት ሕመምተኞችንና ሕፃና