Posts

በሃዋሳ ከተማ ከ593 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ የልማት ስራዎች ይከናወናሉ

Image
ሀዋሳ ጳጉሜ 05/2005 በሃዋሳ ከተማ በተያዘው በጀት አመት ከ593 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ የልማት ስራዎች እንደሚካሄዱ የከተማው አስተዳዳር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ አስታወቀ ። በበጀት አመቱ በከተማዋ የሚካሄዱት የልማት ስራዎች የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እንዲሁም የምዕተ አመቱን የልማት ግቦች ታሳቢ ያደረጉ ናቸው። በከተማዉ ከሚከናወኑት የልማት ስራዎች መካከል የተለያዩ ደረጃ ያላቸው የመኪና መንገዶች ግንባታ ፣በመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፣ በትምህርት ተዳራሽነትና ጥራት ፣ በጤና፣ የተፈጥሮና የአካባቢ ጥበቃና በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮሩ ናቸዉ ። በተለይ በመንገድ ልማት ዘርፍ ስድሳ ኪሎ ሜትር የኮብል ስቶን፣ 30 ኪሎ ሜትር ደረጃ የማሳደግና አዲስ የአስፋልት ፣ 120 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገዶች ጥገና እንደሚካሄድ የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ አሻሬ ኡጋ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አመልክተዋል ። በትምህርት ዘርፎችም ሶሰት የመጀመሪያ ደረጃና ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ፣50 ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች የሚገኑ ሲሆን በጤናዉ ዘርፍም የአንድ ጤና ጣቢያ ግንባታን ማጠናቀቅና የአንድ ሆስፒታል ግንባታ እንደሚጀመር አመልክተዋል ። የከተማውን የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት የማሻሻል ፣የተቀናጀ የቤቶች ልማት የማካሄድ እንዲሁም የከተማው ፅዳትና ውበት የማስጠበቅና የመናፈሻ ስፍራዎችን የማደራጀት ስራዎች እንደሚገኙበት ገልጠዋል ። ለስራዎቹ ማስፈፀሚያ የሚያስፈልገው ከ593 ሚሊዮን ብር በላይ በላይ በጀት ከከተማው አስተዳደርና ከመንግሰት ግምጃ ቤትና ከሌሎችም የገንዘብ ምንጮች የተመደበ መሆኑም ተመልክቷል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=11723&K=1

Pragmatism: What Ethiopia’s Privatisation Project Lacks

Image
Pragmatism seems to be a typical trait in the EPRDF camp, even if it has been declining lately. Since coming to power in 1991, the Revolutionary Democrats have gone through what can arguably be described as a rough policy ride. It is all connected to the timing of their ascendancy to power. The end of the cold war, which saw a dichotomous world of ideological submissions, followed by the collapse of the Soviet Union, brought the economic model of the West to the fore, with no meaningful competition. Capitalism became the buzzword of the day, while democracy is considered the peerless system of governance. Devoted socialists themselves, the EPRDFites were faced with a confusing global reality that made making choices all the more difficult. On the one hand, their long overdue socialist inclination provided them with ideological instruments to bash the fundamentals of capitalism in all its forms. On the other, the rise of capitalism was a force impossible to ignore for any force

የሪፖርተር ጋዜጣ በውሽት ዜና ብዙዎችን ማስደሰቱን ኣመነ፦ የደቡብ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነታቸው አልተነሱም

የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትን በምክትል ርዕሰ መስተዳደርነት ከሚመሩት አራት ኃላፊዎች መካከል ሦስቱ ከኃላፊነታቸው ተነሱ በሚል ባለፈው ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. የተጻፈው ዘገባ ስህተት መሆኑን እየገለጽን፣ ሦስቱም በኃላፊነታቸው ላይ መሆናቸውን እናስታውቃለን፡፡ አሁንም በኃላፊነታቸው ላይ ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ታገሠ ጫፎ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲ ናቸው፡፡  የደቡብ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ዘገባው ፍፁም የተሳሳተና የክልሉ መንግሥት የማያውቀው በመሆኑ የክልሉን መንግሥትና ሕዝብ አሳዝኗል፡፡ ‹‹ይህ የተሳሳተ ዘገባ የወጣው የክልሉ መንግሥት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን በአንድ መንፈስ እያካሄዱበት በሚገኝበት ወቅት መሆኑ፣ ዘገባውን እጅግ የሚያሳዝንና የሚያስገርም ከማድረግ ባሻገር ይህ ተግባር በክልሉ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ ልማትና የሕዝብ ተጠቃሚነት ይጐዳል፤›› ሲል የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡  በወቅቱ ዘገባውን ያቀረበው የክልሉ የሪፖርተር ልዩ ዘጋቢ መረጃ በመሰብሰብ፣ በማጠናቀርና ዘገባውን በማቅረብ ሒደት ላይ ስህተት መሥራቱን የዝግጅት ክፍሉ በመረዳቱ፣ ዘጋቢውን በማገድና በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ማጣራት አድርጎ ተገቢውን ዕርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ሆኖም ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በወጣው ዕትም የተዘገበው ስህተት መሆኑን እየገለጽን የክልሉን መንግሥት፣ ሦስቱን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮችንና አንባቢያንን ከ

ኢኮኖሚውና ቢዝነሱ ‹‹ግሉኮስ›› ያስፈልገዋል

Image
ኢኮኖሚያችንና የቢዝነስ እንቅስቃሴያችን እየፈዘዘ ነው፡፡ ቀዝቀዝ ብሏል፡፡ አተነፋፈሱ ጥሩ አይመስልም፡፡የገንዘብ እንቅስቃሴ እንደነበረው አይደለም፡፡ ክፍያዎች እየዘገዩ ናቸው፡፡ በባንኮችና በደንበኞች መካከል ጠንካራ ግንኙነት የለም፡፡ ባንኮቹ በተለይም የግል ባንኮች እየተዳከሙ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት የገንዘብ እንቅስቃሴ ሙትት እያለ ነው፡፡ በውጭ ምንዛሪ ችግርና እጥረት ምክንያት በጣም የሚያስፈልጉ ዕቃዎች እንደተለመደው ከውጭ እየገቡ አይደለም፡፡ በጥቂቱ የመጡ ካሉም ዋጋቸው የማይቻል እየሆነ ነው፡፡  መንግሥት ራሱ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በሚፈልገው መጠንና ፍጥነት እያገኘ አይደለም፡፡ በፕሮጀክቶች ሒደትና አተገባበር የሚፈለገውን ያህል ዕድገት እያረጋገጠ አይደለም፡፡ ይህ ማለት ዕድገት ቆመ አይደለም፡፡ ዕድገት አሁንም አለ፡፡ በተፈለገው ጊዜ ሊዳሰስና ሊጨበጥ የሚፈለገው የገንዘብ መጠን ግን በእጁ እየገባ አይደለም፡፡  የውጭ ኢንቨስተሮች አስፈላጊውን ፈጣን መስተንግዶና አስተዳደር እያገኘን አይደለም እያሉ እያማረሩ ነው፡፡ የጀመርነው ኢንቨስትመንት ተቋረጠ፣ አሸንፋችኋል ከተባልን በኋላ እንደገና ጨረታ ይወጣል ተባልን፣ አቁሙ ተብለናል፣ መልስ የሚሰጠን አጣን እያሉ እያማረሩ ናቸው፡፡ ገንዘብ መደበቅና ማሸሽ እየተለመደ ነው የሚል አጀንዳ ወደ መድረክ እየመጣ ነው፡፡ ባንክ ከማስቀመጥ ይልቅ በእጅ መያዝ እየተመረጠ ነው፡፡ አገር ውስጥ ከማስቀመጥ ይልቅ ውጭ መላክ ተመራጭ ሆኗል እየተባለ ነው፡፡ አገር ውስጥ ባለው የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ ተጨማሪ ጉልበት ሊፈጥር የሚገባው የውጭ ምንዛሪ ግኝትም ውጭ እንዲቀር እየተደረገ ነው፡፡ የገባ ካለም በጥቁር ገበያ እንደገና እንዲወጣ እየተደረገ በመሆኑ አገሪቱ ተጠቃሚ መሆን አልቻለችም፡፡  እኔ ንፁህ

በሕገ መንግሥት የተረጋገጠ መብት በባለሥልጣናት ሲጣስ!

አዲስ አድማስ ባለፈው ሳምንት እትም ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች በአንድ ቀን መጠራታቸውን አስመልክቶ ባቀረበው ዘገባ፣ የጠቀሳቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር “የሚጠበቅብን ማሳወቅ ነው፤ ይህንኑ በወቅቱ ፈጽመናል” ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ደግሞ “ማሳወቅ ብቻ አይበቃም፣ ማስፈቀድ ያስፈልጋል” ማለታቸውን አስነብቦናል፡፡ ሁለቱም በአንድ ሀገር የሚኖሩ፣ በአንድ ህግ የሚተዳደሩ ናቸውና ለተናገሩት ዋቢ የሚያደርጉት የትኛውን አዋጅና የትኛውን አንቀጽ እንደሆነ መጠየቅ ቢቻል አንባቢያን በቂ ግንዛቤ በጨበጡ ነበር፡፡  አቶ ሽመልስ ዳኛም አቃቤ ህግም ሆነው የሰሩ እንደመሆናቸው ስለ ሕገ መንግሥቱም ሆነ ስለሌሎች አዋጆች ከሌላው ሰው በተሻለ ግንዛቤ ይኖራቸዋልና ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ ፈቃድ መጠየቅን የግድ የሚያደርጉትን ህጎች ቢገልጿቸው ሁሉም በቂ ግንዛቤ ይዞ በህጉ አግባብ በመሄድ አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ ባልተገባ፣ ፖሊስም መሀል ቤት ከመቸገር በዳነ ነበር፡፡  እስካሁን የምንሰማውም የምናውቀውም መሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን አስመልክቶ የሚጠቀሱት የህገ መንግሥቱ አንቀጽ 30/1 እና የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ስርዓት አዋጅ ቁ.31/1983 ናቸው፡፡  “የመሰብሰብ፤ ሠላማዊ ሰልፍ የማድረግና አቤቱታ የማቅረብ መብት” በሚል ርዕስ በሁለት ንዑሳን አንቀጾች የተገለጸው የህገ መንግሥቱ አንቀጽ 30 ንዑስ አንቀጽ 1 “ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሠላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ከቤት ውጪ የሚደረጉ ስብሠባዎችና ሰላማዊ ሠልፎች በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች በሕዝብ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ ወይም በመካሄድ ላይ ያለ ስብ