Posts

የሪፖርተር ጋዜጣ በውሽት ዜና ብዙዎችን ማስደሰቱን ኣመነ፦ የደቡብ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነታቸው አልተነሱም

የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትን በምክትል ርዕሰ መስተዳደርነት ከሚመሩት አራት ኃላፊዎች መካከል ሦስቱ ከኃላፊነታቸው ተነሱ በሚል ባለፈው ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. የተጻፈው ዘገባ ስህተት መሆኑን እየገለጽን፣ ሦስቱም በኃላፊነታቸው ላይ መሆናቸውን እናስታውቃለን፡፡ አሁንም በኃላፊነታቸው ላይ ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ታገሠ ጫፎ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲ ናቸው፡፡  የደቡብ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ዘገባው ፍፁም የተሳሳተና የክልሉ መንግሥት የማያውቀው በመሆኑ የክልሉን መንግሥትና ሕዝብ አሳዝኗል፡፡ ‹‹ይህ የተሳሳተ ዘገባ የወጣው የክልሉ መንግሥት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን በአንድ መንፈስ እያካሄዱበት በሚገኝበት ወቅት መሆኑ፣ ዘገባውን እጅግ የሚያሳዝንና የሚያስገርም ከማድረግ ባሻገር ይህ ተግባር በክልሉ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ ልማትና የሕዝብ ተጠቃሚነት ይጐዳል፤›› ሲል የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡  በወቅቱ ዘገባውን ያቀረበው የክልሉ የሪፖርተር ልዩ ዘጋቢ መረጃ በመሰብሰብ፣ በማጠናቀርና ዘገባውን በማቅረብ ሒደት ላይ ስህተት መሥራቱን የዝግጅት ክፍሉ በመረዳቱ፣ ዘጋቢውን በማገድና በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ማጣራት አድርጎ ተገቢውን ዕርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ሆኖም ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. በወጣው ዕትም የተዘገበው ስህተት መሆኑን እየገለጽን የክልሉን መንግሥት፣ ሦስቱን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮችንና አንባቢያንን ከ

ኢኮኖሚውና ቢዝነሱ ‹‹ግሉኮስ›› ያስፈልገዋል

Image
ኢኮኖሚያችንና የቢዝነስ እንቅስቃሴያችን እየፈዘዘ ነው፡፡ ቀዝቀዝ ብሏል፡፡ አተነፋፈሱ ጥሩ አይመስልም፡፡የገንዘብ እንቅስቃሴ እንደነበረው አይደለም፡፡ ክፍያዎች እየዘገዩ ናቸው፡፡ በባንኮችና በደንበኞች መካከል ጠንካራ ግንኙነት የለም፡፡ ባንኮቹ በተለይም የግል ባንኮች እየተዳከሙ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት የገንዘብ እንቅስቃሴ ሙትት እያለ ነው፡፡ በውጭ ምንዛሪ ችግርና እጥረት ምክንያት በጣም የሚያስፈልጉ ዕቃዎች እንደተለመደው ከውጭ እየገቡ አይደለም፡፡ በጥቂቱ የመጡ ካሉም ዋጋቸው የማይቻል እየሆነ ነው፡፡  መንግሥት ራሱ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በሚፈልገው መጠንና ፍጥነት እያገኘ አይደለም፡፡ በፕሮጀክቶች ሒደትና አተገባበር የሚፈለገውን ያህል ዕድገት እያረጋገጠ አይደለም፡፡ ይህ ማለት ዕድገት ቆመ አይደለም፡፡ ዕድገት አሁንም አለ፡፡ በተፈለገው ጊዜ ሊዳሰስና ሊጨበጥ የሚፈለገው የገንዘብ መጠን ግን በእጁ እየገባ አይደለም፡፡  የውጭ ኢንቨስተሮች አስፈላጊውን ፈጣን መስተንግዶና አስተዳደር እያገኘን አይደለም እያሉ እያማረሩ ነው፡፡ የጀመርነው ኢንቨስትመንት ተቋረጠ፣ አሸንፋችኋል ከተባልን በኋላ እንደገና ጨረታ ይወጣል ተባልን፣ አቁሙ ተብለናል፣ መልስ የሚሰጠን አጣን እያሉ እያማረሩ ናቸው፡፡ ገንዘብ መደበቅና ማሸሽ እየተለመደ ነው የሚል አጀንዳ ወደ መድረክ እየመጣ ነው፡፡ ባንክ ከማስቀመጥ ይልቅ በእጅ መያዝ እየተመረጠ ነው፡፡ አገር ውስጥ ከማስቀመጥ ይልቅ ውጭ መላክ ተመራጭ ሆኗል እየተባለ ነው፡፡ አገር ውስጥ ባለው የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ ተጨማሪ ጉልበት ሊፈጥር የሚገባው የውጭ ምንዛሪ ግኝትም ውጭ እንዲቀር እየተደረገ ነው፡፡ የገባ ካለም በጥቁር ገበያ እንደገና እንዲወጣ እየተደረገ በመሆኑ አገሪቱ ተጠቃሚ መሆን አልቻለችም፡፡  እኔ ንፁህ

በሕገ መንግሥት የተረጋገጠ መብት በባለሥልጣናት ሲጣስ!

አዲስ አድማስ ባለፈው ሳምንት እትም ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች በአንድ ቀን መጠራታቸውን አስመልክቶ ባቀረበው ዘገባ፣ የጠቀሳቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር “የሚጠበቅብን ማሳወቅ ነው፤ ይህንኑ በወቅቱ ፈጽመናል” ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ደግሞ “ማሳወቅ ብቻ አይበቃም፣ ማስፈቀድ ያስፈልጋል” ማለታቸውን አስነብቦናል፡፡ ሁለቱም በአንድ ሀገር የሚኖሩ፣ በአንድ ህግ የሚተዳደሩ ናቸውና ለተናገሩት ዋቢ የሚያደርጉት የትኛውን አዋጅና የትኛውን አንቀጽ እንደሆነ መጠየቅ ቢቻል አንባቢያን በቂ ግንዛቤ በጨበጡ ነበር፡፡  አቶ ሽመልስ ዳኛም አቃቤ ህግም ሆነው የሰሩ እንደመሆናቸው ስለ ሕገ መንግሥቱም ሆነ ስለሌሎች አዋጆች ከሌላው ሰው በተሻለ ግንዛቤ ይኖራቸዋልና ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ ፈቃድ መጠየቅን የግድ የሚያደርጉትን ህጎች ቢገልጿቸው ሁሉም በቂ ግንዛቤ ይዞ በህጉ አግባብ በመሄድ አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ ባልተገባ፣ ፖሊስም መሀል ቤት ከመቸገር በዳነ ነበር፡፡  እስካሁን የምንሰማውም የምናውቀውም መሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን አስመልክቶ የሚጠቀሱት የህገ መንግሥቱ አንቀጽ 30/1 እና የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ስርዓት አዋጅ ቁ.31/1983 ናቸው፡፡  “የመሰብሰብ፤ ሠላማዊ ሰልፍ የማድረግና አቤቱታ የማቅረብ መብት” በሚል ርዕስ በሁለት ንዑሳን አንቀጾች የተገለጸው የህገ መንግሥቱ አንቀጽ 30 ንዑስ አንቀጽ 1 “ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሠላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ከቤት ውጪ የሚደረጉ ስብሠባዎችና ሰላማዊ ሠልፎች በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች በሕዝብ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ ወይም በመካሄድ ላይ ያለ ስብ

በግንባታ ላይ ያለው የሃዋሳ ስታዲዬም

Image

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ጥቅምት 16 /2006 ይጀመራል

Image
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የፕሪሚየር ሊግ እና የብሔራዊ ሊግ ክለብ ተወካዮች በተገኙበት በክለቦች መተዳደሪያ ደንብና የዲስፕሊን መመሪያዎች ማሻሻያ ላይ ዛሬ ነሐሴ 29/2005 በኢትዮጵያ ሆቴል ውይይት አካሄደ፡፡ የፌደሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በመተዳደሪያ ደንቡና በዲስፕሊን መመሪያው ያቀረባቸው ማሻሻያዎች ተገቢ መሆናቸውን የየክለቦቹ ተወካዮች ተናግረዋል፡፡ የተሸሻለው መመሪያ በጠቅላላ ጉባኤው ፀድቆ በስራ ላይ ሲውል በባለፉት ዓመታት በውድድሩ የተከሰቱ ችግሮችን እንደሚቀርፍ እምነታቸው መሆኑን የየክለቦቹ ተወካዮች ገልፀዋል፡፡ በሀገር ውስጥ የተጨዋቾች ዝውውር መንግስት እያጣው ያለው ግብር በተሻሻለው የዲስፕሊን መመሪያ ላይ እንደሚስተካከልም ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለቦች የ2006 የውድድር ዘመን ጨዋታ የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓትም በእለቱ ተካሂዷል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ መርሃ ግብር ጥቅምት 16 የሚጀምር ሲሆን በመጀመሪያው ሳምንት ደደቢት ከኢትዮጵያ ቡና የተገናኙበት ጨዋታ ከወዲሁ ትኩረትን ስቧል፡፡ ደደቢት በ2005 የውድድር ዘመን ፕሪሚየር ሊጉን 1ኛ በመሆን ያጠናቀቀ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ሶስተኛ ሆኖ መጨረሱ ይታወሳል፡፡ በመጀመሪያው ሳምንት ሌሎች ጨዋታዎች ሙገር ሲሚንቶ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ዳሽን ቢራ ከሀረር ቢራ፣ ኢትዮጵያ መድህን ከአርባ ምንጭ፣ መከላከያ ከሲዳማ ቡና፣ ሐዋሳ ከነማ ከመብራት ሃይል እንዲሁም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወላይታ ዲቻ ይገናኛሉ፡፡ የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ የውድድር መርሃ ግብር ዓለም አቀፋዊ ውድድሮቹንና ስታንዳርዱን ጠብቆ የተሰራ በመሆኑ በ2005 የነበረውን የሊጉ የጨዋታ መቆራረጥ ያስተካክላል ተብሏል፡፡ የተለያዩ የዓለም ሀገራት የወዳጅነትና የአቋም መለኪያ ጨዋታዎ