Posts

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ጥቅምት 16 /2006 ይጀመራል

Image
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የፕሪሚየር ሊግ እና የብሔራዊ ሊግ ክለብ ተወካዮች በተገኙበት በክለቦች መተዳደሪያ ደንብና የዲስፕሊን መመሪያዎች ማሻሻያ ላይ ዛሬ ነሐሴ 29/2005 በኢትዮጵያ ሆቴል ውይይት አካሄደ፡፡ የፌደሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በመተዳደሪያ ደንቡና በዲስፕሊን መመሪያው ያቀረባቸው ማሻሻያዎች ተገቢ መሆናቸውን የየክለቦቹ ተወካዮች ተናግረዋል፡፡ የተሸሻለው መመሪያ በጠቅላላ ጉባኤው ፀድቆ በስራ ላይ ሲውል በባለፉት ዓመታት በውድድሩ የተከሰቱ ችግሮችን እንደሚቀርፍ እምነታቸው መሆኑን የየክለቦቹ ተወካዮች ገልፀዋል፡፡ በሀገር ውስጥ የተጨዋቾች ዝውውር መንግስት እያጣው ያለው ግብር በተሻሻለው የዲስፕሊን መመሪያ ላይ እንደሚስተካከልም ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለቦች የ2006 የውድድር ዘመን ጨዋታ የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓትም በእለቱ ተካሂዷል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ መርሃ ግብር ጥቅምት 16 የሚጀምር ሲሆን በመጀመሪያው ሳምንት ደደቢት ከኢትዮጵያ ቡና የተገናኙበት ጨዋታ ከወዲሁ ትኩረትን ስቧል፡፡ ደደቢት በ2005 የውድድር ዘመን ፕሪሚየር ሊጉን 1ኛ በመሆን ያጠናቀቀ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ሶስተኛ ሆኖ መጨረሱ ይታወሳል፡፡ በመጀመሪያው ሳምንት ሌሎች ጨዋታዎች ሙገር ሲሚንቶ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ዳሽን ቢራ ከሀረር ቢራ፣ ኢትዮጵያ መድህን ከአርባ ምንጭ፣ መከላከያ ከሲዳማ ቡና፣ ሐዋሳ ከነማ ከመብራት ሃይል እንዲሁም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወላይታ ዲቻ ይገናኛሉ፡፡ የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ የውድድር መርሃ ግብር ዓለም አቀፋዊ ውድድሮቹንና ስታንዳርዱን ጠብቆ የተሰራ በመሆኑ በ2005 የነበረውን የሊጉ የጨዋታ መቆራረጥ ያስተካክላል ተብሏል፡፡ የተለያዩ የዓለም ሀገራት የወዳጅነትና የአቋም መለኪያ ጨዋታዎ

ሪፖርተር ጋዜጣ 3 ምክትል ርእሰ መስተዳድሮች ከሃላፊነታቸው ተነሱ በማለት ያወጣው ዘገባ መሰረተ ቢስ ነው-የደቡብ ክልል

Image
ሪፖርተር ጋዜጣ በነሃሴ 29/2005 እትሙ “ የደቡብ ክልል 3 ምክትል ርእሰ መስተዳድሮች ከሃላፊነታቸው ተነሱ”  በማለት ያወጣው ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ መግለጫው የክልሉ መንግስት የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራትን በአንድ መንፈስ እያካሄደ በሚገኝበት ወቅት ጋዜጣው ይህን መሰል መሰረተ ቢስ ዘገባ ማሰራጨቱ  አሳዛኝ ድርጊት ነው ብሏል፡፡ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ የሀገሪቱን ህጎች የሚፃረር በመሆኑ የክልሉ መንግስት ተግባሩን የፈፀሙት አካላት ህጉን በሚያዘው መሰረት ተከታትሎ  ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጿል፡፡ ምንጭ፡- የደቡብ ክልል የመንግስት ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ምንጨ ፦ http://www.ertagov.com/amharic/index.php/component/k2/item/1964-%E1%8B%A8%E1%88%AA%E1%8D%96%E1%88%AD%E1%89%B0%E1%88%AD-%E1%8C%8B%E1%8B%9C%E1%8C%A3-%E1%8B%A8%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%89%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%98%E1%88%AB%E1%88%AE%E1%89%BD-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%88%98%E1%88%88%E1%8A%A8%E1%89%B0-%E1%8B%AB%E1%8B%88%E1%8C%A3%E1%8B%8D-%E1%8B%98%E1%8C%88%E1%89%A3-%E1%88%98%E1%88%B0%E1%88%A8%E1%89%B0-%E1%89%A2%E1%88%B5-%E1%8A%90%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8B%B0-%E1%89%A5-%E1%89%A5%E1%88%84%E1%88%A8%E1%88%B0%E1%89%A6%E1%89%BD%E1%8A%93-%E1%88%85%E1%8B%9D%E1%89%A6%E1%89%BD-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሸኛኘት ተደረገለት

Image
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ ቅዳሜ ከሴንትራል ሪፐብሊክ አፍሪካ የሚያካሂደውን ወሳኝ ጨዋታ በቂ ዝግጅት እንዳደረገ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ነሀሴ 29/2005 በተካሄደው የአሸኛኘኘትና የሽልማት  ስነ-ስርአት አሰልጣኝ ሰውነት እንዳሉት ብሄራዊ ቡድኑ  አሸንፎ ለማለፍ ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡   የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት ሳህሉ ገብረወልድ በበክላቸው  ቡድኑ አባላት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገውን ውጤት በማስመዝገብ  አዲስ ታሪክ ለማስመዝገብ  አስፈላጊው ጥረት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

የ‹‹ሜትሮ ፖሊታን›› ደራሲ ከስልጣን ተባረሩ

Image
‹‹ሜትሮ ፖሊታን›› የተሰኘውንና የሐዋሳ ከተማ አስተዳዳር 70/30 (ሰባ በመቶ ብሔር ብሔረሰቦች ተዋፅኦ፣ ሰላሳ በመቶ በሲዳማ ተወላጆች እንዲዋቀር) ባለፈው ሚያዚያ 2004 ዓ.ም. አዘጋጅተው ለውይይት ያቀረቡት  አቶ አለማየሁ አሰፋ ከስልጣን ተባረሩ፤ ዝርዝር ዜናውን ከታች ያንቡ፦ የደቡብ ክልልን ከሚመሩት አራቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች መካከል ሦስቱ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ ለሦስቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መነሳት ከነሐሴ 15 እስከ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተደረገው ግምገማ ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ለእያንዳንዳቸው መነሳት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካከል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ከሆኑ አንድ ዓመት ያልሞላቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ሲሆኑ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና በተመሳሳይ ማዕረግ  የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲ ናቸው፡፡ የአቶ አለማየሁ አሰፋና የአቶ ታገሠ ጫፎ መነሳት የተጠበቀና ውስጥ ለውስጥ ሲነገር የቆየ መሆኑን፣ ያልተጠበቀው ግን የአቶ ሳኒ ረዲ ነበር በማለት አስተያየት የሰጡት የደኢሕዴን አባልና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የክልሉ ባለሥልጣን፣ ሦስቱም ሹማምንት የተገመገሙት በተለያዩ ችግሮች እንደሆነ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ‹‹አቶ ታገሠ በአመራር ብቃት ማነስ በተደጋጋሚ ይተቹ እንደነበር ገልጸው፣ አቶ አለማየሁና አቶ ሳኒ ደግሞ አላስፈላጊ ‹‹ኔትወርክ›› በመፍጠር ብልሹ አሠራር በማስፈናቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡  በግምገማው የተሳተፉ ምንጮች ደግሞ በተለይ አቶ አለማየሁ ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ በተወከሉበት ዳውሮ ዞን ከፍተኛ ተቃውሞ ሲነሳባቸው የኃይል ዕርምጃ እንዲወሰድ

የደቡበ ክልል ሦስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ከኃላፊነት ተነሱ

Image
የደቡብ ክልልን ከሚመሩት አራቱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች መካከል ሦስቱ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ ለሦስቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መነሳት ከነሐሴ 15 እስከ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተደረገው ግምገማ ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ለእያንዳንዳቸው መነሳት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካከል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ከሆኑ አንድ ዓመት ያልሞላቸው አቶ ታገሠ ጫፎ ሲሆኑ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አሰፋና በተመሳሳይ ማዕረግ  የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲ ናቸው፡፡ የአቶ አለማየሁ አሰፋና የአቶ ታገሠ ጫፎ መነሳት የተጠበቀና ውስጥ ለውስጥ ሲነገር የቆየ መሆኑን፣ ያልተጠበቀው ግን የአቶ ሳኒ ረዲ ነበር በማለት አስተያየት የሰጡት የደኢሕዴን አባልና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የክልሉ ባለሥልጣን፣ ሦስቱም ሹማምንት የተገመገሙት በተለያዩ ችግሮች እንደሆነ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ‹‹አቶ ታገሠ በአመራር ብቃት ማነስ በተደጋጋሚ ይተቹ እንደነበር ገልጸው፣ አቶ አለማየሁና አቶ ሳኒ ደግሞ አላስፈላጊ ‹‹ኔትወርክ›› በመፍጠር ብልሹ አሠራር በማስፈናቸው ነው፤›› ብለዋል፡፡  በግምገማው የተሳተፉ ምንጮች ደግሞ በተለይ አቶ አለማየሁ ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ በተወከሉበት ዳውሮ ዞን ከፍተኛ ተቃውሞ ሲነሳባቸው የኃይል ዕርምጃ እንዲወሰድ ማድረጋቸው እንደ አንድ ምክንያት መነሳቱን ያስረዳሉ፡፡ በሌላ በኩል የክልሉ የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑ አንዳንድ አስተያት ሰጪዎች ለሦስቱም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከኃላፊነት መነሳት የአመራር ብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን የኪራይ ሰብሳቢነትና የሙስና ችግሮች መኖራቸውን ይገልጻሉ፡፡  በሥነ