Posts

በመላው አለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች፣ቆንስል ጄኔራሎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እየመከሩ ነው

Image
አዲስ አበባ ነሐሴ 27/2005 በመላው አለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች፣ቆንስል ጄኔራሎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አዲስ አበባ ውስጥ እየመከሩ ነው። ለአንድ ሳምንት የሚቆየውን የምክከር መድረክ የከፈቱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሐኖም አንዳሉት በዲፕሎማሲ ሰራዊት ግንባታ፣በቢዝነስ ዲፕሎማሲ፣በንግድ፣በቴክኖሎጂ ሽግግር፣በኢንቨስመንት፣ብድርና እርዳታ በማፈላለግ፣በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን በማንቀሳቀስ፣ በባህልና ቱሪዝም ረገድ አምባሳደሮቹ ያከናወኗቸውን ተግባራት በተመለከተ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በስፋት ይገመግማሉ። ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅምና ሰላም እኳያ ከጎረቤት አገሮች ጋር ያለው ግንኙነት በተለይም ከሁለቱ ሱዳኖች ከግብጽና ከሶማሊያ ጋር በተያያዘ ጥልቅ ውይይት ይካሄዳል ብለዋል። በስራ አፈጻጸማቸው መልካም ተመክሮ ያላቸው ኤምባሲዎች ልምዳቸውን ለሌሎች የሚያካፍሉበት ልዩ መድረክም ተመቻችቷል። ኢዜአ ያነጋገራቸው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ቋሚ መልእክተኛ ዶክተር ተቀዳ አለሙ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ የአገሪቱን ጥቅም ከማራመድ ባሻገር የአካባቢውን አገራት እና የአፍሪካን ጥቅም በሚገባ የምታስከብር አገር ስለመሆኗ ጠንካራ አመኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ህብረት ሊመቀንበር በመሆኗ የአህጉሪቱን ጥቅም ለማስከበር በመርህ ላይ ተመስርታ ጠንካራ እንቅስቃሴ እያደረገች በመሆኗ በመንግስታቱ ድርጅትና በአፍሪካ አገራት ዘንድ ያላት ተቀባይነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ጥቅምና ወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለመመሰረት የበርካታ አገራት ፍላጎት መሆኑንም ጠቁመዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍ

ፉራ የልማት ምርምር ማዕከል ከየት ደረሰ? በምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው? መረጃ ያላችሁ ሰዎች ኣጋሩን

Image
New

Fichchee – Sidama People’s New year and Tradition – Best Documentary

A documentary video about the Sidama New Year, Fichchee Chembelala : Celebration, Culture and Tradition in Sidamo, Ethiopia.  Fichchee – Sidama People’s New year and Tradition – Documentaryition-documentary/

የፋይናንሰ ግልጸኝነትን ለማስፈን የወጡ ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ አይተገበሩም ተባለ

Image
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 24 ፣ 2005 ( ኤፍ.ቢ.ሲ ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንሰ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፋይናንሰ ግልጸኝነትን ለማስፈን የሚሰራውን ሰራ ለማሳካት በመስኩ የወጡ ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ አንዲተገበሩ አሳሰበ። በፋይናንስ ግልጸኝነት ዙሪያ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አዳራሽ ዛሬ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ ላይ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ ገነት ታደስ እንዳሉት ፥ ኢትዮጵያ ከፋይናንስ አሰራሯ ጋር በተያያዘ ተግባራዊ ያደረገቻቸው ህጎችና መመሪያዎች አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን እና በዚህ ረገድ እየተከናወነ ያለው ስራ በየጊዜው ለውጥ እየታየበት መሆኑን አንስተዋል። ይሁንና ህጎች በአግባቡ አለመተግበርም እየታዩ ያሉ ችግሮች በመሆናቸው የወጡትን ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ በመተግበር ረገድ የሚመለከታቸው ሁሉ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ነው ያሳሰቡት። በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የፋይናንስ ግልጽኝነትና ተጠያቂነት ቡድን መሪ አቶ አለባቸው በላይነህ በበኩላቸው ፥ የፋይናነስ ግልጸኝነትን ለማስፈን በሚሰራው ስራ ሰፊ የግንዛቤ ማስፊያ ስራዎች እየተከናወነ ነው ብለዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተቋማት ችግሮቹ ሳይፈጠሩ በፊት ማከናወን የሚገባቸውን ሁሉ በአግባቡ መወጣት አለባቸው ነው ያሉት ህብረተሰቡም ከሚበጀቱ ፋይናንሶች ጋር በተያያዘ በየጊዜው ግንዛቤው እያደገ መምጣቱን በማንሳት ። የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ፣ የፌዴራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም የተለያዩ ክልሎች የሚመለከታቸው አካላት የስራ ሀላፊዎች  በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተዋል።

አወዛጋቢው የይዞታ ረቂቅ መመርያ አስተያየት እንዲሰጥበት ለከተማ ልማት ሚኒስቴር ተላከ

ሕ ገወጥ ባለይዞታዎችን ሕጋዊ የሚያደርገው አወዛጋቢው ረቂቅ መመርያ አስተያየት እንዲሰጥበት ለከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተላከ፡፡ የ62 ሺሕ ባለይዞታዎች ቀጣይ ዕጣ ፈንታን የሚወስነው ይህ መመርያ በርካታ ውይይቶች ተካሂደውበት ለውሳኔ ቢቀርብም፣ በከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል መግባባት ላይ ባለመደረሱ ሲንከባለል ቆይቷል፡፡  በሕገወጥ ባለይዞታነት ከሚፈረጁት መካከል 44 ሺሕ የሚሆኑት መንግሥት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች በሰነድ ክፍያ የሚፈጽሙ ሲሆኑ፣ 18 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ምንም ዓይነት ሰነድ የሌላቸው ናቸው ተብሏል፡፡  የሊዝ አዋጁን እንዲያስፈጽም በወጣው ደንብ ሕገወጥ ባለይዞታዎች በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሕጋዊ የሚሆኑበትና ከተሞች እንደነባራዊ ሁኔታቸው ሕጋዊ የማድረጉ ተግባር እንደሚከናወን ተደንግጓል፡፡ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ1988 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 2004 ዓ.ም. ድረስ በሕገወጥ መንገድ የተያዙ ይዞታዎችን ሕጋዊ ለማድረግ ረቂቅ መመርያ አዘጋጅቷል፡፡ ነገር ግን እስከ ኅዳር 2004 ዓ.ም. ድረስ የተገነቡ ቤቶችን ሕጋዊ ማድረግ በባለሥልጣናት መካከል አለመግባባት መፍጠሩን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ በሌላ በኩል በግንቦት 1997 ዓ.ም. ከተካሄደው ምርጫ በኋላ የከተማው አስተዳደር የሥልጣን ሽግግር በሚያካሂድበት ወቅት ከፍተኛ የመሬት መቀራመት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የነበረው የከተማው ባለአደራ አስተዳደር ከዚያ በኋላም ሥልጣኑን የተረከበው የከተማው አስተዳደር ግብረ ኃይል በማቋቋም ሕገወጥ ያሏቸውን ግንባታዎች አፍርሰዋል፡፡ ባለሙያዎች እንደሚሉት ዕርምጃ በሚወሰድበት ወቅት ዕርምጃ ሊወሰድባቸው የሚገቡ፣ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች የተዘለሉ በርካታ ይዞታዎች በአዲሱ መመርያ ሕጋዊ