Posts

የፋይናንሰ ግልጸኝነትን ለማስፈን የወጡ ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ አይተገበሩም ተባለ

Image
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 24 ፣ 2005 ( ኤፍ.ቢ.ሲ ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንሰ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፋይናንሰ ግልጸኝነትን ለማስፈን የሚሰራውን ሰራ ለማሳካት በመስኩ የወጡ ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ አንዲተገበሩ አሳሰበ። በፋይናንስ ግልጸኝነት ዙሪያ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አዳራሽ ዛሬ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ ላይ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ ገነት ታደስ እንዳሉት ፥ ኢትዮጵያ ከፋይናንስ አሰራሯ ጋር በተያያዘ ተግባራዊ ያደረገቻቸው ህጎችና መመሪያዎች አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን እና በዚህ ረገድ እየተከናወነ ያለው ስራ በየጊዜው ለውጥ እየታየበት መሆኑን አንስተዋል። ይሁንና ህጎች በአግባቡ አለመተግበርም እየታዩ ያሉ ችግሮች በመሆናቸው የወጡትን ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ በመተግበር ረገድ የሚመለከታቸው ሁሉ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ነው ያሳሰቡት። በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የፋይናንስ ግልጽኝነትና ተጠያቂነት ቡድን መሪ አቶ አለባቸው በላይነህ በበኩላቸው ፥ የፋይናነስ ግልጸኝነትን ለማስፈን በሚሰራው ስራ ሰፊ የግንዛቤ ማስፊያ ስራዎች እየተከናወነ ነው ብለዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተቋማት ችግሮቹ ሳይፈጠሩ በፊት ማከናወን የሚገባቸውን ሁሉ በአግባቡ መወጣት አለባቸው ነው ያሉት ህብረተሰቡም ከሚበጀቱ ፋይናንሶች ጋር በተያያዘ በየጊዜው ግንዛቤው እያደገ መምጣቱን በማንሳት ። የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ፣ የፌዴራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም የተለያዩ ክልሎች የሚመለከታቸው አካላት የስራ ሀላፊዎች  በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተዋል።

አወዛጋቢው የይዞታ ረቂቅ መመርያ አስተያየት እንዲሰጥበት ለከተማ ልማት ሚኒስቴር ተላከ

ሕ ገወጥ ባለይዞታዎችን ሕጋዊ የሚያደርገው አወዛጋቢው ረቂቅ መመርያ አስተያየት እንዲሰጥበት ለከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተላከ፡፡ የ62 ሺሕ ባለይዞታዎች ቀጣይ ዕጣ ፈንታን የሚወስነው ይህ መመርያ በርካታ ውይይቶች ተካሂደውበት ለውሳኔ ቢቀርብም፣ በከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል መግባባት ላይ ባለመደረሱ ሲንከባለል ቆይቷል፡፡  በሕገወጥ ባለይዞታነት ከሚፈረጁት መካከል 44 ሺሕ የሚሆኑት መንግሥት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች በሰነድ ክፍያ የሚፈጽሙ ሲሆኑ፣ 18 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ምንም ዓይነት ሰነድ የሌላቸው ናቸው ተብሏል፡፡  የሊዝ አዋጁን እንዲያስፈጽም በወጣው ደንብ ሕገወጥ ባለይዞታዎች በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሕጋዊ የሚሆኑበትና ከተሞች እንደነባራዊ ሁኔታቸው ሕጋዊ የማድረጉ ተግባር እንደሚከናወን ተደንግጓል፡፡ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ1988 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 2004 ዓ.ም. ድረስ በሕገወጥ መንገድ የተያዙ ይዞታዎችን ሕጋዊ ለማድረግ ረቂቅ መመርያ አዘጋጅቷል፡፡ ነገር ግን እስከ ኅዳር 2004 ዓ.ም. ድረስ የተገነቡ ቤቶችን ሕጋዊ ማድረግ በባለሥልጣናት መካከል አለመግባባት መፍጠሩን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ በሌላ በኩል በግንቦት 1997 ዓ.ም. ከተካሄደው ምርጫ በኋላ የከተማው አስተዳደር የሥልጣን ሽግግር በሚያካሂድበት ወቅት ከፍተኛ የመሬት መቀራመት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የነበረው የከተማው ባለአደራ አስተዳደር ከዚያ በኋላም ሥልጣኑን የተረከበው የከተማው አስተዳደር ግብረ ኃይል በማቋቋም ሕገወጥ ያሏቸውን ግንባታዎች አፍርሰዋል፡፡ ባለሙያዎች እንደሚሉት ዕርምጃ በሚወሰድበት ወቅት ዕርምጃ ሊወሰድባቸው የሚገቡ፣ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች የተዘለሉ በርካታ ይዞታዎች በአዲሱ መመርያ ሕጋዊ

አምስተኛው የከተሞች ሳምንት በባህር ዳር ይከበራል፤ ከሲዳማ ከተሞች ምን ይጠበቃል?

Image
የሲዳማ ከተሞች ከሆኑት ኣለታ ወንዶ፤ ዳሌ-ይርጋኣለም እና ከሃዋሳ በዘንድሮው ኣገር ኣቀፍ የከተሞች ውድድይ ምን ይጠበቃል? ዝግጅታቸው ምን ይመስላል? መረጃ ያላችሁ ሰዎች ተጋሩን። አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 24 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስተኛው የከተሞች ሳምንት  በ2006 ዓ.ም  ከህዳር 11 አሰከ 17 በባህር ዳር ከተማ ሊከበር ነው። በአሉም  "ከተሞቻችን  የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማእከላት በመሆን የመለስን ሌጋሲ ያስቀጥላሉ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል። ለበአሉ አከባበር ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናቸውንም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴርና የባህርዳር ከተማ አስተዳደር  ዛሬ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።  ለዚሁም በአሉ የሚመራበትን መሪ እቅድ ተዘጋጅቷል፤ ዝግጅቱን የሚያስተባብሩ የተለያዩ አደረጃጀቶችም በፌደራል፣ በክልሉ መንግስትና  በከተማዋ አስተዳደር ደረጃ ተቋቁሟል።  የበአሉ አላማም በከተሞች መካከለ ውድድርን መፍጠርና የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡትን በማበረታታት ለሌሎች ከተሞች አርአያ አንዲሆኑ ማድረግ ነው።  ከ17 ሺ በላይ ህዝቦች ያሉዋቸው ከ150 በላይ ከተሞች በባአሉ ይሳተፋሉም ተብሎ ይጠበቃል።  አራተኛው የከተሞች ሳምንት በያዝነው አመት 132 ከተሞችን በማሳተፍ  በአዳማ ከተማ መከበሩ ይታወሳል። http://www.fanabc.com/index.php?option=com_content&view=article&id=5186:2013-08-30-08-26-30&catid=103:2012-08-02-12-34-36&Itemid=235

Poultry for smallholder women, Sidama Southern Nations, Nationalities, and People's Region, Ethiopia

Image
http://www.flickr.com/photos/ilri/8242923977/ New

በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በ2006 ዓ.ም የዲግሪና የመሰናዶ መርሃ ግብር የተማሪዎች መግቢያ መቁረጫ ነጥብን ይፋ ሆነ መልካም እድል ለሲዴ ልጆች

Image
አዲስ አበባ ነሐሴ 24/2005 የትምህርት ሚኒስቴር የ2006 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በዲግሪና በመሰናዶ መርሃ ግብር የተማሪዎች መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ አደረገ። በአዲሱ የትምህርት ዘመን 132 ሺህ 215 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ማግኘታቸውና ከእነዚሁ መካከል ደግሞ 103 ሺሀ 385ቱ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት ማዕቀፍ እንደሚመደቡ ተገልጿል። ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በትምህርት ዘመኑ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በዲግሪ መርሃ ግብር ገብተው ሊማሩ የሚችሉት ተማሪዎች 265 እና ከዛ በላይ ነጥብ ያመጡ ናቸው። ነጥቡ የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅን፣ ኢኮኖሚው የሚፈልገውን የሰው ኃይልና የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም ግምት ውስጥ ያስገባ እንደሆነ ነው የተገለጸው። በዚሁ መሰረት በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ሁሉም መደበኛ ወንድ ተማሪዎች 325 እና ከዛ በላይ ሴቶች ደግሞ 305 እና ከዛ በላይ፣ ለታዳጊ ክልልና ለአርብቶ አደር ልጆች ወንዶች 305 እና ከዛ በላይ ሴቶች 300 እና ከዛ በላይ ያመጡ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይደለደላሉ። በተመሳሳይ የግል ተፈታኝ የሆኑ ወንዶች 330 እና ከዛ በላይ ሴቶች 320 እና ከዛ በላይ ካመጡ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይደለደላሉ እንደሚደለደሉ ተገልጿል። በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ መደበኛ ተማሪዎች ወንዶች 285 እና ከዛ በላይ ሴቶች 280 እና ከዛ በላይ፣ ለታዳጊ ክልልና ለአርብቶ አደር ልጆች ወንዶች 275 እና ከዛ በላይ ሴቶች 270 እና ከዛ በላይ ነጥብ ያመጡ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚደለደሉ ታውቋል። ለሁሉም መስማት የተሳናቸው 270 እና ከዛ በላይ፣ ማየት የተሳናቸው 230 እና ከዛ በላይ እንዲሁም ሁሉም የግል ተፈታኞች 290 እና ከዛ በላይ