Posts

Some old BOOK

Image
History of the Sidama Haile Sellassie I University Read more on :  http://books.google.com.pe/books?id=rNeEGwAACAAJ&dq=sidama&hl=en&sa=X&ei=HVkfUo3kJoa5sQSkrIDgDA&ved=0CE4Q6AEwCA

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

Image
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ማለፊያ ነጥብ ውጤትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የዩኒቨርስቲ መግቢያና ወደ መሰናዶ ማለፊያ ነጥብን ለመወሰን  ፥ የዩኒቨርስቲዎችን ቀጣይ የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። በአጠቃላይ 548 ሺህ 138 ተማሪዎች የ10 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ወስደው 70 በመቶዎቹ 2 ነጥብ እና ካዛ በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ ፥ በተመሳሳይም የ12ኛ ክፍልን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ከወሰዱት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞች ከ350 ነጥብ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቀደም ሲል  የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውሷል ። በነገው እለትም የሁለቱም ፈተናዎች የመቁረጫ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

SEPDM pledges to ensure sustainable development

Image
Addis Ababa, 27 August  2013 (WIC) - South Ethiopian Peoples Democratic Movement pledges to further build sustainable development in the region. This came as SEPDM Central Committee meeting came to conclusion on 26 August.  The Central Committee made discussion as of 24 August in Hawassa on the political and organization performance of the movement. The focus was on development and good governance issues. The Committee concluded the performance of the GTP, in agriculture, employment, civil service reform and other sectors, were satisfactory. It lauded the people of the region and its members for the performance it dubbed positive.  The green development happening in the state has so far been great, it said, and it is in line with the late Meles Zenawi’s vision of doing so.  Probing into performances of the health and education sector, it appreciated the performance but demanded more to be done in those sectors to meet the targets set.  The Central Committee set out mechanism that se

ሁላችንም ጉድለታችንን አውቀን ብናስተካክል ኖሮ ኢትዮጵያችን የትና የት በደረሰች ነበር?

Image
ጉድለት መኖሩና ስህተት መፈጸም ምንጊዜም የትም ያለ ነው፡፡ ዋናው ጉዳይ ጉድለት ለምን ታየ? ስህተት ለምን ተፈጸመ? የሚለው አይደለም፡፡ ችግራችንንና ጉድለታችንን ዓይተንና መርምረን እናስተካክላለን ወይ? የሚለው ነው ዋናው ጉዳይ፣ ዋናው ቁም ነገር፡፡  መንግሥትም እንደ መንግሥት ጉድለት አለበት ስህተት ይፈጽማል፡፡ ገዥው ፓርቲም እንደ ገዥ ፓርቲ ስህተት ይፈጽማል ጉድለት አለበት፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ጉድለት አለባቸው ስህተት ይፈጽማሉ፡፡ የግል ዘርፉ ጉድለት አለበት ስህተት ይፈጽማል፡፡ ሲቪል ማኅበረሰቡም ጉድለት አለበት ስህተት ይፈጽማል፡፡ መገናኛ ብዙኃንም ስህተት ይፈጽማሉ ጉድለት አለባቸው፡፡ ግን! ነገር ግን! እነዚህ አካላት የራሳቸውን ስህተትና ጉድለት ያውቃሉ? ያያሉ? ወይስ በሌላው ስህተትና ጉድለት ላይ ብቻ ነው የሚያተኩሩት? የራሳቸውን ስህተት መረዳትና ማወቅ ብቻ ነው ወይስ ለማስተካከል ይጥራሉ? ይታገላሉ?  የእኛ ፅኑ ዕምነት ሁላችንም ስህተታችንንና ጉድለታችንን ዓይተን፣ አውቀንና አምነን ብናስተካክል አገራችን የትና የት ትደርስ ነበር የሚል ነው፡፡  መንግሥት ከቃላት ባሻገር ከልብ በተግባር በመልካም አስተዳደር ላይ በተጨባጭ የሚታየው ጉድለትና ስህተት ምንድነው? ዲሞክራሲን እውን ለማድረግ፣ ሰብዓዊ መብት ለማክበር፣ ፍትሕ ለማንገስ፣ የፕሬስ ነፃነትን ዳር ለማድረስና ሙስናን ለማስወገድ ተጨባጭ ድክመቴ ምንድነው? ብሎ ለማወቅ ቢረባረብና ለማረም ቢታገል ትልቁ የአገር ችግር ይፈታል፡፡ አመቺ የሥርዓት ግንባታ ይዘረጋል፡፡ በሁሉም መስክ ታሪካዊ ለውጥ እውን ለማድረግ ጉዞው ቀላልና ብርሃን ይሆናል፡፡  ተቃዋሚዎች ራሳቸው የትም ይኑሩ የት በመንግሥት በኩል ያለውን ጉድለት ብቻ ለማየት ከመረባረብ ባሻገር ምን ዓይነት ጉድለትና ስህተ

ከኃላፊነት የተነሱ የቤቶች ኤጀንሲ ባለሥልጣናት ያወጧቸው መመርያዎች ታገዱ

ከመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በተነሱት ከፍተኛ አመራሮች የሥልጣን ዘመን የወጡ መመርያዎችና የመሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ ትግበራዎች እንዲታገዱ ትዕዛዝ  ተሰጠ፡፡ የወጡት መመርያዎችና የመሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ ጥናቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የተሠሩ ሥራዎች በሙሉ እንዲታገዱ ትዕዛዝ የሰጠው የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ነው፡፡ ሚኒስቴሩ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት መመርያዎቹ የወጡበት መንገድና የመሠረታዊ የሥራ ለውጡ ተጠንቶ እንዲቀርብለት ጨምሮ አዟል፡፡ ምንጮች እንደገለጹት፣ ኤጀንሲው መመርያ በማውጣት በኩል ያለው ሥልጣን ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡፡ የመሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ (ቢፒአር) ጥናት የተገበረው ሚኒስቴሩን ሳያማክርና ሚኒስቴሩ ሳያፀድቀው ነው ተብሏል፡፡  በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ፊርማ ከሥልጣናቸው የተነሱት የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈሪ ፍቅሬ፣ ምክትል ሥራ አስኪያጆች አቶ ኃይሉ ሐደሬና አቶ ገብሩ ባይልብኝ፣ እንዲሁም የቤቶች አስተዳደር የሥራ ሒደት ባለቤት የነበሩትና ተቀይረው ወደ ጥቃቅንና አነስተኛ ኤጀንሲ የተዛወሩት አቶ ኪዳኔ ሥዩም ናቸው፡፡  በእነዚህ ከፍተኛ አመራሮች የሥልጣን ዘመን ከወጡት መመርያዎች ውስጥ እጅግ አነጋጋሪ ሆኖ የቆየውና እስካሁን ትኩሳቱ ያልበረደው የአከራይ ተከራይ፣ የቤቶች አሰጣጥ፣ የጥገናና ፈቃድ አሰጣጥ መመርያዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በተለይ የአከራይ ተከራይ መመርያ ወጥቶ ተግባራዊ በሆነበት ወቅት በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ቀውሶች መፈጠራቸው አይዘነጋም፡፡ ይህ መመርያ የወጣበት ምክንያት በወቅቱ እንደተገለጸው፣ ከኤጀንሲው ቤቶች የተከራዩ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ሸንሽነው ለሌሎች ነጋዴዎች አከራይተዋል፡፡ ይህ አሠራር የኤጀንሲውን ሕግጋት ይፃረራል በሚል ነው፡፡