Posts

በተያያዘ ዜናም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊን 1ኛ አመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ የሲዳማ ዞን ጭሬ ወረዳ ነዋሪዎች የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጀጐ አገኘው በችግኝ ተከላው ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በተለይ በአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ላይ በኢትዮጵያም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ራዕይ ነበራቸው፡፡ ይህንንም ራዕያቸውን ለማሳካት በወረዳው 14 ፓርኮች ተለይተው በ127 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ ለመትከል ከታቀዱት 32 ሺህ ችግኞች ግማሽ ያህሉ ተከላ ተከናውኗል ብለዋል፡፡ ቀሪ ችግኞችን የመትከሉ ሁኔታም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው  አቶ ጀጐ የገለፁት፡፡ በችግኝ ተከላው ያነጋግርናቸው የወረዳው ነዋሪዎችም ችግኞችን በመንከባከብ ረገድም ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ የአረንጓዴ ልማቱን እናሳካለን ማለታቸውን የዘገበው በኃይሉ ጌታቸው ነው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/16NehTextN305.html

የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጅ ተግባራዊ ያደረጉ ከ98 ሺህ የሚበልጡ ሞዴል ቤተሰቦች ተመረቁ

ሐዋሳ ነሐሴ 20/2005 በሲዳማ ዞን በተጠናቀቀው በጀት አመት በአንድ ለአምስት ትስስር ሰልጥነው የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆችን ተግባራዊ ያደረጉ ከ98 ሺህ የሚበልጡ ሞዴል ቤተሰቦች መመረቃቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ፡፡ በመምሪያው የጤና ልማት እቅድ የሥራ ሂደት ባለሙያ አቶ አበበ በካ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት በዞኑ የጤና ልማት ሠራዊት ግንባታን በማጠናከር የጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራምን ስኬታማ ለማድረግ የአንድ ለአምስት ትስስር አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በዞኑ የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆችን ተግባራዊ በማድረግ በሽታን የመከላከል የጤና ፖሊሲ ውጤታማ እንዲሆን በተፈጠረው የአንድ ለአምስት ትስስርት በተጠናቀቀው በጀት አመት ስልጠና ወስደው የጤና ኤክስቴሽን ተግባራዊ ያደረጉ ሞዴል ቤተሰቦች መመረቃቸውን ተናግረዋል፡፡ ከ30 ሺህ በላይ ቤተሰቦች አሁንም ስልጠና እየወሰዱ መሆኑንና ከዚህ በፊት የተመረቁትን ጨምሮ ሞዴል የጤና ቤተሰቦች ቁጥር በዞኑ 603 ሺህ 367 መድረስ እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡ ከሁለት አመት በፊት በዞኑ ከተሞች በተጀመረው የከተማ ጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም የሰለጠኑ 2 ሺህ 337 የከተማ ሞዴል የጤና ቤተሰቦች መመረቃቸውን አቶ አበበ ተናግረዋል፡፡ የተመረቁት የጤና ሞዴል ቤተሰቦች በግልና አካባቢ ንጽህና፣በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ፣በመፀዳጃ ቤት ንጽሕና አያያዝ፣በገጠር መፀዳጃ ቤት በመገንባት ተጠቃሚና የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ የቻሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=11234&K=1

ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ማን ይሆኑ?

Image
ኢትዮጵያን ላለፉት 12 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩት ሁለተኛው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የሥራ ዘመናቸው በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ከአንድ በኋላ ወር በመስከረም 2006 ዓ.ም. ማጠናቀቂያ አካባቢ ሦስተኛው ፕሬዚዳንት ይሰየማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሦስተኛው ፕሬዚዳንት ማን ሊሆኑ ይችላሉ? ወይም ይገመታሉ? ለሚሉ ጥያቄዎች የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ግምታቸውንና በመረጣ ወቅት ምን መደረግ እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ገዥው  ፓርቲ ኢሕአዴግ ሦስተኛውን ፕሬዚዳንት በሚቀጥለው ወር ይፋ ያደርጋል፡፡ በሌላ በኩል የፕሬዚዳንትነቱ የሥራ ኃላፊነት ያን ያህል ትርጉም ስለሌለው እንደማያስጨንቃቸው የሚናገሩም አሉ፡፡ የመጀመሪያው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በ1987 ዓ.ም. በተደረገው የፓርላማ ምርጫ ተወዳድረው ከተመረጡ በኋላ፣ በወቅቱ የአመራር አባል የነበሩበት ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች በደረሱበት ውሳኔ መሠረት ፕሬዚዳንትነታቸው በፓርላማ ፀድቆ፣ እስከ 1993 ዓ.ም. ድረስ ከኢሕአዴግ ጋር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስከሚለያዩ ድረስ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ቆይተዋል፡፡ ከእሳቸው በመቀጠል በቅርቡ የሚሰናበቱት አቶ ግርማ ላለፉት አሥራ ሁለት ዓመታት ቆይታ አድርገዋል፡፡ በሕገ መንግሥቱ መሠረት አንድ ፕሬዚዳንት ከዚህ በላይ ስለማይቆይ በአዲሱ ዓመት ሦስተኛው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ይሰየማሉ፡፡ ምንም እንኳ ኢሕአዴግ ቀደም ብሎ ለሕዝቡ የማሳወቅ ባህል ባይኖረውም፣ በኅብረተሰቡ ውስጥ የተለያዩ ግለሰቦች ስሞች እየተነሱ ናቸው፡፡ ለፕሬዚዳንትነት በዕጩነት ስማቸው የሚነሱ ግለሰቦችንና የተሰጡ አስተያየቶችን የያዘው ዝርዝር ዘገባ  ለመመልከት እዚህ ይጫኑ፡፡ በመሀል አዲስ አበባ ከአራት ኪሎ ወደ መስቀ

የግሉ ዘርፍ በሙስና የሚጠየቅበት ረቂቅ ሕግ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊፀድቅ ነው

Image
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ በግሉ ዘርፍ የሚካሄዱ የሙስና ተግባራት ዕርምጃ እንዲወሰድ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ተነጋግሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ገለጹ፡፡ ‹‹የሙስና ወንጀሎችን እንደገና ለመደንገግ የወጣ ረቂቅ አዋጅ›› በሚል የተዘጋጀው የፀረ ሙስና አዋጅ ከፀደቀ፣ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አንደኛው ክንፍ ፊቱን ወደ ግሉ ዘርፍ እንደሚያዞር እየተነገረ ነው፡፡  ለፀረ ሙስና ኮሚሽን የቀረበው የረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ እንደሚያስረዳው፣ ‹‹ሕዝባዊ ድርጅት›› የሚባሉት ከሕዝቡ የተሰበሰበ ገንዘብ ወይም ንብረት የሚያስተዳድሩ አካላት ሲሆኑ፣ በተለያዩ መንገዶች የሚቋቋሙ ማኅበራት፣ የአክሲዮን ኩባንያዎች፣ በአክሲዮን የተቋቋሙ ባንኮችና የኢንሹራንስ ተቋማትን ያጠቃልላል፡፡  ይህ የሕግ ረቂቅ ታኀሳስ 2005 ዓ.ም. ተዘጋጅቶ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ለውይይት በቀረበበት ወቅት፣ ለፀረ ሙስና ኮሚሽን ከተለያዩ አቅጣጫዎች በርካታ ጥቆማዎች መቅረባቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡  ለፀረ ሙስና ኮሚሽን የቀረበው የጥቆማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ነው የሚሉት ምንጮች፣ ኮሚሽኑ እየከናወነ ካለው በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ላይ ያነጣጠረ ሥራ ብዛት አንፃር ሊከብደው እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ በዚሁ መነሻነት ኮሚሽኑ ሊኖረው ስለሚገባው አዲስ ቅርፅና የሰው ኃይል አደረጃጀት የኮሚሽኑ ኃላፊዎች ውስጥ ውስጡን መነጋገር መጀመራቸው ታውቋል፡፡  በአሁኑ ጊዜ ኮሚሽኑ ባለው የሰው ኃይል በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አለ በሚባለው የሙስና ወንጀል ላይ ምርመራ አድርጎ ክስ ለመመሥረት አስቸጋሪ እንደሆነበት፣ በዚህ የሰው ኃይል በግሉ ዘርፍ ሙስና ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ጫና ሊፈጥርበት ይችላል የሚል ሥጋት መፈጠሩን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡

‹‹የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ስድስት ዓመት ገለልተኛ ሆኖ ካገለገለ በኋላ ነፃ ሆኖ ሐሳቡን መግለጽ መቻል አለበት››

Image
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የመጀመሪያው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ከሽግግር መንግሥቱ በኋላ በኢትዮጵያ በሦስት ዙር (ተርም) ሁለት ርዕሰ ብሔሮች [ፕሬዚዳንቶች] ተሰይመዋል፡፡ ላለፉት 12 ዓመታት በሥራ ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በ2005 ዓ.ም. የሥራ ዘመናቸው ያበቃል፡፡ በ2006 ዓ.ም. በመስከረም ወር መጨረሻ አካባቢ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ጉባዔ ሲከፈት ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት የሚያገለግሉ አዲስ ፕሬዚዳንት ይሰየማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ወደተንጣለለው ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ማን ሊገባ ይችላል የሚለው ጉዳይ እስካሁን ባይታወቅም፣ የተለያዩ የኅብረተሰቡ ክፍሎች የተለያዩ ሰዎችን ሰብዕና በመምዘዝ እየተነጋገሩ ነው፡፡ ገዥው ፓርቲም በዚህ ጉዳይ ላይ መጠመዱ ተሰምቷል፡፡ ኢትዮጵያ ፓርላሜንታዊ ሥርዓት የምትከተል አገር ተደርጋ የኢፌዲሪ መንግሥት ሲመሠረት፣ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሆነው መንበሩን የተቆናጠጡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ነበሩ፡፡ ከፕሬዚዳንትነታቸው ቆይታ፣ ከቤተ መንግሥት ሕይወትና ከቀጣዩ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አሿሿምና ተግባር ጋር በተያያዘ የአሁኑን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶን  ውድነህ ዘነበ   አነጋግሯቸዋል፡፡  ሪፖርተር፡- የኢፌዲሪ መንግሥት ሲመሠረት የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሆነው የተሰየሙት እርስዎ ነበሩ፡፡  የተመረጡበት ሒደት እንዴት ነበር? የተጠቆሙ ሰዎችስ ነበሩ? ዶ/ር ነጋሶ ፡- በ1987 ዓ.ም. ከምርጫው በፊት ነው የሆነው፡፡ ሒደቱ አሁን ተለውጦ ከሆነ አላውቅም፡፡ የዚያን ጊዜ በሥራ አስፈጻሚ ተነጋግረን ሦስት ሐሳቦች ቀረቡ፡፡ አንደኛ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ፣ ሁለተኛ ፕሮፌሰር ጀማል አብዱልቃድር [የኦሕዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ]፣ ሦስተኛ አም