Posts

The False Banana, Key to Food Security

Image
One study from Debub University in Hawassa  notes  that the Ethiopian government has historically promoted research and development of cereal crops, which are more susceptible to natural disasters such as drought, and are typically sold for profit instead of directly generating food security and benefitting local communities.  The Tree Against Hunger  offers several potential reasons for a focus on cereals instead of enset. Enset production is complex and varies based on location, making it unappealing for many development programs, even for domestic Ethiopian aid initiatives. It also is primarily produced in some of the areas of Ethiopia that are least developed and most difficult to access. These barriers, and the tendency for Western developmental aid to focus on cereal production have limited international extension programs designed for enset. With high cereal prices and low yields, the importance of generating awareness and investing research and resources into enset production

የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት በሀገር ውስጥ ሊመረት ነው

Image
የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት በሀገር ውስጥ ሊመረት ነው ፡፡ በሀገር ደረጃ የኤች.አይ.ቪ (ኤድስ) ስርጭት እየቀነሰ ቢመጣም ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበት ተጠ ይቋል ፡፡ በኤች.አይ.ቪ(ኤድስ) ላይ የሚሰሩ የተለያዩ አካላት በጋራ የሰጡት መግለጫ ከገጠሩ ይልቅ በከተማ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በሰፊው መሰራት አለበት ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጤናና ስነ-ምግብ ኢኒስቲትዩትን በመወከል ዶ/ር ይበልጣል አሰፋ በተለይም በፀረ የኤች.አይ.ቪ መድሃኒት አጠቃቀም ላይ በሰፊው መስራት እንደሚፈልግ ነው የገለፁት፡፡ ዶ/ር ይበልጣል እንደሚሉት የፀረ የኤች.አይ.ቪ መድሃኒት አጠቃቀም እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም በተለይ በመረጃ አሰጣጥ ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡ የጸረ ኤች.አይ.ቪ (ኤድስ) መድሀኒትን በ2007  መጨሻ ላይ በሀገር ውስጥ ለማምረት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም የኢትዮጵያ ጤናና ስነ-ምግብ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡ ቅደመ ዝግጅቱ ሲጠናቀቅም 5 የጸረ ኤች.አይ.ቪ (ኤድስ) መድሀኒት አምራች ፋብሪካዎች ወደ ስራ ሊገቡ እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡ የፌደራል ኤች.አይ.ቪ (ኤድስ) መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ም/ዳይሬክተር አቶ መስቀሌ ሌራ እንደሚሉት ደግሞ የኤች.አይ.ቪ (ኤድስ) ስርጭቱ ለስራ በሚንቀሳቀሰው ወጣቱ ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካይ ዶክተር ፍሬሕይወት መብራቱ በበኩላቸው እስከአሁን ድረስ ኤች.አይ.ቪ (ኤድስን) በተመለከተ የተሰራው ሥራ ውጤት አያሳ በመምጣቱ ጥረቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ በተለይም ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ እቅድ ተዘጋጅቶ ቫይረሱ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ እንደሚሰራም ነው የገለጹት፡፡ የኤች.አይ.ቪ (ኤድስ) ሥርጭትን በተመለከተ ከወንዶች ይ

የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር ዛሬም አልተፈታም

Image
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 17 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት መቆራረጥ በመዲናችን አዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች እየተባባሰ የመጣ ችግር ሆኗል ። ሃገሪቱ እያመነጨች ያለው የኤሌክትሪክ ሃይል በቂ የሚባል ቢሆንም የአገልግሎት ጥራት መጓደል ግን በብዙዎች ዘንድ ተደጋጋሚ ቅሬታን እያስነሳ ነው ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ችግሩ መኖሩን አምኖ ይቀበላል ፤ የኬርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምህረት ደበበ እንደሚሉት ፥ የኤሌክትሪክ መቆራረጡ በማህበረሰቡና በሃገሪቱ ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ከፍተኛ ነው። ከዚህ ቀደም ለጣቢያችን ቅሬታቸውን ያቀረቡ አካላት በየአካባቢው የሚተከሉ የሃይል ማሰራጫ ትራንስፈርመሮች ጥራት የጎደላቸው መሆን የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞችም ፈጣን ምላሽ አለመስጠት፤ ከዚህም አለፍ ሲል እጅ መንሻ ይቀበላሉ ሲሉ ሮሮ ማሰማታቸው የሚታወስ ነው። አቶ ምህረትም  በኮርፖሬሽኑ ውስጥ መልካም ስነ ምግባር የሌላቸው ሰራተኞች መኖራቸውን በማመን ቅሬታው ተገቢ መሆኑን ይቀበላሉ። የሲቪል ሰርቪስ ሚንስቴርም ባካሄደው ጥናት  ህዝቡ ቅሬታ ከሚያሰማባቸው የፌደራል ተቋማት መካከል አንዱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ነው። ችግሩ የኮርፖሬሽኑን አቅም እንደተፈታተነው ያመኑት ሃላፊው ጉዳዩ በመንግስት ደረጃ እየታየ መሆኑን ጠቅሰው ፥ ከዚህ ጎን ለጎንም ኮርፖሬሽኑ ማዕከላትን አደራጅቶ እየሰራ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ ቀድሞ የነበሩ  አሁንም ያልተፈቱና ለኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ ምክንያት የሆኑ እክሎች እንዳሉ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ በስፋት እየተካሄዱ ያሉት የመንገድ ፣ የባቡርና የውሃ መስመር ዝርጋታዎች ተጠቃሽ ሲሆኑ ፥ እነዚህን መሰረተ ልማቶች ለመዘርጋት በሚደረገው ጥረት በርካታ የኤሌክትሪክ

በሀገሪቱ በኤችአይቪ\ኤድስ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱ ተገለፀ

Image
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2005/ዋኢማ/ - በሀገር አቀፍ ደረጃ በኤችአይቪ ኤድስ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን የፌዴራል ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መስቀሌ ሌራ ዛሬ በጋራ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለፁት፤ በቫይረሱ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 0 ነጥብ 9 በመቶ ቀንሷል፡፡ ለተገኘው ውጤትም መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ህብረተሰቡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ጠቁመው፤ በተለይም መንግስት ግልፅ የሆነ እስትራቴጂክ እቅድ በመቅረፅ በጠንካራ አመራር ተግባራዊ በማድረጉ ነው ብለዋል፡፡ የቫይረሱን ስርጭት ይበልጥ ለመከላልና ለመቆጣጠርም የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፤ በተለያዩ ዘርፎች ለማሳካት የታቀደውን እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከግብ ለማድረስ ወጣቱ ትውልድን ከቫይረሱ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አቶ መስቀሌ ተናረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጤናና ስነ-ምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ይበልጣል አሰፋ በበኩላቸው፤ በአጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱም ስለ ኤችአይቪ ኤድስ አጠቃላይ ጥናት እንደሚያደርግ ተናግረው፤ በዚህ መሰረትም በአሁኑ ወቅት ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ውስጥ 1 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት አዋቂዎች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት በወንዶች 1 በመቶ ሲሆን በሴቶች ደግሞ 1 ነጥብ 9 በመቶ መሆኑን ጠቁመው፤ የቫይረሱ ስርጭት በከተማና በገጠር ያለው እንደሚለያይ ተናግረዋል፡፡ በዚህ መሰረትም በከተማ ያለው የቫይረሱ ስርጭት 4 ነጥብ 2 በመቶ ሲሆን፤ በገጠር ደግሞ 0 ነጥብ 6 መሆኑን ዶክተር ይበልጣል ገል

የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ችግር ፈቺ ከ200 በላይ የምርምር ፕሮጀክቶች እያካሄደ ነው

Image
ሃዋሳ ነሐሴ 17/2005 የሃዋሳ ዩኒቨርሰስቲ ችግር ፈቺ የሆኑ ከ200 የሚበልጡ የምርምር ፕሮጀክቶች በራሱና በውጪ ሀገራት ትብብር እያካሄደ መሆኑን ገለጠ። በዩኒቨርሰቲ የምርምር ፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር አለማየሁ ረጋሳ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት የምርምር ስራዎቻቸውን በየአመቱ በማስፋፋት በአሁኑ ውቅት 180 ፕሮጀክቶች በራሳቸው አቅምና ከ40 በላይ ደግሞ በውጪ ሀገራት ትብብር እየተካሄደ ነው። ከምርምር ፕሮጀክቶቹ መካከል ትምህርት ፣ግብርና፣ተፈጥሮ ሀብትና እፅዋት ሳይንስ፣እንስሳት ጤና፣አግሮኖሚ፣ ኑውትሪሽንና ሌሎች ማህበራዊና የኢኮኖሚ ተጠቃሜታ ያላቸው እንደሚገኙበት አስታውቀዋል። በክልሉ ወረዳዎች በተመረጡ ስድስት የቴክኖሎጂ መንደሮች የሚያካሄዳቸው ምርምር ስራዎች ከስድስት ወራት እሰከ ሶስት አመታት እንደሚቆዩ ገልጸዋል። የምርምር ስራዎቹ ችግር ፈቺና ህብረተሰብ አሳታፊ መሆናቸውን አመልክተው ህብረተሰቡን ከመጥቀም ባሻገር የመምህራንን የብቃት አቅም ያሳድጋል፣የትምህርት ጥራትን በመጠበቅ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጠዋል። ከዚህ በፊት የሚካሄዱ የምርምር ውጤቶች ሼልፍ ላይ ይቀሩ እንደነበር በማስታወስ አሁን ለህብረተሰቡ ቅርበት ባላቸው የቴክኖሎጂ መንደሮች በመሞከር በማላመድና ወደ ምርት ስራ በማሸጋገር እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ በሰፊው እየተሰራ ነው ብለዋል። ለምርምር ስራው በዩኒቨርሰቲ በኩል 5 ሚሊዮን ብር መመደቡን አመልክተው በእያንዳንዱ የምርምር ፕሮጀክቶች ከአንድ እስከ አራት ተመራማሪዎች እንደሚሳተፉ ዶክተር አለማየሁ ተናግረዋል። ከውጪ ሀገራት ኖርዌይ፣ ካናዳ፣ አሜሪካና የሌሎች ሀገራት ዩኒቨርሰቲዎች የምርምር ስራውን በትብብር ለማካሄድ ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑን ገልጠዋል። መንግሰት የጀመረው