Posts

“Sidama Camping”, Year 2

Image
This past weekend we went camping in Southeastern New Hampshire with a group of Ethiopian adoptive families — our second straight year. The core group of campers go way-back and have mid-teenaged girls, but they open the camping to any Ethiopian adoptive families, and Little Boy has such a blast last year with the older kids that we could not say “No” to  a second year. He calls it “Sidama camping,” because that’s what we call it, because more than a few of the kids are of Sidama origin and bear a strong physical resemblance to Little Boy. http://www.meredithgreen.com/?p=8904 source:  http://www.meredithgreen.com/?p=8904

SIDAMA PEOPLE: ETHIOPIA`S KUSHITIC EXPERT COFFEE GROWERS

Image
The Sidama people agricultural and semi-pastoral Kushitic people living in the southern part of the Ethiopia, in the Horn of Africa. The majority of the Sidama people live in the Southern part of Ethiopia with notable geographical features like lake Awassa in the North and lake Abaya in the South. Sidama region of Ethiopia is home of the Sidamo Coffee. The area is characterised by lush green countryside making it known as the Garden of Ethiopia. The Sidama along with Agew and Beja were the first settlers in the northern highlands of the present day Ethiopia before the arrival of Yemeni habeshas (Abyssineans). The Sidama people and their sub-tribes ( major Sidama group, Alaba, Tambaro, Qewena and Marakoare) are estimated to be around 8 million; constituting 4.01%  of the Ethiopian population and are the fifth largest ethnic group in Ethiopia.                                       Beautiful Sidama tribe woman from Sidama region, Ethiopia Like other comparable communities, th

በመኸር እርሻ ሥራ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደገ እየሰሩ መሆናቸውን በሲዳማ ዞን የጐርቼ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ፡፡

በወረዳው በ2ዐዐ5 እና በ2ዐዐ6 ዓ/ም የመኸር እርሻ ከ3 ሺህ 57ዐ  ሄክታር በላይ መሬት በዋና ዋና ሰብሎች ዘር ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡፡ አርሶ አደር አመሎ ኪቦ አና አርሶ አደር ቀጤ ወጀቦ በወረዳው የሐርቤ ሚቀና ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ የመኸር እርሻ ሥራን ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ገልፀው በተለያዩ ጊዜያት ባገኙት የክህሎት ሥልጠና በመጠቀም ጥምርታቸውን በጠበቀ መልኩ በመዝራት ላይ እንዳሉ ተናግረዋል፡፡ የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ስጦታው ከንባታ በበኩላቸው በ2ዐዐ5 እና በ2ዐዐ6 ዓ/ም የመኸር እርሻ ከ3 ሺህ 57ዐ ሄክታር በላይ መሬት በዋና ዋና የሰብል ዘሮች ለመሸፈን የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝና እስከ አሁንም 3 መቶ 36 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈናቸውን ገልፀዋል፡፡ በመኸር እርሻ በዘር ከሚሸፈን ማሳ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል ሲል የዘገበው የወረዳው የመንግሰት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው፡፡ ምንጭ፦ http://www.smm.gov.et/_Text/13NehTextN805.html

በሲዳማ ዞን ጐርቼ ወረዳ የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲ እውን ለማድረግ ከ12 ሺህ በላይ ችግኝ ተክለዋል፡፡

Image
በችግኝ ተከላው የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰንበቱ ተካ የአረንጓዴ ልማት ቀያሽ ከሆኑት ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተር የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠል ህዝቡና አመራሩ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ህብረተሰቡም  በችግኝ ተከላውና በፓርክ ምስረታው ላይ ያሳየውን ቁርጠኝነት በእንክብካቤ ስራው ላይም አጠናክሮ ሊቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡ በችግኝ ተከላው ወቅት ያነጋገርናቸው አንዳንድ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርን የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ለማሳካት የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል፡፡ በወረዳው በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስም በሁሉም ቀበሌያት ፓርኮች ተቋቁመዋል ከ12 ሺህ በላይ ችግኞችም ተተክለዋል ሲል የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዘግቧል፡፡ የዞኑ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ አሸብር ልሳኑ በበኩላቸው ከፓርኩ የሚገኘው ገቢ በዚሁ አካባቢ ለሚገኙ ማህበረሰቦች የተለያዩ የመሰረተ ልማት አውታሮች እንደሚሟሉበት ተናግረው  ህብረተሰቡ ፓርኩን በባለቤትነት እንዲቆጣጠርም ጭምር አሳስበዋል፡፡ በዚሁ ዙሪያ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በተደረገ ውይይት ፓርኩ የማንም ሳይሆን የራሳችን በመሆኑ ከዚህ በኃላ የሚፈጠረውን ጥቃት ለመከላከል ወንጀለኞችን አሳልፈን ለህግ እንሠጣለን ሲሉ የሀገር ሽማግሌዎች ተናግረዋል፡፡ የደቡብ ኦሞ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አንደዘገበው፡፡ ምንጭ፦ http://www.smm.gov.et/_Text/13NehTextN705.html

የባንኮች የውጭ ምንዛሪ ግዢና አጠቃቀም ግልጽነት ይጐድለዋል

Image
የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ከሚያገኝባቸው ምንጮች መካከል የውጭ ንግድ (Export) እና በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በባንኮች በኩል የሚልኩት ገንዘብ (Remittance) ዋናዎቹ ናቸው፡፡ መንግሥት የውጭ ንግዳችን እንዲያድግና ለገቢ ንግዳችን (Import) የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ሰፊ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዋናነት በቡና ላይ ተመሥርቶ የነበረው የውጭ ንግዳችን ዛሬ መሠረቱ ሰፍቶ አበባ፣ ቆዳ፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ የቅባት እህሎች፣ የቁም ከብቶችና ሌሎችም ተጨምረዋል፡፡ በውጭ ንግድ ላይ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች መሬት በአነስተኛ ዋጋ ከማቅረብ ጀምሮ ከውጭ የሚያስገቧቸው መሠረታዊ ዕቃዎች በአብዛኛው ከቀረጥና ታክስ ነፃ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ላኪዎች ገንዘብ ከባንኮች በአነስተኛ ወለድ ያገኛሉ፡፡ ከባንኮች ለሚበደሩት ገንዘብም መንግሥት ዋስትና የሚሰጥበት አግባብ አለ፡፡ ምርታቸውንም ተወዳዳሪ እንዲሆን ያለምንም ቀረጥና ታክስ ወደ ውጭ አገር ልከው እንዲሸጡ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ማበረታቻ ተደርጎለት የሚገኝ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም ላይ ክፍተት ይታያል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ አገር ገንዘቦች መግዣና መሸጫ ዋጋን ይወስናል፡፡ የየቀኑ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫም ዋጋም በሬድዮና በቴሌቪዥን ከምንስማው ባፈነገጠ መልኩ ባንኮች ከመግዣ ዋጋ በተጨማሪ በመግዣና በመሸጫ መካከል ባለው ዋጋ (Mid rate)፣ አንዳንዴም በመሸጫ ዋጋ (Selling rate) ከላኪዎች (Exporters) እንደሚገዙ ይሰማል፡፡ በተለይ የዚህ ዓይነት የውጭ ምንዛሪ ግዢ በአገሪቱ የጠረፍ ከተሞች በኩል ከሚወጡ ዕቃዎች ሽያጭ በሚገኝ የውጭ ምንዛሪ ላይ እንደሚበረታታ ውስጥ አዋቂዎች ይገልጻሉ፡፡ አፈጻጸሙም ግልጽነት የጎደለው፣ ሙስ