Posts

ካላ በቀለ ዋዪ የቀድሞ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ከፍተኛ ኣመራር ከሰይፌ ነበልባል ሬድዮ ጋር በወቅታዊ የሲዳማ ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በተመለተከ ያላችሁን ጥያቄ እና ኣስተያየት ይላኩልን

Image
ፎቶ  https://www.facebook.com/bekele.wariyo/photos ካላ በቀለ ዋዪ የቀድሞ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ከፍተኛ ኣመራር ከሰይፌ ነበልባል ሬድዮ ጋር በወቅታዊ የሲዳማ ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በተመለተከ ያላችሁን ጥያቄ እና ኣስተያየት በሚከተለው ኣድራሻ ይላኩል፤ ምላሻቸውን ጠይቀን እናቀረባለን፦ nomonanoto@gmail.com  እናመሰግናለን።  ካላ በቀለ ዋዪ በቃለ ምልልሱ የተነሱ ኣንኳር ጉዳዮች በሲዳማ ህዝብ ላይ የሚደርስውን ኣስተዳደራዊ በደል  የሲዳማ ህዝብ የመልካም ኣስተዳደር  ጥያቄ የሲዳማ ህዝብ የራስ ገዝ የክልል ኣስተዳደር ጥያቄ በመንግስት ሰለመታፈን   ካላ በቀለ ዋዪ በወቅታዊው የሲዳማ የፖለቲካ ሁኔታ እና የክልል ጥያቄ በተመለከተ ከሰይፌ ነበልባል ሬድዮ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

እነ “ሻኪራ” በአሞራ ገደል

Image
የዛሬ ሳምንት ሀዋሳ ነበርኩኝ፡፡ የወትሮዋ ሳቂታዋ ሀዋሳ አልነበረችም፡፡ አኩርፋለች፡፡ ሌላ ችግር ገጥሟት ግን አይደለም፡፡ ክረምቱ ነው ያስኮረፋት፡፡ ዝናቡ፣ ቅዝቃዜውና ደመና የሸፈነው ሰማይ ተጫጭነዋት ነበር፡፡ እንደኔ እንደኔ ሀዋሳ ደርሶ አሞራ ገደልን ሳይጐበኙ መመለስ ካለመሄድ እኩል ነው፡፡ እዚህ ስፍራ ዓሳ እንደጉድ ይበላል፡፡ ያውም ቁጥር - ልክ እንደ ስጋ፡፡ የአሳ ቁርጥ ተመጋቢዎች በእንጨት ግድግዳ በተከበበው ዳስ መሳይ ቤት ውስጥ ግፊያውና መረጋገጡን ተያይዘውታል፡፡ በሀዋሳ ሀይቅ ዳር ባለው በዚህ ስፍራ ሰው ከአንድ ቦታ አሳውን ይገዛና እዛው ዳስ ቤት ውስጥ የአሳውን እሾክ እያስወጣ ቁርጡን በሳህን እየያዘ ማባያውን ለማግኘት ሁለት ጐን ለጐን የተቀመጡ ማባያ አቅራቢዎች ጋር መገናኘት ይጠበቅበታል፡፡ አንዱ “ዳጣ” የተባለው እና ከሚጥሚጣ እንዲሁም ከሌሎች ቅመሞች የተሰራ የሚያቃጥል ማባያ ሲሆን (እኔ በጣም ከማቃጠሉ የተነሳ “እንላቀስ” ብየዋለሁ) ሁለተኛው ትንንሽ ክብ የበቆሎ ቂጣዎች ናቸው፡፡ ሁለት ወጣቶች የአሳ ቁርጥ ከግፊያው ውስጥ ይዘው ወጥተው አንዱ ሌላውን፣ “ሂድና ሲዲ ይዘህ ና፣ ታዲያ ስክራች እንዳይኖረው” ሲል አስጠነቀቀው፡፡ ሲዲ ምንድነው ስል ጠየቅሁት አንዱን ወጣት፡፡ “ሲመጣ ታይዋለሽ” አለና ዳጣ ሊያስጨምር መስከረም ወደ ተባለች ዳጣ ሻጭ አመራ፡፡ እኔም ስክራች እንዳይኖረው የተባለውን ሲዲ በጉጉት መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ ለካስ ሲዲ የሚሉት የበቆሎውን ቂጣ ነው፡፡ “ስክራች” የተባለው ደግሞ ያረረ እና የተሰነጣጠቀ እንዳይሆን ለማለት የተጠቀሙበት አገላለፅ ነው፡፡ ከወጣቶቹ የእንብላ ግብዣ ቀረበልኝ፡፡ የአሳ ቁርጥ በልቼ ስለማላውቅ ብፈራም “ሲዲ”ውን በዳጣ ግን አልማርኩትም፡፡ ወጣቶቹ ቁርጡን እየበሉ ሳሉ አንዱ “ሲዲውን በርን (burn)

በሲዳማ ዞን ከ424 ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የተለያዩ በሽታዎች መከላከያ ክትባት ተሰጠ ተባለ

ሃዋሳ ነሐሴ 15/2005 በሲዳማ ዞን በተጠናቀቀው የበጀት አመት ከ424 ሺህ ከሚበልጡ ህፃናት የተለያዩ በሽታዎች መከላከያ ክትባት መሰጠቱን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ ። በመምሪያዉ የጤና ልማት እቅድ የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ አበበ በካዬ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት መንግሰት ለህፃናትና እናቶች ጤና መጠበቅ በሰጠው ትኩረት በሽታን አስቀድሞ የመከላከሉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። በዞኑ 19 ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች እድሜያቸው ከአንድ አመት በታች ለሆናቸዉ 424 ሺህ 126 ህፃናት የፖሊዮ ፣ የቲቢ፣ የኩፍኝና የሳንባ ምች በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠቱን አስታዉቀዋል ። በዞኑ በመደበኛ የክትባት አገልግሎት በበጀት አመቱ 105 ሺህ 910 ህፃናት መከተባቸውንም አስረድተዋል። በተጨማሪ 15 ሺህ ለሚሆኑ ከፍተኛ ምግብ አጥረት ችግር ላለባቸው ነፍስጡር እናቶችና ህፃናት የተለያዩ አልሚ ምግቦች እንደተሰጣቸውና ከ 80 ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የቫይታሚን ኤ እደላ መደረጉንም አስረድተዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=11072&K=1

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረትና የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲዎች ውህደት ፈፀሙ

አዲስ አበባ ነሐሴ 15/2005 የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረትና የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲዎች ውህደት መፈጸማቸውን ትናንት አስታወቁ። የኢትዮጵያ ማሕበረ ዴሞክራሲ-ደቡብ ኅብረት አንድነት ፓርቲ (ኢማዴ-ደህአፓ) በሚል አዲስ ስያሜ ውህደቱን ይፋ ያደረገው ይኸው ፓርቲ የፀረ-ሽብር ሕጉን እንደሚቃወም አስታውቋል። የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻው ውህደቱን አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ሁለቱ ፓርቲዎች በአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በነበራቸው የጋራ አቋም ራዕያቸውን በጋራ ለማሳካት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። የኢትዮጵያ ማሕበረ ዴሞክራሲ-ደቡብ ኅብረት አንድነት ፓርቲ (ኢማዴ-ደህአፓ) ሕጋዊ ሰውነት እንዲያገኝ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ በማቅረብ ቦርዱ ሰኔ 3 ቀን 2005 ዓ.ም የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ውህደቱን በትናንትው ዕለት ይፋ ያደረገው ይኸው ፓርቲ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ በአገሪቱ ተግባራዊ የሆነውን የፀረ-ሽብር ሕግን እንደሚቃወም አስታውቋል። እንደ አቶ ጥላሁን ገለፃ የፀረ-ሽብር ሕጉ ሠላማዊ የሕዝቦች ተቃውሞን የማፈን ባህሪይ ስላለው ፓርቲያቸው እንደ ሌሎች የመድረክ አባላት ሁሉ ሕጉን ይቃወማል። ፓርቲው በማኒፌስቶው በግልጽ እንዳስቀመጠው የፀረ-ሽብር ሕጉ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚጋፋ በመሆኑ ሕጉን አጥብቆ እንደሚቃወም ገልጸዋል። በዚህም በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም ፓርቲው ከመፈለግ ባሻገር ትግል እንደሚያደርግ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ማሕበረ ዴሞክራሲ-ደቡብ ኅብረት አንድነት ፓርቲ የኃይማኖት አክራሪነትን፣ የኃይማኖታዊ መንግሥት መቋቋምን እንዲሁም ኃይማ

ሕዝብ ‹‹መልካም አስተዳደር በተግባር!›› እያለ ነው

Image
መንግሥት መልካም አስተዳደር መኖር አለበት ይላል ወይ? አዎን! ኢሕአዴግም በጉባዔው ብሏል፣ በውሳኔም አሳልፏል፡፡ በየቀኑ መግለጫ ይሰጥበታል፡፡ መልካም አስተዳደር እውን የማታደርጉ ወዮላችሁ ብሏል፡፡ የመልካም አስተዳደር አለመኖር አደጋንም ገልጿል፡፡ መንግሥትም ብሏል፣ ኢሕአዴግም ብሏል፣ ሕዝብም ሰምቷል፣ አዳምጧል፡፡  ጥያቄው የተባለው፣ የተወሰነውና ቃል የተገባው መልካም አስተዳደር የት አለ የሚል ነው፡፡ የሕዝቡ ጥያቄ ‹‹መልካም አስተዳደር በተግባር!›› ነውና፡፡ በተግባር ያልታየ ነገር ‹‹ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ›› ነውና፡፡ መንግሥት በፌዴራል ደረጃም በክልል ደረጃም ወደ ተጨባጭና አሳማኝ ተግባር ይግባ፡፡ ይናገር ሳይሆን ያሳይ፡፡  በዚህ መሥሪያ ቤት ሕዝቡ መልካም አስተዳደር አላገኘም ከተባለ መንግሥት ያንን መሥሪያ ቤት ገባ ብሎ መመርመርና መፈተሽ አለበት፡፡ በመልካም አስተዳደር መጥፋት ምክንያት ያላግባብና ከሕግ ውጭ የተሰጠ ጥቅም ካለ ውሳኔው ትክክል አልነበረም በማለት፣ የወሰኑት ሰዎችም መጠየቅ አለባቸው ብሎ የማስተካከያና የእርምት ዕርምጃ መውሰድ አለበት፡፡  በመልካም አስተዳደር ምክንያት በደል የደረሰባቸው ዜጎች ካሉ ፈትሾ ያላግባብና ከሕግ ውጭ መብታቸው ተጥሷል፣ ተጎድተዋል በማለት የደረሰባቸው በደል እንዳይቀጥል አስተካክሎ፣ አርሞና ይቅርታ ጠይቆ ትክክለኛ ዕርምጃ ሊወስድ ይገባል፡፡ ያኔ ነው ሕዝብ እውነትም መልካም አስተዳደር አለ የሚለው፡፡ እውነትም ለመልካም አስተዳደር ከልብ ቆሟል ብሎ ሕዝብ የሚያምነውና ከጎኑ የሚቆመው፡፡ ስለዚህ ተግባር! ተግባር! አሁንም ተግባር! መንግሥት ለመልካም አስተዳደር መስፈን እንቅስቃሴ ሲያደርግ ሥራው ቀላልና ፈጣን ይሆንለታል ማለት አይደለም፡፡ ሴረኛ ያደናቅፈዋል፡፡ ሙሰኛና ፀረ መልካም