የፍትሕ ስባቷና ተደራሽነቷ
የፍትሕ ተደራሽነትን (Access to justice) የፅንሰ ሐሳብ ትንተናና በአገራችን ያለውን አተገባበር መፈተሽ ለባለድርሻ አካላት (ለሕዝቡ፣ ለመንግሥት የፍትሕ አካላት እንዲሁም በመብት ላይ ለሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ያለው አስተዋጽኦ ሰፊ ነው፡፡ የፍትሕ ተደራሽነት የፍትሕ ፅንሰ ሐሳብ አካል ተደርጎ የሚወስድ ሲሆን፣ በራሱም የግለሰቦች መብት ነው፡፡ የፍትሕ ተደራሽነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ባለመብት መሆን ትርጉም ያጣል፡፡ በሕግ የተቀመጡ መብትና ግዴታን አለማወቅ (ወይም ለማወቅ የሚያስችል ሁኔታ አለመኖር)፣ ቢታወቅም የሕግ ባለሙያ ዕርዳታ ባለማግኘት ወይም የዳኝነት ሥልጣን ያላቸው አካላት ተደራሽነት ባለመረጋገጡ መብትን አለመጠየቅ ወይም ለተጣሰ መብት ሕጋዊ መፍትሔ አለማግኘት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው፡፡ ለመሆኑ በአገራችን ያሉ ሕጐች ለግለሰቦች የፍትሕ ተደራሽነት መብት ዋስትና ይሰጣሉ? የመብቱ አፈጻጸምስ በተግባር ምን ይመስላል? የሚሉትን ነጥቦች በፌዴራል ደረጃ መዳሰስ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ነው፡፡ የፍትሕ ተደራሽነት መብት ትርጉም በፅንሰ ሐሳብ ደረጃ የፍትሕ ተደራሽነት መብት የፍትሕ ፈላጊውን ማዕከል በማድረግ ሰፋ ያለ ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ የፍትሕ ተደራሽነት አንድን አጋጣሚ ብቻ የሚመለከት ሳይሆን፣ ፍትሕ ፈላጊው መብቱን ለማስከበር ተገቢ የሆነ መፍትሔ ለማግኘት የሚከተለውን ሒደት በሙሉ ያጠቃልላል፡፡ ግለሰቦች በተለይ ለመብት ጥሰት የተጋለጡ ሰዎች የደረሰባቸውን ኢፍትሐዊነት ለማወቅ የሚያስችላቸውና ኢፍትሐዊነቱ የሕግ የበላይነትን ወይም ሕግን መሠረት አድርጐ እንዲታረም በመንግሥት ተቋማት ውስጥ መፍትሔ የሚያገኙበትን ሒደት የፍትሕ ተደራሽነት መብት ልንለው እንችላለን፡፡ የፍትሕ ተደራሽነት በውስጡ ብዙ መብቶችን የሚያካትት ቢሆንም፣ በዚህ ጽ